Dehai News

(ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ዛላምበሳ ገብተዋል

Posted by: Semere Asmelash

Date: Tuesday, 11 September 2018

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ዛላምበሳ ገብተዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2018 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አዲስ ዓመትን ለማክበር ዛላምበሳ ተገኝተዋል፡፡

መሪዎቹ ዛላምበሳ ሲደርሱ በሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡




በስነሰርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮነን፣ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካዔል እና ሌሎች የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡

በስነስርዓቱ ላይ የሁለቱ ሀገራት ብሄራዊ መዝሙር ከተሰማ በኋላ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ንግግር አድርገዋል፡፡

ዶክተር ደብረጽዮን ለሁለቱ ህዝቦች ለዚህ ቀን ስላደረሳችሁ እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

መሪዎች ማለዳ ላይ በቡሬ ግንባር ተገኝተው ከሁለቱ ሀገራት ወታደሮች ጋር አዲስ ዓመትን አክብረዋል፡፡

እንዲሁም መሪዎቹ የቡሬ – ድባይ ሲማ ድንበርን ከሰዓታት በፊት ከፍተዋል፡፡

በአብርሃም ፈቀደ

ዛላምበሳ




ቡሬ




EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events