Dehai

(ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ቡና ኤርትራዊውን ሮቤል ተክለሚካኤልና ናትናኤል በርሔን አስፈረመ

Posted by: Semere Asmelash

Date: Wednesday, 07 April 2021

ኢትዮጵያ ቡና ኤርትራዊውን ሮቤል ተክለሚካኤልና ናትናኤል በርሔን አስፈረመ

አዲስ አበባ፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብን ሁለት ተጫዋቾችን ማስፈረሙን አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ቡና የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን አንበል እና የቀይ ባህር እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች የነበረው እና የሴካፋ ሀገራት ውድድር ላይ የውድድሩ  ኮከብ ተጫዋች ተብሎ የተመረጠውን ሮቤል ተክለሚካኤል ማስፈሙን ነው የገለፀው።

በተጨማሪም ለደደቢት እንዲሁም ለከፋ ቡና የተጫወተውን ናትናኤል በርሔን እንዳስፈረመ በክለቡ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ላይ ገልጿል።

ሁለቱ ተጫዋቾች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የሚያቆያቸውን ስምምነት ከክለቡ ጋር ተፈራርመዋል።


EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events