Dehai

Satenaw.com: የአገር ክህደት ወንጀል በፈጸሙ 76 ጄነራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች እና የበታች ሹማምንቶች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ወጣ

Posted by: Berhane Habtemariam

Date: Sunday, 22 November 2020

ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ ሙሉ መግለጫ

በትግራይ ክልል በሚገኘው በሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም አገር የማፍረስ ሴራ አቅደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩና የአገር ክህደት ወንጀል የፈጸሙ የጁንታው ሕወሓት ወንበዴ ቡድን የበላይ የሥራ ኃላፊዎችን አድኖ ለህግ ለማቅረብ ከሳምንት በፊት ማለትም ህዳር 3/2013 ዓ.ም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደወጣባቸው መገለፁ ይታወቃል፡፡

በተመሳሳይም ከጁንታው የሕወሓት ቡድን አባላት ጋር እየተገናኙ አገር በማፍረስ ሴራ ውስጥ በመሳተፍ የሀገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጄነራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች እንዲሁም በፖሊስ አመራሮች ላይ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው ያስታወሰው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን መግለጫ፤ ከጁንታው የሕወሓት የጥፋት ቡድን አገር የማተራመስና የማፍረስ ሴራ እጃቸውን ባስገቡና በአገር ክህደት ወንጀል የተሳተፉ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ተከታትሎ በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የማድረግ ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ኮሚሽኑ ገልጿል።

በዚህም መሰረት በሀገር መከላከያ ሠራዊት በስራ ላይ ያሉና በጡረታ የተሰናበቱ ጄነራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች የተጣለባቸውን ህዝባዊና አገራዊ አደራና ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው እና የጁንታው የሕወሓት ቡድን የሴራ አካል በመሆን የአገር ክህደት ወንጀል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችንም አድኖ ለህግ ለማቅረብ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጠባቸው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን መግለፅ ይወዳል፡፡
የሀገር ህልውናን አደጋ ላይ በመጣልና ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል በመናድ ወንጀል ውስጥ በመሳተፍ የሚፈለጉትና የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው በስራ ላይ ያሉና በጡረታ የተሰናበቱ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጄነራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች ፡-

  1. ሜጀር ጀነራል ማህሾ በየነ
  2. ሜጀር ጀነራል መሀመድ አይሻ ዘይኑ
  3. ሜጀር ጀነራል ሙሉ ግርማይ ገ/ህይወት
  4. ሜጀር ጀነራል ሀለፎም እጂጉ
  5. ብርጋዴል ጀነራል ፍትዊ ፀሃዬ ገ/እግዚአብሔር
  6. ብርጋዴል ጀነራል ግደይ ሀይሉ ገ/እግዚአብሔር
  7. ብርጋዴል ጀነራል ነጋሽ ዳኘው
  8. ብርጋዴል ጀነራል መብራቱ ወ/አረጋይ
  9. ብርጋዴል ጀነራል ወልደ ጊዮርጊስ
  10. ብርጋዴል ጀነራል አብዲሳ ፍላንሳ
  11. ብርጋዴል ጀነራል ጉሽ ገብሬ
  12. ብርጋዴል ጀነራል ከበደ ፍቃዱ
  13. ብርጋዴል ጀነራል ገብረጊዮርጊስ
  14. ብርጋዴል ጀነራል ህንፃ ወ/ገወርጊስ
  15. ኮሎኔል ተወልደ ገ/ትንሳይ
  16. ኮሎኔል ንጉሴ ገብሩ
  17. ኮሎኔል መብራቱ አሰፋ /አልማዝ/
  18. ኮሎኔል ዘገየ ንጉስ
  19. ኮሎኔል ያለም
  20. ኮሎኔል መብራቱ ተድላ
  21. ኮሎኔል ነጋሽ መብራቱ
  22. ኮሎኔል ተክሉ በላይ
  23. ኮሎኔል ጥጋቡ መለስ
  24. ኮሎኔል ግርማ ተካ
  25. ኮሎኔል ሙሉጌታ ገብረክርስቶስ ነጋሽ
  26. ኮሎኔል አራሞ ገ/መድህን
  27. ኮሎኔል ተስፋዬ ገ/መድህን
  28. ኮሎኔል ግርማል አለማየሁ
  29. ኮሎኔል ነጋሽ አለፎም
  30. ኮሎኔል ተስፋዬ ምሩፅ
  31. ኮሎኔል ካሳየ አሰፋ
  32. ኮሎኔል ነጋሲ ታደሰ ስዩም
  33. ኮሎኔል ኪሮስ ሓጎስ ገ/ዝጋብሔር
  34. ኮሎኔል ሙርፅ ገብረሊባኖስ አብርሃ
  35. ኮሎኔል ሓ/ስላሴ ኪሮስ ተስፋይ
  36. ኮሎኔል ምሩፅ በርሔ/ተወርወር/
  37. ኮሎኔል ሀይለስላሴ አሰፋ
  38. ኮሎኔል ደርበው ኃጎስ
  39. ኮሎኔል ወልዴ ሀጎስ
  40. ኮሎኔል ንጉሴ አማረ
  41. ኮሎኔል ነጋሲ ታደሰ
  42. ኮሎኔል ባራኪ /ወዲ ራያ/
  43. ኮሎኔል ከበደ ገ/ሚካኤል
  44. ኮሎኔል ፀጋ ብርሀን ገ/እዜር
  45. ኮሎኔል ዘሩ ሀ/መለኮት
  46. ኮሎኔል ሀይለ መዝገብ
  47. ኮሎኔል አርአያ ገብሩ ግደይ
  48. ኮሎኔል የማነ ገ/ሚካኤል
  49. ኮሎኔል ዘሩ መረሳ
  50. ኮሎኔል ልጃለም ገ/ህይወት
  51. ኮሎኔል አስመላሽ ወልዴ
  52. ኮሎኔል ፍሰሀ ግደይ
  53. ኮሎኔል አምባቸው ወ/ገብርኤል
  54. ኮሎኔል ገብረመስቀል ወልደገብርኤል
  55. ኮሎኔል ወልዱሀጎስ ገብሩ
  56. ኮሎኔል ገ/ሚካኤል ሀጎስ
  57. ኮሎኔል ስብሀቱ መብራቱ
  58. ኮሎኔል ጣሰው ወ/ጊዮርጊስ
  59. ኮሎኔል ገ/እግዚያብሔር አለምሰገድ
  60. ኮሎኔል ነጋሲ ታደሰ
  61. ኮሎኔል ተክለ በላይ
  62. ሌተናል ኮሎኔል ተወልደ አብርሃ ወ/ሚካኤል
  63. ሌተናል ኮሎኔል ሙዘይ ተሰማ ስዩም
  64. ሌተናል ኮሎኔል ሀዲሽ ገብረፃድቅ አለማየሁ
  65. ሌተናል ኮሎኔል ፍስሃ በየነ ገ/ኪዳን
  66. ሌተናል ኮሎኔል ምሩፅ ወ/አረጋይ ገ/መስቀል
  67. ሌተናል ኮሎኔል ሙሩፅ በርሀ ኣበራ
  68. ሌተናል ኮሎኔል ፀሀዬ ሀጎስ
  69. ሌተናል ኮሎኔል ሀጎስ ኪሮስ
  70. ሌተናል ኮሎኔል ገብረ ህንፃ ሀዲሽ
  71. ሌተናል ኮሎኔል ገብረመድህን ወ/ማርያም አሉላ
  72. ሌተናል ኮሎኔል ፈለቀ አይጠገብ
  73. ሻለቃ አስገዶም መስፍን
  74. ሻምበል ባሻ ሙእዝ መልካም
  75. ሻምበል አርአያ ተ/ኃይማኖት
  76. ሻምበል ተስፋ ህይወት ናቸው።

ስማቸው የተዘረዘረው ጄነራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች ከሀገር መከላከያ ሠራዊት እሴቶች መካከል ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም የሚለውን ወደ ጎን በመተው የወንበዴው ጁንታ ሕወሓት የጥፋት ቡድን የሴራ አካል በመሆን በወንጀል የሚፈለጉ መሆናቸውን ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በመግለጫው አሳውቋል፡፡

በመሆኑም መላው የሃገራችን ህዝቦች በተለይም ደግሞ የትግራይ ህዝብ፤ የክልሉ ልዩ ሀይል አባላትና ሚሊሻዎች እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሠራዊት፤ የአገራችን የፖሊስ ሠራዊትና የደህንነት ተቋማት እነዚህን የጁንታውን የሕወሓት የጥፋት ቡድን ተፈላጊዎች አድኖ ለህግ ለማቅረብ እየተደረገ ባለው ጥረት በያላችሁበት የድርሻችሁን እንድትወጡ ኮሚሽኑ ጥሪ እያቀረበ፤ በቀጣይም በጁንታው የሕወሓት የጥፋት ቡድን አገር የማተራመስና የማፍረስ ሴራ እንዲሁም በአገር ክህደት ወንጀል የተሳተፉትንና በየትኛውም የኃላፊነት ደረጃና መዋቅር ላይ ያሉ ተጠርጣሪዎችን ተከታትሎ በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የማድረግ ስራውም ሆነ በጉዳዩ ዙሪያ ተከታታይ መረጃዎችን በመገናኛ ብዙሃን በኩል ለህብረተሰቡ ይፋ የማድረግ ሂደቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን መግለፁን ኢብኮ ዘግቧል፡፡

 

EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events