Dehai

Goolgule.com: “ወያኔ የኦነግ ሠራዊትንና ደጋፊዎችን በጅብ ሲበሉ ታይ ነበር፣ ኦነግ የማፍያ ድርጅት ነው” የኦነግ አባል

Posted by: Berhane.Habtemariam59@web.de

Date: Tuesday, 08 September 2020

የህወሓትን ሆድ ዕቃ ቦርቡሮ የጨረሰው የውስጥ ትግሉ ነው። አሁን የመጣው ውዝግብ የሥልጣን ጥማት እንጂ ሌላ አለመሆኑንን ዶ/ር ጀማል መሀመድ ገምታ ተናገሩ። ልክ እንደ ሃጫሉ የሞት ማስፈራሪያ ደርሷቸው እንደነበርም ስም ጠቅሰው አስታወቁ። ኦህዴድን የከዱ አክቲቪስቶችን በመጋለብ ኦሮሚያ ላይ ቀውስ የሚፈጥረውን ጃዋርን ሆ ብሎ የሚከተለውን ሲያዩ እንደ ኦሮሞ ኃፍረት እንደሚሰማቸው አስታወቁ።

ባሌ ተወልደው፣ የህክምና ዲግሪያቸውን ካገኙ በኋላ ኦነግን ተቀላቅለው የነበሩት ሐኪም ጀማል ወደ ኦነግ በመሆናቸው ብቻ አስር ዓመታትን በእስር አሳልፈው ወደ ሎንዶን ተሰደዋል። በእስር ወቅት የደረሰባቸውን ስቃይ ለልጆቻቸውና ንጹህ ኅሊና ላላቸው ስለማይጠቅም ከመግለጽ እንደሚቆጠቡ አስታውቀው የተናገሩት ለኢሳት ነው። አሁን በኢትዮጵያም ሆነ በኦሮሚያ የተፈጠረው ችግር የሥልጣን ጥማት እንደሆነ ያብራሩት ዶክተሩ ዋና መነሻ ምክንያቱም ለውስጥ ትግል ዕውቅና ላለመስጠት መሆኑንን አመልክተዋል። 

ዶ/ር ዐቢይ ገና ወደ ሥልጣን ሲመጡ “አማራ ለቃቅመህ አባረርህ” መባላቸውን ገልጸዋል። ለውጡን ፊት ሆኖ በብስለት፣ በመመካከርና በመተባበር ለድል ያበቁትን የኦህዴድና የብአዴን አመራሮችን ለመለየት የተፈለገውም ከሥልጣን ጥማት መነሻ ብቻ እንደሆነ በዝርዝር መረጃ እያጣቀሱ ገልጸዋል። እነሱ ባይተባበሩ ኖሮ ለውጡ እንደማይታሰብም አስረደተዋል።

ደጋግመው የኅሊና ጽዳት የጎደለው ሲሉ የሚወቅሱትን የወቅቱን ፖለቲካ “እንደ ህክምና ባለሙያ የተጋገነ ነገር አልወደም” በማለት ስለቄሮ ትግል እውነት ያሉትን አብራርተዋል። “ቄሮ በትግሉ ውስጥ ሚና እንዳለው ባይካድም፣ ዛሬ በቀለና ጃዋር ቄሮ የሚሉት ቀደም ሲል ለሞተው ቄሮ ክብር ሳይሆን ገና ወደፊት ስልጣን እስክንይዝ ድረስ ሙትልን ለማለት ነው” በማለት ድርጊቱን እንደ ኦሮሞ እንደሚጠየፉት አስታውቀዋል። በትግሉ ውስጥ የኦሮ-ማራ ኅብረት ታላቅ ዋጋ እንዳለውም ጠቅሰዋል። ያም ሆኖ ግን ከ85% (ሰማኒያ አምስት በመቶ) በላይ ትግሉ ያለቀው በብልኃት በውስጥ ትግል መሆኑን እንደሚያውቁ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። ለዚህ አኩሪ ተግባር ዕውቅና መስጠት እንደማይፈለግም ምሳሌና ምልክት እየሰጡ ጠቁመዋል።

ጃዋር መጠነኛ አስተዋጾ ቢኖረውም እግሩ አገር ቤት ከገባ በኋላ ሁሉንም የድሉን ዝና ጠቅልሎ ለመውሰድ ፈለገና ጩኸት ተጀመረ ያሉት የቀድሞ የኦነግ አባል “ሲንገበገብ ሁሉንም አጣው” ሲሉ ሃዘናቸውን ገልጸዋል። አስራ ሶስት ዓመት እስር ተፈርዶባቸው አስር ዓመት ከታሰሩ በኋላ የተፈቱት ዶ/ር ጀማል “ጥቂት ጯሂዎች አብዛኛውን እያስፈራሩ ነው” ሲሉ ስለታፈኑ ድምጾችም ተናግረዋል።

“ኦ.ኤም.ኤን. የጃዋርና የጫጩቶቹ ወይም የአሉላ ድምጽ ነው፤ ጥቂቶች አብዛኞችን የሚያስፈራሩበት መሣሪያ ነው” ካሉ በኋላ ሚዲያው ለኦሮሞ ሕዝብ የሠራው ነገር እንደሌለ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ አስረድተዋል። በኦሮሞ ህዝብ መዋጮ፣ የኦሮሞ ህዝብ ላይ፣ ኦሮሞን የሚያፈርስ፣ የኦሮሞ መሪዎችን እያጣጣለ፣ ለወያኔ የሚሰራ ሚዲያ መሆኑንን አመልክተዋል። በዚሁ የጩኸት ሚዲያ ቀስቃሽነት “የጫት መቃሚያ፣ የጨብሲ የሚከፈላቸው” ቄሮ እየተባሉ ሌላውን እንዲያስፈራሩ ተደርጎ “መንግሥት” መሆናቸውን እስኪያውጁ መድረሳቸውንም አክለዋል። የዚህ ሁሉ ድራማ ባለቤት ጃዋር መሆኑንን በግልጽ አስቀመጠዋል። ንግግራቸው በመንግሥት ሚዲያ የአርሲ አባቶች ከተናገሩት ጋር የሚዛመድ ሆኗል።

በዲኤንኤ ኦሮሞም ሆነ አማራ የሆነ እንደሌለ እምነታቸውን ያሳዩት የህክምና ባለሙያ፣ በጃዋር ዙሪያ የተሰባሰቡት ኦህዴድ ለትምህርትና ለስራ ወደ ውጭ ልኳቸው የከዱ የኦህዴድ አባላትና በደርግ ዘመን ወንጀል የፈጸሙ ግፈኞች መሆናቸውን ጠቁመዋል። አያይዘውም ከዳተኞችና ወንጀለኞች ታዛዥ፣ የሚጋለቡ፣ ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ ልሁን የሚሉ የደረቀ ስብዕና የተላበሱ ሲሉ ስብስቡን የእምነት አጉዳዮች እንደሆነ ገልጸዋል። ከነዚህ ኃይሎች ውስጥ የወጣው አክቲቪዝም ኦሮሞ ደግ ነው በሚል ንግድ ውስጥ መግባቱንና ዛሬ የሚስተዋለው ሩጫና ሤራ ንግዱ ስለሚጣፍጥ ስልጣን ይዞ ለመዝረፍ እንጂ ለኦሮሞ ሕዝብ የተለየ ነገር ለማድረግ ታስቦ እንዳልሆነ አብራርተዋል።

ኦነግ አክራሪ እንዳልነበር ሲናገሩ ዲማ ነገዎ፣ ሌንጮ ለታና ገላሳ ዲልቦን አንስተዋል። እነሱን ገፍቶ ድርጅቱን የተቆጣጥረው የአንድ መንደር ወደ ነፍሰ ገዳይነት መቀየሩን አመልክተዋል። ሌላው ቀርቶ የተለየ ሃሳብ ያላቸውን ሳይመርጡ እንደሚያጠፉ አመልክተዋል። ሃጫሉ የተገደለው በመናገሩ መሆኑንን ያመለከቱት ዶ/ር ጀማል፣ እሳቸውም ማስፈራሪያ በስልካቸው እንደደረሳቸው አልሸሸጉም። ማስፈራሪያው ስልካቸው ላይ እንዳለ፣ ይህም የሆነው በመናገራቸው እንደሆነ ጠቁመው በርካታዎች መታፈናቸውን አስረደዋል። አቶ ሌንጮ ዛሬ ደንቢዶሎ የማይሄዱትም መንግሥት ከልክሏቸው ሳይሆን እነሱኑ ፈርተው መሆኑንን ገልጸዋል።

ሌንጮ ለታን በሃይማኖት፣ በአመላከትና በመንደር ዘመቻ አካሂደው እንደገፏቸው፣ ሌሎችም ላይ ተመሳሳይ ተግባር መፈጸሙን በማመልከት “ጃዋር ሲመጣ ግን አርሲ፣ ሙስሊም፣ …” ያልተባለው ብዙ የሚጮሁለት በማደራጀቱ፣ እነዚህ የሚጮሁ ጥቂቶች ደግሞ የሚከፈላቸው ስለሆኑ እንደሆነ ዶ/ሩ ያስረዳሉ። ከኢሳት ጋር ሰፊ ቃለ ምልልስ ያደረጉት ዶክተር ጀማል ኦነግ ዛሬ ስልጣን ቢይዝ ኦሮሚያን ገንጥሎ የሚመራበት ፕሮግራም፣ ድፍርትና ነባራዊ ሁኔታ እንደሌለ ሲገልጹ “ቱልቱላ ነው” በማለት ነው።

አስራ ሁለት ሺህ (12,000) የሚጠጉ የኦነግ ሰራዊት አባላት፣ እናቶች፣ ወጣቶችና ደጋፊዎች ሁርሶ ታስረው እንደነበር ያወሱት ሐኪም፣ እስረኞች በወደቀ ወታደር ብረት ቆብ (ሄልሜት) ገንፎ አገንፍተው ሲመገቡ ለኮሌራ መጋለጣቸውን አስታውሰዋል። እንደ ሃኪም ሰገራ በጃቸው በማጠብ እርዳታ ሲያደርጉ እንደነበር፣ ያም ሆኖ ግን ከ1,047 በላይ የሞቱ ወገኖችን መቁጠራቸውን ገልጸዋል። እስር ቤቱ የተደራጀ አመራር ስላልነበረው አንዳንዴ የሚመደቡ ተረኞች ህክምና እንዳይሰጡ ይከለክሏቸው እንደነበር አመልክተዋል። በቀላሉ ሊረዱ የሚችሉ ወገኖች አይናቸው እያየ በኮሌራ ማለቃቸው በእስር ዘመናቸው ልባቸው ከተነካበት ጉዳዮች መካከል የሚጠቀስ ነው።

ተቅማጥ ሲያዝቸው ለመጸዳዳት ወደ ውጭ ሲወጡ በርካታ የኦሮሞ ልጆችና ሰራዊት አባላት በቁማቸው በጅብ እንደተበሉ ዶ/ር ጀማል አጋልጠዋል። ይህንን ታሪክ ማንም እንደማያነሳውም አመልክተዋል። የሕክምና ባለሙያ በመሆናቸው በርካታ ለመናገር የማይፈቅዱትና ለአዕምሮ የማይመቹ ጉዳዮች በእስር ቆይታቸው ማሳለፋቸውን አንስተዋል።

“በ30 ዓመት ያየሁት መጥፎ ባህል ውጤታማ ከሆንክ ትጠላለህ። ከተዳፈርክና አሸንፈህ ከወጣህ ይነሱብሃል” በማለት አጠቃላይ ዛሬ ላይ ያለም ችግር ሲገልጹ እስር ቤት ወያኔዎች ሰው በመርፌ ገድሏል ብለው እንደወነጀሏቸው በማስታወስ ነው። ይህ ስሜት ካለመቻል፤ ከዕውቀት ማነስና ከቅናት የሚመነጭ መሆኑንን አመላክተዋል። በተለይም የኦሮሚያ ፖለቲካ የቅናት ውጤት እንደሆነ አጥበቀው ተናግረዋል።

ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ተቧድነው በመንጋ አመላከከት አፈና እንደሚያካሂዱ፣ አፈናው አብዛኞችን አንቆ እንደያዘና ይህ የጥቂቶች ጩኸት የአክራሪነትና የተቆርቋሪነት ተደርጎ የሚወሰደው ፍጹም አግባብ እንዳልሆነ ዶክትሩ ሞግተዋል። ሲያስረዱም “አክራሪ አይዶሎጂ አለው። አይዶሎጂውን ይጠብቃል። ሌት ተቀን ላመነበት መርህ ይሰራል።  ለፕሪንሲፕል ይሞታል” ካሉ በኋላ አሁን የሚታየው ግን ሌላ መሆኑንን፣ እሱም የፖለቲካ ቁማርና በጩኸት ሌሎችን አስፈራርቶ የማፈን አካሄድ እንደሆነ አስምረው አልፈዋል። “ውሸታሞች” ሲሉ ዘልፈዋቸዋል።

ምንም እንኳ ተመሳሳይ ድርጅት ውስጥ ቢኖሩም ሳይከዳ ባመነበት መንገድ ቆይቶ ወያኔንን ሰርስሮ ለጣለው ኦህዴድ ምስጋና እንደሚያሻው ያስታወቁት ዶክተር ጀማል፣ “… አፈጣጠሩ መጥፎ ቢሆንም ፣ ልጅ ሆኖ ገብቶ በጥበብ፣ በሂደት፣ ለውጥ አመጡ ጀግኖች ናቸው” ካሉ በኋላ አባል ሆነው በጦር ሜዳ ሳይቀር ያገለገሉትን ድርጅታቸውን “ኦነግ አፈጣጠሩ መልካም ነበር ቆይቶ ፌክ ሆነ፤ ገዳይ ሆነ” ገልጸውታል።

የቃለምልልሱ ቪዲዮ እዚህ ላይ ይገኛል

https://www.youtube.com/watch?v=_37CuOc-jDQ&feature=youtu.be

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

 

6ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 6 - ERi-TV Documentary

Dehai Events