Dehai

Globalresearch.ca: ህወሓት “ጭንቅላቱ ደርቋል” – ጠ/ሚ/ር ዐቢይ

Posted by: Berhane.Habtemariam59@web.de

Date: Thursday, 10 September 2020

ህወሓት “ጭንቅላቱ ደርቋል” – ጠ/ሚ/ር ዐቢይ

ህወሓት የተሰኘው የበረሃ ወንበዴዎች ስብስብ ላለፉት ሁለት ዐሥርተ ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ እስኪደነቁር ድረስ ሕገመንግሥት መናድ እያለ ተቃዋሚዎቹን ሁሉ ሲያሸማቅቅ እንዳልኖረ ዛሬ ያንኑ ሕገመንግሥት በመጻረር በትግራይ ሕገወጥ ምርጫ እያካሄደ ይገኛል።

ትላንት ማታ በETV በተላለፈው ቃለ ምልልስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በትግራይ የሚካሄደውን ሕገወጥ ምርጫ ከጨረቃ ቤት ሥራ ጋር እንደሚያመሳስሉት ገለጹ። ጠያቂው “በትግራይ ክልል የሚካሄደውን ክልላዊ ምርጫ እንዴት ይመለከቱታል?” ብሎ ለጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ላቀረበላቸው ጥያቄ “የትግራይን (የዛሬ) ምርጫ እንደ ጨረቃ ቤት ነው የምመለከተው፤ እዚያ ያለው ኃይል ጭንቅላቱ ደርቋል፤ ኪሱ ሲደርቅ ይጠፋል። እኛ የትግራይ ሕዝብን በልማት እንደግፋለን እንጂ ጦር አናዘምተበትም” ብለዋል።

“የትግራይ ምርጫ የጨረቃ ምርጫ ነው! ኮሽ ባለ ቁጥር ይደነግጣሉ! ሲኖትራክ ሲያልፍ ዶዘር መጣ ሊያፈርሰን ነው ብለው ይፈራሉ ሕጋዊ ምርጫ አይደለም።

“የሚሊሻ ብዛት አሳሳቢ አይደለም አሁን ትግራይ የሚያስፈልጋት ጦርነት ሳይሆን ውሃ ነው፣ የህወሓት የቁራ ጩኸት አሳሳቢ አይደለም፣ እኔ ለትግራይ የፊት ማስክ እንጂ ጥይት አልክም” ብለዋል።

ሲቀጥሉም “የጨረቃ ቤት ካርታ አንደሌለው ሁሉ ይሄም ምርጫ ሕጋዊ ያልሆነ ምርጫ ቦርድ የማያውቀው ነው”። … አገራዊው ምርጫ ሲካሂድ እዚያ ያለው ቡድን ካልተሳተፈ ፓርላማ መቀመጫ አይኖረውም። ለዚህ ብለን ጦርነት አንከፍተም። ለትግራይ ሕዝብ ኮሮናን አንዲከላከል አፍ መሸፈኛን እንሰጣለን አንጂ፣ ውሃን እናስገባለን፣ እድገትን እናመጣለን እንጂ የሆኑ ቡድኖችን ለመዋጋት ጦርነት አንከፍትም ። እዛ ያለው ሀይል ጭንቅላቱ ደርቋል። ኪሱ ሲደርቅ ይጠፋል። በድሮ በሞተ ሀሳብ የሚንቀሳቀስ ነው” ብለዋል።

ሙሉው ቃለ ምልልስ እዚህ ላይ ይገኛል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ


6ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 6 - ERi-TV Documentary

Dehai Events