Dehai

Goolgule.com: EFFORTን መውረስ ለዶ/ር አብይ ቀዳሚ ተግባር ነው!!!

Posted by: Berhane.Habtemariam59@web.de

Date: Friday, 27 April 2018

 

ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ሆነው የተመረጡ ዕለት ባደረጉት ንግግር የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እድገት እና ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ለማረጋገጥ፣ በተለይ አዳዲስ ባለሃብቶችን እንዲፈጠሩ ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሰሩ ገልፀዋል። ይህን እውን ለማድረግ የጠ/ሚኒስትሩ የመጀመሪያ ተግባር መሆን ያለበት #EFFORTን በመውረስ ወደ ግል ባለሃብቶች ማዘዋወር (privatize) ነው። ምክንያቱም፣

1ኛ) ለሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ልማትና እድገት፣ በተለይ አዳዲስ ባለሃብቶችን በመፍጠሩ ረገድ ዋና እንቅፋት መሆናቸው በዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ በዝርዝር ተገልጿል

2ኛ) #በአርከበ_ዕቁባይ መሪነት ተግባራዊ የተደረገው የሀገሪቱ ኢንዱስትሪ ፖሊስ የEFFORT ድርጅቶችን ተጠቃሚ በማድረግና የግል ቢዝነስ ተቋማትን እድገት በማቀጨጭ ላይ የተመሠረተ ስለመሆኑ ይህን ፅሁፍ ያንብቡ።

3ኛ፦ የEFFORT መነሻ ካፒታል 100ሚሊዮን ዶላር ሲሆን ሙሉ በሙሉ በኢትዮጲያ ህዝብ እና የአለም አቀፉ ማህብረሰብ ላይ በተፈፀመ #ህገ_ወጥ_ዘረፋ የተገኘ ነው። ይህን ማያያዣ በመጫን ዝርዝሩን ማንበብ ይቻላል

4ኛ) የEFFORT ድርጅቶች ጥራት ያለው ምርት በማቅረብ ተወዳዳሪ ከመሆን ይልቅ ከ47ሺህ በሚበልጡ ሰራተኞቹ ላይ የመብት ጥሰት የሚፈፀምባቸው የጭቆና መሣሪያዎች ናቸው

ማጠቃለያ

*1ኛ እና 2ኛ ላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች መሠረት EFFORTን መውረስ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እድገት ከማስቀጠል አንፃር ቀዳሚ ተግባር ነው።

** 3ኛ እና 4ኛ ላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች መሠረት EFFORTን መውረስ ከሞራል አንፃር አግባብ ነው።

ስለዚህ EFFORTን መውረስ ለዶ/ር አብይ ቀዳሚ ተግባር ነው!!!

ስዩም ተሾመ

ምንጭ፤ Seyoum Teshome facebook


ፈንቅል - 1ይ ክፋል | Fenkil (Part 1) - ERi-TV Documentary

Dehai Events