World News

Goolgule.com: “ኦሮሞ የሞተላትን አገር ጥሎ ወዴትም አይገነጠልም! ኦሮሞ ከኢትዮጵያ ውጭ አገር የለውም! አይኖረውም!” ዐቢይ አሕመድ ኦሮሞ አገር መምራት ብቻ ሳይሆን አገር መገንባት ይችላል

Posted by: Berhane.Habtemariam59@web.de

Date: Saturday, 22 September 2018

ህወሓት የሰየመለትን ስም፣ ዓርማና መዝሙር በማስወገድ ራሱን ነጻ ያወጣው የቀድሞው ኦህዴድ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) የሚል ስያሜ በመውሰድ አዲስ ፓርቲ ሆኗል፤ የሚከተሉትን የኦዴፓ/ኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በማድረግ መርጧል 1. ዶክተር አብይ አህመድ፤ 2. አቶ ለማ መገርሳ፤ 3. ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፤ 4. አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ፤ 5. ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፤ 6. አቶ አዲሱ አረጋ፤ 7. አቶ ሽመልስ አብዲሳ፤ 8. አቶ ፍቃዱ ተሰማ፤ 9. ዶክተር ዓለሙ ስሜ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚከተሉትን 55 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትን መርጧል፤ እስካሁን ይፋ በሆነው የምርጫ ውጤት መሰረትም፦

    1. ዶክተር አብይ አህመድ
    2. አቶ ለማ መገርሳ
    3. ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ
    4. አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ
    5. ወይዘሮ አዳነች አቤቤ
    6. ኢንጂነር ታከለ ኡማ
    7. አቶ ሽመልስ አብዲሳ
    8. አቶ ኡመር ሁሴን
    9. ወይዘሮ ጠይባ ሀሰን
    10. አቶ አዲሱ አረጋ
    11. ዶክተር ግርማ አመንቴ
    12. ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ
    13. ዶክተር ሚልኬሳ ሚደጋ
    14. አቶ ተሾመ አዱኛ
    15. አቶ ታዬ ደንደአ
    16. ዶክተር አለሙ ስሜ
    17. ዶክተር ቶላ በሪሶ
    18. አቶ ደመላሽ ገብረሚካኤል
    19. አቶ ግርማ ሀይሉ
    20. አቶ ወርቁ ጋቸና
    21. አቶ ሻፊ ሁሴን
    22. አቶ ቶሎሳ ገደፋ
    23. አቶ ፍቃዱ ተሰማ
    24. አቶ ብርሃኑ በቀለ
    25. አቶ አወሉ አብዲ
    26. አቶ ጌቱ ወዬሳ
    27. አቶ ካሳሁን ጎፌ
    28. አቶ መላኩ ፈንታ
    29. አቶ ታረቀኝ ገለታ
    30. አቶ አበራ ወርቁ
    31. አቶ መኩዬ መሃመድ
    32. አቶ አህመድ ቱሳ
    33. አቶ አሰግድ ጌታቸው
    34. አቶ ደንጌ ብሩ
    35. አቶ ነመራ ቡሊ
    36. አቶ አብዱልአዚዝ መሃመድ
    37. አቶ ሮባ ቱርጬ
    38. አቶ ጀማል ከድር
    39. አቶ መሃመድ ከማል
    40. አቶ ከፍያለው ተፈራ
    41. አቶ መስፍን አሰፋ
    42. ወይዘሪት ሌሊሴ ነሜ
    43. አቶ ናስር ሁሴን
    44. አቶ ሞገስ ኢደኤ
    45. ዶክተር ደረጄ ዱጉማ
    46. ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ
    47. ወይዘሮ ሎሚ በዶ
    48. ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ
    49. ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ
    50. አቶ ማሾ ኦላና
    51. ወይዘሮ አለምፀሀይ ሽፈራ
    52. አቶ አህመድ እድሪስ
    53. ወይዘሮ ሙና አህመድ እና
    54. አቶ ጥላሁን ፍቃዱ
    55. አቶ አብዱላኪም ሙሉ

ረቡዕ መስከረም 9፤2011ዓም በተጀመረው የኦዴፓ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢ የሆነ መልዕክት አስተላልፈው ነበር። የመልዕክታቸው ፍሬ ነገሮች ከዚህ በታች ሰፍረዋል። መረጃውን ከተለያየ የፌስቡክና የማኅበራዊ ሚዲያ በቅብብል ያገኘነው ነው።

  • “እሳት ውስጥ ቆመን፣ ስድቡን ሁሉ ችለን፣ ትግሉን ከዳር አድርሰነዋል። ኦሮሞ ከለቅሶ መውጣት አለበት። … ይህ አገር ያለ ኦሮሞ አገር መሆን አይችልም። ለኦሮሞ ኢትዮጵያ ብቻ ትጠበዋለች። አፍሪካንም መገንባት ይችላል ብለን ተነሥተናል። … ረጅም መንገድ እንድንሄድ ከፈለጋችሁ ይቺን አገር የመገንባት ኃለፊነት እንዳለብን እንወቅ። … አድዋ ላይ ማን ነው ያሸነፈው? … ይህንን አገር ለማን ትተን ነው የምንመለሰው? አንመለስም”
  • “ኢትዮጵያን እንገነባለን፣ አፍሪካን እንገነባለን፣ ማንም ኃይል ደግሞ ከዚህ ሊያቆመን አይችልም”
  • “ኦሮሞ ማቀፍን፣ ጉዲፈቻን እናት የሌላቸውን ልጆች ማሳደግን ነው ያስተማረን፣ ኦሮሞ ከተዋጋ ያሸንፋል እንጂ ሰውን መግደልን አላስተማረንም”
  • “የዚህ አገር አንድነት ለማስጠበቅ ኦሮሞ ኃላፊነት አለበት … ኢትዮጵያ ከጠላት ጋር ባደረገችው ጦርነቶች ውስጥ ኦሮሞ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል … አባጅፋር ለኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም ጭምር አርቀው የሚያስቡ ነበሩ … አሁን ባለንበት ዘመን በትናንትናው ስልት ማሸነፍ አይቻልም”
  • “ኦሮሞ አገር መምራት አይችልም የሚሉን አሉ፤ ኦሮሞ አገር መምራት ብቻ ሳይሆን አገር መገንባት ይችላል፤ ኦሮሞ ገዳን ለዓለም እንደ ሰጠ ሁሉ፣ ኦሮሞ በቅርቡ አዲስ ፍልስፍና ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ሰጥቶ ሊያሳያቸው ይፈልጋል።
  • “ከዚህ በኋላ በኦሮሞ ህዝብ ስም መነገድ የለም። ኦሮሞ የሞተላትን አገር ጥሎ ወዴትም አይገነጠልም። ኦሮሞ ከኢትዮጵያ ውጭ አገር የለውም፤ አይኖረውም። ኢትዮጵያ ብዙ አባቶቻችን ከአድዋ ጀምሮ ዋጋ የከፈሉባት አገራችን ነች። አንዳንዶች ጠዋት ስለ አንድነት ስለ አብሮነት እያወሩ ማታ አገር ስለማፍረስ ይዶልታሉ። መደመር እንደዚህ አይደለም። የኦሮሞ ህዝብ ወላዋዮችን ይጠየፋል። የምትበተን ኢትዮጵያ የለችም”

ስብሰባው ዛሬ ሲጠናቀቅ ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

(የተመራጮቹ ስምና አንዳንዶቹ ፎቶዎቹ የተወሰዱት ከፋና ፌስቡክ እና ከኢንተርኔት ነው)


6ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 6 - ERi-TV Documentary

Dehai Events