World News

(ኢቲቪ) በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተጀመረውን ግንኙነት ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል የትብብር ፍኖተ ካርታ ተዘጋጀ

Posted by: Semere Asmelash

Date: Tuesday, 29 January 2019

AFRICA

በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተጀመረውን ግንኙነት ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል የትብብር ፍኖተ ካርታ ተዘጋጀ

 
 
በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተጀመረውን ግንኙነት ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል የትብብር ፍኖተ ካርታ ተዘጋጀ

በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተጀመረውን ግንኙነት በተቋማዊ አሰራር ለመደገፍ የሚያስችል የትብብር ፍኖተ ካርታ ተለይቶ መዘጋጀቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ፍኖተ ካርታው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰብሳቢነት በገንዘብና ኢኮኖሚ እና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት ትብብር ተለይቶ መዘጋጀቱ ተነግሯል።

በፍኖተ ካርታው መሰረትም በሁለቱ ሃገራት መካከል የሚኖረው የድንበር ንግድ፣የወደብ አጠቃቀም ፣ የጉምሩክ ፣የኢምግሬሽንና የትራንስፖርት ትብብሮች የሚመሩበት ህጋዊ ማዕቀፍ ለመፍጠር ረቂቅ የስምምነት ህጎች ዝግጅት ተጠናቆ ለኤርትራ ወገኖች ደርሶ ውይይት ተደርጎበታል።

በቀጣይ በሁለቱ ወገኖች አጠቃላይ የሁለትዮሽ ትብብር እና የጋራ ኮሚሽን መቋቋሚያ ስምምነት እንደሚፈረምም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የሚኒስቴሩ የ2019 ዓ/ም የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየተገመገመ ነው።
(Source: ኢቲቪ)

EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events