World News

(Satenaw) የታላቁ መሰሪ ኑዛዜ ! .. ተደብቆ የነበረው የመለስ ኑዛዜ ከ 5 ዓመት በኋላ ተጋለጠ

Posted by: Semere Asmelash

Date: Tuesday, 24 July 2018

የታላቁ መሰሪ ኑዛዜ ! .. ተደብቆ የነበረው የመለስ ኑዛዜ ከ 5 ዓመት በኋላ ተጋለጠ

•1/ የመለስ ራዕይ የተባለው የሀገሪቱ የኢህአዲግ መመሪያ ሆኖ በሐይለማርያም ዘመን ለ5 ዓመት የተሰራበት የነበረው (ዶክትሪን) መመሪያ የመለስ ዜናዊ ኑዛዜ ነበር፡

• ብራስልስ ሆስፒታል በህክምና ላይ እያለ የተደረገ የመለስ ዜናዊ ኑዛዜ፡፡
ኑዛዜውን የሰጠው በሆስፒታሉ ውስጥ በህክምና ላይ እያለ አለመትረፉን ሲያረጋግጥ ሊሞት 18 ቀን ብቻ ሲቀረው የሰጠው የኑዛዜ ቃል ነው፡፡

ኢትዮጵያን ከህዉሓት ደደቢቶች ዉጪ ከሆነች ፥ በሚከተለዉ መንገድ ሀገሪቷን ለማፈራረስ በህይወት እያለ ያቀደውን ሲሞትም እንዲቀጥል በሚል የሰጠው ኑዛዜ ከ 5 ዓመት በኋላ ይፋ ሆኗል ተብሎ ቀርቧል እነሆ ።

• ኑዛዜውን በወቅቱ ቀርቦ የተቀበለው አቶ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ ነው፡፡ የኑዛዜው 8 ዋና ርዕስ ያለውና በስሩ ደግሞ በርካታ ንኡስ ክፍል ያለው ነው፡፡
• አቶ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ ኑዛዜውን ጽፎ ከተረከበ በኋላ እንዲያስረክብ የታዘዘው የአድዋ ተወላጆች ለሆኑትና ንግስተ ሳባ በሚል ማህበር ለተደራጁት ነው፡፡
• እነዚህ የአድዋ ልጆች የመለስን ኑዛዜ ፈፃሚና አስፈፃሚ የሆኑ ሲሆን ኑዛዜውን በማናቸውም መንገድ ተፈጻሚ የሚያደርጉ ናቸው፡፡
እነሱም፡–
1/ ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገ/ሚካኤል
2/ አቶ ስብሀት ነጋ
3/ አቶ አርከበ እቁባይ
4/ አቶ አባይ ጸሐይዬ
5/ አቶ አስመላሽ ወ/ሥላሴ
6/ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ነጋና
7/ አቶ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ ኑዛዜውን የተቀበሉ ናቸው፡፡

8ቱ ኑዛዜዎች፤
•1/ የአድዋ ትግራይን የበላይነት ማስፈን ።

•2/ የአድዋ ተወላጆችን በከፍተኛ ስልጣን እርከን ላይ ማስቀመጥና ከነሱ ውጪ የሆኑት ሹሞች ከጀርባ ሆኖ መቆጣጠር ፡፡

•3/ ስትራዴጂ በመንደፍ በማንኛውም ጦር ክፍል አዛዥ ጄኔራሎች በፖሊስና በደህንነት ውስጥ የበላይ ባለሥልጣን
• በውጭ ጉዳይ
• በመከላከያ
• በየኤምባሲው
• በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ
በአጠቃላይ በፖለቲካ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ኑሮ ለመምራት ብቃት ያለው ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገ/ሚካኤል ስለሆነ እሱ በማናቸውም ሚኒስቴር መ/ቤት እና በማናቸውም ተቋማት ከጀርባ ሆኖ እንዲመራ ።

•4/ ጠቅላይ ሚ/ር ኃይለ ማርያምን ሲምቦል በማድረግ ደብረ ጽዮን ያዘዘውን ብቻ እንዲሰራ ማድረግ

•5/ ሀ ብሔርን ማጋጨት ፤ ብሔርን ብቻ ሣይሆን እንዱን ብሔርም በመከፋፈል እርስ በርሳቸው እንዳይግባቡ ለማድረግ በጥቅም መለያየት ፡፡
ለ. አማራውን ትምክህተኛ የዱሮውን ሥርዓት ናፋቂ በማለት በአደባባይ መዝለፍ፤ መውቀስ፡፡
ሐ. አማራውና ኦሮሞዉን ከውጭ ጠላት የበለጠ ጠላት ስለሆነ በማናቸውም መንገድ ማዳከም አጥብቃችሁ ስሩ፡፡
መ. በኢኮኖሚ እንዲዳከም እና የትግሬ ጥገኛ ሆኖ የትግራይን ሀያልነት አምኖ እንዲቀበል ማድረግ፡፡
ሠ. የኦሮሞዉን ምሁር ማሳደድና ሞራሉ እንዲወድቅ ማድረግ፤ሃገር ጥሎ እንዲሰደድ ማድረግ ትልቁ ስራችሁ ይሁን ይላል፡፡
ረ. ትግራይን ለሪፈረንደም ማዘጋጀት ማለትም በኢኮኖሚ በማሳደግ በእርሻው አዲስ በተቀየሰዉ ክልል መሰረት ግብርና በቤንሻንጉልና በጋምቤላ ማስፋፋት
ሰ. ኢንዱስትሪውን በትግራይ እንዲስፋፋ ማድረግ፤
ሸ. ታላቋ ትግራይን ለመመስረት ማለትም ምዕራብ ጎንደርን ይዞ ቤንሻንጉልንና ጋምቤላን የሚያካትት ግድብ በትግራይ ክልል ውስጥ እንዲካተት ማድረግ፡፡
ቀ. ይህንን ማፕ ዓለም አውቆት እንዲቀበለው ማድረግ፡፡
በ. ከአጎራባች ክልሎች የተወሰዱትን ቦታዎች ላይ የሰፈሩ ነዋሪን የትግራይ መታወቂያ በግድ እንዲወስዱ ማስገደድ፤አንወስድም ካሉ ማዋከብ ፤ማስጨነቅ፤በኢኮኖሚ እንዲወድቁ ማድረግ፤ማሰርና በጣም የሚያስቸግሩ ካሉ መግደል ፡፡
ተ. በየአካባቢው ያሉ የሀገር ተቆርቋሪዎች ታሪክ አዋቂ ሽማግሌዎችና ለህዝብ አሳቢዎችን ማጥፋት ፡፡

•6/ ሀ. ከሱዳን ጋር ድንበርተኛ ለመሆን ሱዳን የምትፈልገውን ሁሉ ማድረግ፡፡
ለ. ትግራይን ከሱዳን ጋር ድንበርተኛ እንደሆነች ለዓለም ህብረተሰብ ተቀባይነት እንዲኖረው ማድረግ፡፡
ሐ. የዓለም ህብረተሰብ ማለትን ሃያላኑ የትግራይን ማፕ እውቅና እንዲሰጡ ለነሱ መታዘዝ
ለምሳሌ ፦ ወታደር ማዝመት ፤ መሬት መስጠት (የሱማሌና የደቡብ ሱዳንን ዓይነት)
መ. በባንዲራው ላይ ያለውን (የኢሉምናት) ማለትም የግብረ ሰዶምና ርካሽ ባህል ምልክት
የሆነውን በባንዲራችን ላይ አርማ እንዲሆን ማድረግ፡፡

•7/ ሀ. የአድዋ ተወላጅ የሆኑትንና የሳባ ማህበር አባል የሥርዓቱ ታማኝ አድርጎ በትምህርትና በሙያ ማሰልጠን፡፡

ለ/ አሰልጥኖ ወደ መሃል አገርና ወደ ተለያዩ ክልሎች በመላክ በተለይ በደህንነት ሥራ ላይ እንዲሰማሩ ማድረግ ፡፡
ሐ/ በውትድርናም የሌላውን ብሄረሰብ ከመቅጠር ይልቅ የትግራይን ወጣቶች ብቻ በብቃት አሰልጥኖ ማሰማራት ፡፡
መ/ የሳባ ማህበር ዋና መ/ቤቱ አድዋ ሲሆን ቅርንጫፉ አ/አበባ ቦሌ የሚገኝ ነው፡፡በዚህ ሴፍ ሀውስ በሚል የሚታወቀው መ/ቤት የመንግስት አሰራሮች የሚቀረፅበት ሲሆን በዚህ መ/ቤት የተነደፉ የአስተዳደር የአሰራርና የአተገባበር ዕቅዶች በሙሉ ተቀርፀው ወደ ታች የሚፈሱ ናቸው ፡፡
ሠ/ ጠ/ሚ/ር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ለፊርማ ብቻ የሚጠራ ሲሆን የሚፈርምበትን ወረቀት ማንበብ ሥልጣን እንዳይኖረው አድርጎ መቅረጽ፡፡
የስብሰባቸው ሰዓት ከቀኑ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ሲሆን ከዚያ በኋላ በአካባቢው ማንም ሰው ዝር የሚል የለም፡፡ (በጌታቸዉ.አሰፋ ቁጥጥር ስር በሮማን እገታ የተባለው ልብ ይሏል)

•8/ ሀ/ የኦሮሞና.የአማራ ጠባቦችን መጠቀም ፡፡ የሁለቱን. ኤሊቶች ማጋጨት ወደ ሕዝቡ እንዲወርድ በማድረግ በማጣላት ስራ ላይ በርትታችሁ እንደትሰሩ ፡፡

•9/ አዲስአበባ ጉዳይ በተለየ ሁኔታ የአፍሪካ ከተማ ከመሆኗ አንፃር ትልቁ የመወዛገቢያና የመከፋፈያ ቁልፍ ማድረግና የአለምን ቀልብ መሳቢያ መድረክ እስከሚሆን ድረስ መስራት ።. [በ19:98 የተሰራው አሻጥር ልብ ይሏል]
ለ/ አማራና ኦሮሞ አንድ የሆኑ ቀን የታላቋ ትግራይና. የሕዉሓት ጉዳይ ያልቃልና የማጋጨትና የማጣለት ሥራችሁ ከማናቸውም ሥራ ቅድሚያ ስጡት፡፡

ሐ/ የትግራይ ሪፐብሊክ የሚመሰረተው በጎንደርና በወሎ መሬት ላይ ነው የአማራው ከፍተኛ ሃይል ደግሞ ጎንደር ነው ፡፡ ስለዚህ ጎንደርን በመከፋፈል እንዲዳከሙ ማድረግ፤

መ/ ጎንደርን መከፋፈያ መንገድ ዋናው በውስጡ የተለያዩ ብሄሮች ነን የሚሉ ስለ አሉ እነሱን የራሳቸውን ክልል እንዲመሰርቱ የብሄር ጭቆና አለብን በማለት ሪፈረንደም እንዲጠይቁ ማነሳሳት እናንተም ያንን ጥያቄ በመደገፍ የኢኮኖሚ የፖለቲካና የጦር መሣሪያ ድጋፍ በማድረግ እንዲገፉበት መገፋፋት፡፡

ሠ/ አሁን የተጀመረው የቅማንት ማንነት ጥሩ ጅምር ስለሆነ ሌሎቹንም እነሽናሻ
የመሣሠሉትን መቀስቀስና እርስ በርስ እንዲፋጁ ማድረግ፤

ረ/ ሌላው ደቡብ ጎንደር ሰሜን ጎንደር ምዕራብ ጎንደር በማለት ከፋፍሎ አንዱን ማገዝና በሌላው ላይ እንዲዘምት ማድረግ።

ሰ/ ትልቁ ሥራ ደግሜ አደራ የምለው በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ አማራው ከኦሮሞው ጋረው እንዳይስማሙ ጥረት ማድረግ ነው፡፡

ሸ/ ኦሮሞውን በትምህርት ደካማ እንዲሆኑ ማድረግ በተለይ ከለአማራው ጋር እንይግባቡ ማድረጊያው ትልቁ መሣሪ የኦሮሞ ልጆች አማርኛ እንዳይማሩና ብሄራዊ ቋንቋ እንዲያውቁ ማድረግ፡፡

ቀ/ ትግራይ በሪፈረንደም እራሷን እስከምትችል ድረስ እግር የሚያወጣውን ኦሮሞ እግሩን መቁረጥ ፡፡በኢኮኖሚ ማዳከም፤የኦሮሞ ህዝብ ከሌላው ብሄር ጋር እንዳይግባባ ማድረግ፡፡

በ/ ከኦሮሚያ አጎራበች ካሉ ክልሎች በግጦሽ እና በውሃ እንዲጣሉ ማድረግ፡፡

ተ/ በየጊዜው ኦሮሞ ሊገነጠል ነው ብሎ ማስወራት፡፡ ኦፒዲዮን በኦነግ አምሳያ መሳል ። እንዲገነጠል አድርጎ እንደ.ህዉሓቷ ትግራይ ሪፈረንደም እንዲጠይቅ ማድረግ፤ ከዚያ አማራውም ስለማይችል የራሱን ሪፈረንደም እንዲጠይቅ ማስገደድ፡፡

ቸ/ ቀጥሎ ቤንሻንጉልና ጋምቤላ ሪፈረንደም እንዲጠይቁና ከትግራይ ጋር እንዲሰሩ ማድረግ፡፡

ኀ/ ደቡብ ብሔረሰቦች አብረው እንዲገነጠሉ ማግባባትና ግፊት ማድረግ፡፡

• 10/ በሐይማኖቶችና በቤተ እምነቶች ጣልቃ በመግባት ማበጣበጥ ልዩነታቸውን መለጠጥ ማስፋት ።

• 11/ የኤርትራ ጉዳይ ፈፅሞ እንዳይነሳ ፣ ከካዝና መሳቢያ ዉስጥ ተቆልፎ በፍፁም እንዳይወጣ ። መቋጫም እንዳያገኝ ድንበሩ ላይ ያሉት ወታደሮች ፈፅሞ ስለ ሰላም እንዳይሰሙ ማድረግ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚነሱትን ማናቸውም ሰላማዊ ጥያቄዎች ከሻዕቢያ ጋር ማገናኘትና ማሸማቀቅ መወንጀል ።

በዚህ ጊዜ ሃገሪቱ እንድትበታተንና የትግራይ የበላይነት ሰፍኖ ትግራይ በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጣ በመቃብር ውስጥ ሆኜ አያታለሁ ፡፡

‹‹ የኑዛዜው አደራ እስካሁን በሐገሪቱ ላይ ተሞክሮ ከሽፏል ።

የኑዛዜውን ቃል ፈትሹት…

እንኩዋንም. ሞት ቀደመህ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ከዚህ ኑዛዜ ዉጪ የደደቢት ጅቦች ሌላ አይመኙልህም ። ታሪክህን አወቅህ አሁንስ አይበቃም፤የኑዛዜውን ተግባራዊነት ትጠብቃለህ ወይስ ሃገርህን ለማዳን ተባብረህ ትነሳለህ?

መልሱ___ያንተዉ. ነው ።

ኢስማኤል ዳውድ

EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events