Date: Thursday, 18 July 2019
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው አስመራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት ከኤርትራ መንግስት ጋር የሁለቱን አገራት ጥቅም ያማከለ ሁሉን አቀፍ ትብብር ላይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡
ከ በኩል የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንድ አመት ውስጥ ከ 130 ሺህ በላይ መንገደኞችን ከአዲስ አበባ ወደ አስመራና ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ ማጓጓዙን አስታውቋል ፡፡
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ለሁለት አስርት አመታት ተቋርጦ የነበረውን ግንኙነታቸውን በመመለስ ሰላማዊ ግንኙነት በጀመሩበት ማግስት የተከፈተው የሁለቱ ሀገሮች የአየር ጉዞ የዛሬ አመት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ ባደረገው ጉዞ መጀመሩ ይታወሳል ፡፡ ፡፡
በዚህም ለአመታት ተራርቀው የነበሩ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶችን በቀን ሁለት ጊዜ በረራ በማድረግ ማገናኘት መቻሉንም ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡