Date: Sunday, 19 January 2020
ባሕር ዳር (አብመድ) በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር የተመራ ልዑኩ ጎንደር አፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ማስተዋል ስዩም (ኢንጂነር) እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
ከኤርትራ ተጨማሪ ልዑካን ወደ ጎንደር እንደሚገቡም እየተጠበቀ ነው፡፡
የውጭ ሀገራት እና የሀገር ውስጥ እንግዶችም ወደ ከተማዋ የገቡ ነው፡፡
እንግዶችን ለመቀበል ደግሞ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና ፋሲል ከነማን ጨምሮ የከተማዋ ባለሀብቶችና ተቋማት ለመጓጓዣ አገልግሎት መኪኖችን በማቅረብ ላይ ናቸው።