World News

(መረጃ) የህዳሴው ግድብ በሚቀጥሉት 10 አመታት አይጠናቀቅም – ብዙው ነገር ለፖለቲካ ጥቅም ሲባል ወሬ ብቻ ነበር ።

Posted by: Semere Asmelash

Date: Tuesday, 24 July 2018


የህዳሴው ግድብ በሚቀጥሉት 10 አመታት አይጠናቀቅም – ብዙው ነገር ለፖለቲካ ጥቅም ሲባል ወሬ ብቻ ነበር ።


ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ጋር ባደረጉት ውይይት ስለህዳሴው ግድብ የተናገሩት በዚህ ፍጥነት ከተጓዝን በአስር አመትም ላንጨርሰው እንችላለን ብዙው ነገር ለፖለቲካ ጥቅም ሲባል ወሬ ብቻ ነበር ። ይህን ሲሉ ውዝፍ ስራችንን ተገንዝበን በፍጥነት መስራት አለብን በሚለው አውድ ውስጥ ነው። ለሀገራችን መስራት አለብን፣ እሁድ ቢሮ ስገባ የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ሰራተኞችን አላጋኛቸውም፣ በፍጥነት መሄድ አለብን እያሉ ሲያስረዱ ነው ስለ ግድቡ ከላይ የተጠቀሰውን የተናገሩት ሲሉ በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ምሁራን ይናገራሉ። ሌላኛው ምሁር በበኩላቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩን አነጋገር አጠር አድርገው የህዳሴው ግድብ በሚቀጥሉት 10 አመታት አይጠናቀቅም – ብዙው ነገር ለፖለቲካ ጥቅም ሲባል ወሬ ብቻ ነበር ። ሲሉ ፅፈውታል ።

የሕዳሴውን ግድብ አስመልክቶ አሁን እየተነገረ የሚገኘውን እውነታ በይፋ በ2011 ዓም Ethiopia’s dictator offers Egypt partial ownership of Nile dam ኢትዮጵያ ሪቪው ላይ The Nile Dam: Redemption or Deception of the TPLF regime?  እንዲሁም More evidence that Nile dam is a propaganda stunt እንዲሁም 2013 Ethiopians in Los Angeles organize to stop fund raising for Nile dam scam  በኢትዮጵያ ሪቪው ላይ 2016 The Dam-Nation of Ethiopia by the T-TPLF የሕዳሴውን ግድብ አስመልክቶ በግልጽ ቋንቋ እውነታው ተፅፏል። ዛሬ እነዚህ ጽሁፎች በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ተደግመዋል። በወቅቱ ግድቡን አስመልክቶ የፖለቲካ ጨዋታ መሆኑንና ሕወሓት እያምታታ መሆኑን በግልጽ ጽሁፎቹ ሲያስቀምጡ የሕወሓት አገዛዝ ሰዎችና አንዳንድ ተቃዋሚዎች በኢትዮጵያ ሪቪው ላይ ከፍተኛ የሆነ የጥላቻ ዘመቻ እና የስም ማጥፋት አካሂደዋል። እውነታው ግን እነሆ ጊዜውን ጠብቆ በዶክተር አብይ ተጋልጧል።

የሕዳሴው ግድብ ቦንድ ሽያጭ መልሰናል በሚል ፕሮፓጋንዳ ቢሰራም አብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍልና ዲያስፖራው ገንዘባችን ተበልቷል ሲል ማማረሩን በማሕበራዊ ድረገጽ የሚለቀቁ መረጃዎች ያመለክታሉ በተለይ በመካከለኛው ምስራቅ አረብ አገራት የሚገኙ ወገኖቻችን ወደ ኤምባሲ በገቡ ሰዓት ሁሉ ከፍተኛ የሆነ ዘረፋ በ አባይ ቦንድ ስም ይካሔድብን ነበር ሲሉ አማረው ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከከፍተኛ ተቋማት መምሕራን ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ የህዳሴው ግድብ በሚቀጥሉት 10 አመታት አይጠናቀቅም፡፡ ብዙው ነገር ለፖለቲካ ጥቅም ሲባል ወሬ ብቻ ነበር ። ብለው መናገራቸው አሳሳቢም አነገጋሪም ከመሆኑም በላይ በቦንድ ሽያጭ ስም የተሰበሰበው ገንዘብ የት እንደገባ ያጠያይቃል።

በአባይ ግድብ ስም የተሸጠ ቦንድ የተሰበሰበው ገንዘብ የት ገባ ይህ ጥያቄ መመለስ አለበት። የአባይን ግድብ ጉዳይ በተመለከተ ተጠያቂው ዶክተር አብይ አሕመድ ሳይሆን ከእሱ በፊት የነበረው የሕወሓት አገዛዝ ነው። ማንም የሕዝብ ገንዘብ ዘርፎ ዝም መባል የለበትም። ለ አባይ ግድብ ተብሎ ከደሃ ጉሮሮ ተነጥቆ የተወሰደው ገንዘብ ምንም ሳይሰራበት የባለስልጣናትን ኪስ ሲያደልብ እንደነበር ተጋልጧል። ያለፈው ሕወሓት መራሹ አገዛዝ ከተጠያቂነት አያመልጥም ፣ የ አባይ ግድብ ይህን ያሕል ፐርሰንት ቀረው ሊያልቅ ነው በማለት ሕዝብን ሲያጭበረብር እንደነበር በግልጽ ታውቋል። ከዚህ ቀደም በግድቡ አከባቢ ሲሰሩ የነበሩ ሰራተኞች የሚልኩልንን መረጃ ይፋ ስናደርግ የሃገር ጉዳይ ነው የሉዋላዊነት ጉዳይ ነው እየተባልን ከተቃዋሚ ወገኖች ሳይቀር ጫና እንዳልደረሰብን ዛሬ ላይ የህዳሴው ግድብ በሚቀጥሉት 10 አመታት አይጠናቀቅም፡፡ ብዙው ነገር ለፖለቲካ ጥቅም ሲባል ወሬ ብቻ ነበር ። ተብለናል። ከተጠያቂነትና ከሃላፊነት መሸሽ አይቻልም።

የህዳሴው ግድብ በሚቀጥሉት 10 አመታት አይጠናቀቅም – ብዙው ነገር ለፖለቲካ ጥቅም ሲባል ወሬ ብቻ ነበር ።



EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events