World News

Mereja.com: ጦርነት ላይ ያለች የምትመስለው ትግራይ፣ በተለይም መቀሌ ከተማ፣ የመቀሌ ሪፖርታዥ

Posted by: Berhane.Habtemariam59@web.de

Date: Wednesday, 02 January 2019

መቀሌ በውድቀት ዋዜማ ላይ ....... !

የትግራይ ሕዝብና የዘራፊና ነፍሰ ገዳዩዋ ህውሃት ወቅታዊ ሁኔታ!!


የጉዞ ማስታወሻ ሪፓርት!!!

"መቀሌ ሀገር ሆናለች በውድቀት ዋዜማ ላይም ትገኛለች

========================
ሰሞኑን በትግራይ ክልል ከአላማጣ መቀሌ፣ አዲግራት፣ አድዋ፣ አክሱም፣ ሽሬ እንደስላሴን አልፌ ተከዘኔን አቋርጨ በሊማሊሞ አማራ ክልል እስግገባ በነበረኝ ቆይታ የታዘብኩትን በአራት እይታ ከፍየ ላቅርብ (በፖለቲካ፣በኢኮኖሚና በሚዲያ፣በሕዝቡ ሁኔታ).....
January 2, 2019

1. በፖለቲካ_እይታ .....
=============
ገና ወደ መቀሌ ስትገባ አስጨናቂ ፍተሻ ይጠብቅሀል፡፡ የማትጠየቀው ፓስፖርት ብቻ ነው፡፡ አዲስ ሰው ከሆንክ የት ነው የመጣኸው?፣ ለምን ሥራ ነው የመጣኸው? እስኪ መታወቂያ ..... በቃ ምን አለፋችሁ የሀገራችን ክልል ሳይሆን ሌላ አዲስ ሀገር የምንገባ ነው የሚመስለው። ወደ ሰማዕታት ሀውልት ዝቅ ብሎ የሚገኘው "ዋን ፕላኔት" ሆቴል የህወሃት ታዳኝ አውሬዎች ገዳማቸው አድርገው የሚዶሉቱበት ስፍራ በመሆኑ ሲቪልና ሚሊቴሪ በለበሱ ጠባቂዎች ታጥሯል።

በዚያ ስታልፍ ግልምጫውና ክትትሉ የጉድ ነው...... እኔ እስር ላይ እንዳሉ ያህል ነው የተሰማኝ። እስር ማለት የሚጀምረው ከአስተሳሰብ እና ሰው በነፃነት መንቀሳቀስ አለመቻሉ በመሆኑ የመቀሌ ነዋሪ በእጅጉ ሽብርና ጭንቀት ውስጥ ነው ያለው። በመቀሌ ያሉ የህወሃት ካድሬዎች ኢትዮጵያ እየፈረሰች ትግራይ ብቻ ሰላም ሆኗ ያለች መሆኑን እርግጠኛ ሁነው ያወሩልሀል። ይህ ብቻ በቂ ነው ሌላ ቦታ አተራማሿ ህወሃት ስለመሆኗ፡፡ ምንድነው ከተማው ድባቡ ብለህ ...?! ከጠየክ ትግሬና አማራ ተጣልተው ይሉሀል።

ልብ አድርጉ..! አሁንም ህዝብ ለህዝብ ጦርነት ፈጥረው ህወሃት ነፃ ልትሆን የዘየደችውን ዘዴ የህወሃት ታማኝ ካድሬዎች በየቀበሌው ዘመቻ ወርደው ግልፅ ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛሉ። "ንቁ አማራ ዳግመኛ ሊጮቅናችሁ፣ መሬታችሁን ሊወስድ ነው። ስለ እናንተ ከህወሃት ውጭ ማንም ሊሆናችው አይችልም" በማለት ከፍተኛ የወንጀል ሥራ ሕዝብ ለሕዝብ ለማጋጨት ሴራ ተጠምደዋል።

መቀሌ በህወሃት ጭፍራ ፖለቲከኞች ሽብር እየተነዛባት፣ በተዘረፈ ብር እየጠጡ በቃ ስድብ ነው የምትሰማው።

ዶር አብይ እዚያ ስሙ "ደንቆሮ መሪ" የሚል ነው። ልብ አድርጉ ምዕራባውያን ሳይቀሩ ፀሀይ በምዕራብ የመውጣት ያክል ነው ያመጣው ለውጥ ያሉለትን መሪ አንድ እንከፍ የህወሃት ካድሬ የራያና ጊዮርጊስ ቢራ ይዞ አፉን ይከፍታል።

በጣም የገረመኝ ይህ በተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የማንነትና ወሰን ማስከበር አጥኝ ቡድን ሥራ ጀምራለው ቢል "ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር በቃ ትፈርሳለች ማለት ነው።" እየተባባሉ የአቋም መግለጫ የህወሃት ጭፍሮች በየ መጠጥ ቤቱ ሲዝቱ መስማት የተለመደ ነው። እንኳን ለኢትዮጵያ ቀርቶ ከኤርትራ ጦር መንጋጋ ያወጣቸው የኢትዮጵያ ወጣት መሆኑን ዘንግተውታል።

በጣም የሚገርመው ... ገና ከመቀሌ ከተማ ወጥተህ ወደ ሽሬ ስትገባ ህዝቡ የሚነግርህ ከመቀሌው የተለየ ነው፡፡ ከመቀሌ ከተማ ውጭ ያለው የትግራይ ህዝብ ምን ሌቦች ሀገር ዘርፈው መቀሌ መተው ተደብቀው ህዝቡን ያሰድባሉ... እነዚህ ውሾች ይሉሀል። እውነትም የሀየሎም አርአያ ልጆች ....... ከህወሃት ውጭ መንግስት የለም አይኖርም የሚለው ደግሞ ሲሞግትና በዚህ ደንቆሮ መሪስ አንመራም በማለት የህወሃትን ጨው እየላሰ የሚያላዝን ጋለሞታ ታያለህ።

መቀሌን ለቀህ ሽሬ ስትገባ ፍተሻውና ትርምሱና ውክብያው ግን መቀሌ ላይ ያበቃል። ወጣ ስትል ሕዝቡ በፀጥታ ሲወጣ ሲገባ ስታይ ያስቅሀል። መቀሌ ላይ በየ ቅያሱ ትፈተሻለህ፣ በየሰአቱ ፈንጅ ተያዘ እየተባለ ህዝቡን እያሸበሩት፣ በቃ መቀሌ የፖለቲካና የጦርነት ከተማ መስላለች። ህወሃት ለራሷ ነገ ትታሰር፣ ከነገ በስትያ ተምቦቅቡቃ ሕዝቡን እያሸበረች ነው። ቱ......ቱ....... እንዲህስ ሆነው ከሚኖሩ ለምነው ቢታሰሩ ይቀላቸው ነበር።.... ሽንታሞች ወንድ ሁላ አይመስሉህም። ብቻ ምን አለፋችሁ የትግራይ ህዝብ በተለይ መቀሌ በወሮበላ ባልተማሩ ሆድ አደር ፖለቲከኞች ውጥረት ውስጥ ትገኛለች።

2. በኢኮኖሚ .....
===========
እንደሚታወቀው ልክ እንደ እሩስያ መቀሌ ገዝቶ ከሚበሉት እንጅ አምርቶ ከሚሸጡት ተርታ አትሰለፍም የወልድያ፣ ጎንደር መንገድ በመዘጋቱና ዞሮ በአፋር በኩል በመግባት በመቻሉ ባይታጣም በውድም ቢሆን ታገኛለህ። ሽሮ ከ40 እስከ 50 ብር በጣም ዝቅተኛ የተባለ ቤት በልተህ ትከፍላለህ። 1 ቢራ 17 ብር ጀምሮ 1 ሊትር ውሃ 14 ብር ትከፍላለህ።

በተቃራኒው ተከዜን እልፍ ብለህ አማራ ክልል ስትገባ ሽሮ 25 ብር ብቻ ትከፍላለህ። ቢራ በ13 ብር 1 ሊትር ውሃም በ10 ብር ትገዛለህ፡፡ ግን ይህ ለምን ሆነ ብለህ መቀሌዎችን ስትጠይቅ "ያ ደንቆሮ መሪ" ወደ ኤርትራ እንዲጫን ፈቅዶ ነዋ ይሉሀል። የቢራ ማከፋፈያዎች ግን ዋጋ አለመጨመራቸው እየታወቀ ህወሃት መሀል አገር ላይ ስታደርግ እንደነበረው ህዝቡን በኑሮ ውድነት እያስመረሩትና ለውጡ ያናጋው ለማስመሰል የዘየዱት መሆኑን ትገነዘባለህ።

መቀሌ ላይ ባሉት የንግድ ቤቶች በVAT ደረስኝ የሚገበያይ የለም። የትኛውም ሆቴል በልተህ ጠጥተህ ስትከፍል ያለ VAT ደረሰኝ ነው። ምነው እነ ህገ መንግስት፣ ህግ ይከበር ምናምን ይህን የሀገር እድገት ግብር የዜግነት ግዴታ መሆኑን ዘነጉትሳ ገቢዎች ሆይ ከወዴት አለህ?!

መቀሌ ከተማ ከሮማናት አደባባይ ቁልቁል ወርደህ ወደ ቀኝ ታጥፈህ ቀጥታ ስትሄድ የማይጨው ጫት ተዘጋጅቶ አንዱ እስር በ200 ብር ሂሳብ አንድ ሚኒባስ ላይ ከውስጡና ከላይ 200 እስር ጭና 40 ሺህ ብር ድረስ ከፍለው ወደ አስመራ ይጭናሉ።

በል እንግዲህ ወዲ አፎም ንቃ ህዝብን ሳያደንዙት በሱስ የመቀሌ ንግድ_እንቅስቃሴ በእጅጉ ተዳክሟል እኛ ያረፍንበት ሆቴል ወደ 30 መኝታ ኖሮት በቀን ብዙ ካከራየ 5 ወይም 6 መኝታ ብቻ ነው። ባለቤቱ ምሬታቸውን ሲገልፁ ሌቦች ሰርቀው መጥተው በተደበቁት እኛ እንቸገራለን አሉን።

ወዳጄ ድሮ በህወሃት አስገዳጅነት ለ1 ቀን ስብሰባ ሀገር አቋርጠህ እዚያ መቀሌ መጥተህ እንድትሰበስብና ብርህን እንድታፈስ ትገደድ ነበር። አሁን ወፍ የለም በደህናው ግዜ ምግብ ለስራ በማለት በትንሽ ስራ ብዙ እየከፈሉ ህዝቡን አስተኝተው በመቀለብ ድህነትንና ልመናን እንዲለማመድ ህወሃት አድርጋ አልፎ አልፎ ትንሽ የሙከራ መሳይ ሰብል እርሻ ላይ ልታይ ትችላለህ ይህ ደግሞ ኢኮኖሚውን በእጅጉ ይጎዳዋል።

የመቀሌ የንግድ ጡዘት የዋጋ ንረት ሆን ተብሎ የተደረገ መሆኑን ሳይ ለካ ህዝቡ መልሶ መልሶ ሰልፍ ሰልፍ የሚለው ይህ ጡዘት አማሮት እንደሆነ መገመት አያዳግትም።

3. ሚዲያ .....
=======
በትግራይ ክልል መቀመጫቸውን መቀሌ ያደረጉ ወደ 4 የሚደርሱ የቴሌቪዥን ጣቢያዋች አሉ። ሥራቸው ህዝብን ለአመፅ መቀስቀስ፣ የጦርነት ሙዚቃ መክፈት ፀረ-አብይ፣ ፀረ -ለውጥ አስተሳሰቦችን ማስተናገድ ...በቃ ግልፅ ስድብ አስቡት ምን ያህል ወጭ ለእነዚህ ሚዲያዎች ክልሉ ከመንግስት ካዝና እየከፈለ ጋዜጠኛ አይሏቸው መሀይሞችን ቀጥሮ ብር ያፈሳል።

ለፕሮፖጋንዳ ህዝቡ ድግሞ በሌላ መልኩ ሲቸገር ስታይ ያስቅሀል። ኢሳትን፣ ኢቲቪን መክፈት እንደ ነውር የሚቆጥርበት ነው። አልፎ አልፎ ህወሃት ጠል የሆኑና የነሱ ፕሮፖጋንዳ የሰለቸው ኢቲቪን ከፍተው ይሰማሉ።

በመጨረሻም ዶር አብይ የትግራይን ህዝብ ከእነዚህ መሰሪዎች ነፃ አውጣቸው። እኛ ያየነውን ነፃነት አሳያቸው ህዝቡን አደናግረውታል። መጥፎ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ ሳይከቱት ዶር ልትደርስላቸው ይገባል። ሰፊው ሕዝብ በጥቂት ሆዳም መሀይሞች ተጋርዷል። መጋረጃውን ቅደድላቸው።
ለትግራይ ፀልዩላት!!!

ዘጋቢያችን ዩሀንስ በቀለ ነው እናመሰግናለን፡፡

EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events