World News

Mereja.com: ኢሳያስ አፈወርቂ መቀሌ ያልሔደው የሰኔ 16 የአዲስ አበባው ችግር ተፈጥሮ የሕዝቦች ግንኙነት እንዳይበላሽ ነው።

Posted by: Berhane.Habtemariam59@web.de

Date: Tuesday, 24 July 2018

 

የዩንቨርስቲ ምሁራኖች እና ከጠቅላይ ሚነስትሩ ጋር ካደረጉት ውይይት የጅጅጋ ዩንቨርስቲው መምሕር ሙክታር እንደከተበው።

ስለሚዲያዎች የተጠየቀን ጥያቄ በመንተራስ ስለ ENN ወሳኝ ነገር ተናግረዋል። ሚድያው በመንግስት መስሪያቤት መዋቅር ይሰራ የነበረ፣ የደሞዝ አከፋፈሉም ከሌላው የተለየ የነበረ፣ አንዳንድ አጥፊ ዘገባዎችንም ከዚሁ መስሪያቤት ጋር ሆኖ በዚሁ መዋቅር ፈንድ እየታገዘ የሚሰራ ነበር። ማናጀሩ የሚይዘው መኪና የመንግስት ነበር። እኛ አልዘገናውም፣ ያደረግነው ይህን መስሪያቤት ሪፎርም ስናደርገው በጀቱ ቀነሰባቸው፣ ከጀርባቸው ያሉ ሰዎች ፈንዱን ሲያቋርጡባቸው ዘጉት። መንግስት ዘጋው ሲሉ ይከሳሉ! የተዘጉት ግን በዚህ መንገድ ነው ብለዋል! (መስሪያቤቱን ገምቱ እናንተ!) አይ አንቺ ሀገር!


የእኔ የቀጣይ ሁለት አመት ዋና አላማ ቀጣዩ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ መሆኑን እና የኢትዮጵያ ህዝብ በመረጠው መንግስት መተዳደር መጀመሩን ማረጋገጥ ነው ሲሉ ከወንበራችን ተነስተን አጨበጨብን (ይህን የማይመሰክሩ ሰዎች የእውነት ሰዎች አደሉም!

ህገመንግስቱ ይሻሻላል! ካሉ በሃላ የባንዲራን ጉዳይ አንስተው “መለወጥ ያለብን ስርአትን ነው። አንዳንድ ሰው በሆነ ባንዲራ ዘመን የደረሰበትን በማስታወስ ሊቃወም ይችላል። ለምሳሌ በልሙጡ ባንዴራ ዘመን የተገደለ፣ የተሰደደ፣ የተበደለ ይህን ትዝታ ከባንዲራ ጋር ያይዛል፣ የኮኮቡም ጥላቻ ከዚሁ ጋር የሚያያዝ ነው። የኢትዮጰደያ ህዝብ መክሮበት የባንዲራን ጉዳይ ይወስናል። የአሜሪካ ባንድራ ብዙ ጊዜ ተሻሽሏል፣ አዲስ ነገር አይደለም ባንዲራ ማሻሻል። ግን ስርአትን በማሻሻል ላይ እናተኩር” ቃል በቃል ባይሆን ይህን ሀሳብ ነው የተናገሩት!

ፖለቲካውን ከትምህርት ተቋማት እናስወጣዋለን። ሀሳብ የሚንሸራሸርበት ቦታ እናደርገዋለን። ይህ ካልሆነ የተፎካካሪ ፓርቲ ፅቤት መክፈት ሊኖርብን ነው! ስለዚህ ዩኒቨርስቲዎች ከፖለቲካ ስራዎች መራቅ አለባቸው ብለዋል ጠቅላዬ!

እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ ትንሽም ጊዜ ብቆይ የትግራይን ህዝብ ጠቅሜ ነው የማሳልፋት። የትግራይ ህዝብ ከዚህ ስርዓት የተለየ ጥቅም አላገኘም! አንዳንዶች ሃያ አመት ህዝቡን ዞር ብሎ ሳያዩት፣ አሁን ጥቅማቸው ሲነካ ህዝብ ውስጥ የሚደበቁትን ነገር የትግራይ ህዝብ ያውቃል! ይህን ታዝቦ ህዝቡ ማን እንደሚጠቅመው የራሱ ውሳኔ ያሳልፋል!!! ነው ያሉት ጠቅላዬ

ኢሳያስን መቀሌ ብወስደው በጣም ደስ ይለኝ ነበረ! ምኞቴም ያ ነበር! ምክንያቱም መቀሌ ከአስመራ አንፃር በዚህ ሃያ አመታት ውስጥ ለውጧን በመመልከት የቁጭት ስሜትን በመፍጠር የሁለቱ ወንድማማች ህዝቦችን የጋራ እድገት ትርፉ ለሁለትም ህዝቦች እንደሆነ ለማሳየት ነው። ግን ስጋቴ እንደአዲሳባው አይነት ነገር ቢከሰት የሁለቱ ህዝቦችን ይጎዳል ብዬ ስለሰጋሁ ሀሳቡን ተውኩት ነው ያሉት

ስለህዳሴው ግድብ የተናገሩት “በዚህ ፍጥነት ከተጓዝን በአስር አመትም ላንጨርሰው እንችላለን” ይህን ሲሉ ውዝፍ ስራችንን ተገንዝበን በፍጥነት መስራት አለብን በሚለው አውድ ውስጥ ነው። ለሀገራችን መስራት አለብን፣ እሁድ ቢሮ ስገባ የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ሰራተኞችን አላጋኛቸውም፣ በፍጥነት መሄድ አለብን እያሉ ሲያስረዱ ነው ስለ ግድቡ ከላይ የተጠቀሰውን የተናገሩት!

የኢህአዴግ ፍልስፍና ይቀየራል አይነት ወሬ ውሸት ነው! እሳቸው ያሉት የኦህዴድ ፖለቲካዊ አተያይና ፍልስፍና፣ ስያሜው፣ ሎጎው ይለወጣል አሉ፣ ይህን ያሉት አሁን ካለን ሀገራዊ የመደመር እይታ አንፃር ኦህዴድ ከፍ ወዳለ ቁመና እንደሚያድግ ለማስረዳት በወጠኑት ሀሳብ አውድ ነው ይህን የተናገረው!


EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events