World News

Goolgule.com: ከቅዳሜው የህወሓት ሰልፍ በፊት በትግራይ “ከዓቅም በታች የሰረቁ” ተፈረደባቸው

Posted by: Berhane.Habtemariam59@web.de

Date: Friday, 07 December 2018

 

ቅዳሜ በህወሓት አስገዳጅነትና ተለማማጭነት አሁን በመላው ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ለውጥ የመቃወም እንደምታ ያለው ሰልፍ ተጠርቷል። እስካሁን ድረስ በርካታ መረን የወጣ ሌብነት የፈጸሙ፣ እጅግ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብቶችን የጣሱና ሌሎች ተፈላጊ ወንጀለኞችን በትግራይ ደብቆ የያዘው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) በኤፈርት አልባሽነት ቅዳሜ “ሰላማዊ” ያለውን ሰልፍ በመቀሌ፣ ትግራይ ጠርቷል። ሌብነትን እንቃወማለን ለማለትም በአንዳንዶች ዘንድ “ከዓቅም በታች የሰረቁ” የተባሉ አነስተኛና ጥቃቅን ሌቦች ላይ ፍርድ አስተላልፏል።

የመቀሌ ከተማ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ዘመንፈስቅዱስ ፍሰሃን ጠቅሶ ኢዜአ እንደዘገበው የሰልፉ አንዱ ዓላማ “ህገመንግሥቱ ይከበር” የሚል ነው ብሏል። ይህ በህወሓት አነጋገር ከአንቀጽ 39 ጀምሮ በርካታ ነገሮችን ሊያስብል የሚችል አገላለጽ፤ ህወሓት ከሁለት ዐሥርተ ዓመታት በላይ ሳያከብረው የኖረውን ህገመንግሥት አሁን ግምባር ቀደም የመታገያ መሣሪያ ማድረጉ አስቀድሞ ለራሱ የሠራው ሥራ እንዳለ አመላካች ነው።

ከዚህ ሌላ በሰልፉ ላይ “የትግራይን ህዝብ ለማምበርከክ የሚደረጉ ሴራዎች ተቀባይነት” የላቸውም፤ “በማንነት ጥያቄና በአዋሳኝ አካባቢዎች ምክንያት በማድረግ የክልሉን ህዝብ የሚነኩ ትንኮሳዎች” አንቀበልም፤ የውጭ ጣልቃ-ገብነትና የውስጥ ሤራዎች እንዲቆሙ እንጠይቃለን፤ ወዘተ የሚሉ መልዕክቶች በሰልፉ እንደሚተላለፉ ዘመንፈስቅዱስ አመላክተዋል።

ይህ አስቀድሞ ምን ያህል ሕዝብ እንደሚወጣበት፣ ምን ዓይነት መፈክር እንደሚፈከርበት ተጠናቆና ተዘጋጅቶ የተጠራ ሰልፍ፤ የትግራይ ሕዝብን በየትኛውም መልኩ እንደማይደግፍ አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች ይናገራሉ። ሆኖም በዚህ በ“ባሎኒ” ስታዲየም የተጠራውን ሰልፍ ሕዝባዊ ቁመና ለማላበስ ህወሓት የተለያዩ የሚዲያ ተወካዮችን በክልሉ መስተዳድር ስም በክብር በደብዳቤ ጋብዟል። ምን ያህሉ እንደሚገኙ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት ውስጥ በአሸባሪነት እስካሁን ተመዝግቦ የሚገኘው ህወሓት፤የወንበዴው ቡድን አምበል የነበረውን የመለስ (ለገሰ) ዜናዊ ፎቶ ያለበትን ቲሸርት መቀሌ ላይ ሕዝቡን አስለብሶ ሐሙስ ዕለት የድጋፍ ሰልፍ አስወጥቷል። በመላው ኢትዮጵያ የሚገኘው ሕዝብ የመለስን ፎቶ ላለማየት ካለበት ቦታ ሁሉ አውርዶ አገሩን በተረከበበት ጊዜ (ከፓርላማም በዚህ ዓመት የመለስ ፎቶ ተወግዷል)፤ ህወሓት የማሌሊትን ጨርቅ በግድ አስለብሶ ሕዝቡ እንዲታይ አድርጓል።

በሌላ በኩል የሌባና የወንጀለኛ ተባባሪ ደባቂ በመሆን ሰሞኑን በተለያዩ ሁኔታዎች ስሙ ሲወቀስ የነበረው ህወሓት፤ በትግራይ 63 ግለሰቦችን በእስርና በገንዘብ ቀጥቻለሁ ብሏል። አሃዱ ሬዲዮ እንደዘገበው ከሆነ “የክልሉ የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ የህዝብና የመንግስት ሀብትን በመዝረፍና ፍትህን በማዛባት ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል የተባሉ 63 ግለሰቦች በእስርና በገንዘብ እንዲቀጡ ማድረጉን አስታወቋል። በግለሰቦቹ ተዘርፎ የቆየ 8 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብና ከአንድ ሺህ ካሬ ሜትር በላይ የከተማ መሬት ወደ መንግስት ካዝና እንዲመለስ፤ ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ 52 ግለሰቦች ከ6 እስከ 8 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት፤ 11ዱ ደግሞ ከ9 እስከ 16 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ እንደተላለፈባቸው” ሬዲዮው ኮሚሽነሩን በመጥቀስ ዘግቧል።

ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ እንደሚሉት በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ እየተቃወመ ያለው ህወሓት፤ አሁን ደግሞ ሌቦችንና በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን ሸሽጎ ስለሚገኝ ለዚህ ማጣፊ እንዲሆን ያደረገው ነው ይላሉ። ሁኔታው ያልጣማቸውና ከዚህ በላይ በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ሌብነትና ወንጀል የፈጸሙትን የህወሓት ሰዎች አሳልፎ ከመስጠት ልቅ እነዚህን “ከዓቅም በታች የሰረቁ” ግለሰቦችን በመቅጣት ራሱን ከተጠያቂነት ለማስመለጥ የሚያደርገው ከንቱ ልፋት ነው በማለት አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።

ከበረሃ ጀምሮ በውንብድና ተግባሩ በዓለምአቀፍ ደረጃ የሚታወቀው ህወሓት፤ ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም የግል ንብረቱ አድርጎ ሲበዘብዝና የፈለገውን ግፍ ሲፈጽም የቆየበት ጊዜ እያከተመ ሲመጣ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ብጥብጥ በማስነሳትና ስፖንሰር በማድረግ ዓላማውን ለማስፈጸም ሲጥር እንደነበር ይነገራል። በተለይ በሶማሊ ክልል ሤራው ከከሸፈ በኋላ በጋምቤላም በተመሳሳይ ሁኔታ አመራሮቹ ተነስተው ለውጥ በክልሎቹ ሥር እየያዘ ነው። በቀጣይነት ደግሞ ዋና ምሽጉ አድርጎ ሲንቀሳቀስበት የነበረው የአፋር ክልል በአሁኑ ጊዜ በለውጥ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኝ ሲሆን ቤንሻንጉልም በዚያው መስመር ላይ ይገኛል። ይህ ሲጠናቀቅ ህወሓት በግፍ አፍኖ በያዘው የትግራይ ሕዝብ መተፋቱ እንደማይቀር ብዙዎች የሚስማሙበት ነው።


7ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 7 - ERi-TV Documentary

Dehai Events