World News

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

Posted by: Semere Asmelash

Date: Wednesday, 25 December 2019

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ።

ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋርም የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ እና የፕሬዚዳንቱ አማካሪ የማነ ገብረአብ በጉብኝቱ ተካተዋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ ለሁለት አስርት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነት ከታደሰ በኋላ በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል።

በአሁኑ ጉብኝታቸውም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

በለይኩን ዓለም

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ ...





EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events