World News

Mereja.com: ኢሕአዴግ በሆዳም ካድሬዎቹና በጥቅም በገዛቸው ወሮበሎች ሃገር እየበጠበጠ ነው።

Posted by: Berhane.Habtemariam59@web.de

Date: Wednesday, 13 June 2018

ተአምር ከሰማይ የወረደ ያሕል ስናጋንን አገራችን ወደ ከባድ አደጋ እያመራች ነው።
ልንክደው የማንችለው = አትኩሮት የነፈግነው = በራሳችን ድክመት ኢሕአዴግ የፈጠረው

  • – የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይሎች በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚያደርጉት ግድያና ማሳደድ
  • – የኦሕዴድ ካድሬዎች አማራውን እያፈናቀሉ ቤቱን እያቃጠሉ እየገደሉ ማሳደድ
  • –በቤንሻንጉል ጉምዝ በአማራው ላይ አሰቃቂ ግድያና ማፈናቀል እስከ ብልት መስለብ
  • – በአፋር ሕዝብና በ አማራ ሕዝብ መካከል የተከሰተው ግጭት
  • – በጌድዎ ሕዝብና በጉጂ ኦሮሞዎች መካከል በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው ግጭት
  • – በኦሮሞና በሲዳማ ሕዝብ መካከል የሚደረገው ግጭት
  • – በሲዳማና በወላይታ ሕዝብ መሓል የተከሰተው ግጭት
  • – በጉራጌና በቀቤና መካከል የተከሰተው ግጭት
  • – በሀረር በክልሉ ካድሬዎች መካከል የተለኮሰው እሳት
  • – በትግራይ በሀጋር ሉአላዊነት ስም የተሰራጨው አደንዛዥ አጀንዳ … ወዘተረፈ …

አደግመዋለሁ ስለ እውነት እንቁም ስለሕግ እንቁም ስለ ሕዝብ መብት እንቁም። ከላይ በዝርዝር የተከሰቱና የቀተሉ ወደፊትም የሚከሰቱ ግጭቶች በዋናነት ስፖንሰር ሆኖ የሚያካሂደው የሚያስፈጽመው ኢሕአዴግ የተባለ ስልጣኑን መነጠቅ የማይፈልግ ስለ ሕዝብ ደንታ ቢስ የሆነ ድርጅት ነው። ኢሕአዴግ በሆዳም ካድሬዎቹና በጥቅም በገዛቸው ወሮበሎች ሃገር እየበጠበጠ ነው። ሕዝብን እየገደለ እያፈናቀለና እያሳደደ ነው። ለዚህ ደግሞ የተቃዋሚውን መዘናጋት ተጠቅሞበታል። ተቃዋሚው ከመታገልና በሕዝብ ውስጥ ስራ ከመስራት ይልቅ ተዓምር የወረደ ያሕል የኢሕአዴግን አጀንዳ በቅንነት ሲያስፈጽም ሕዝብ አደጋ ላይ ሆኗል።ተአምር ከሰማይ የወረደ ያሕል ስናጋንን አገራችን ወደ ከባድ አደጋ እያመራች ነው። የስርዐቱ የጎሳ ፌዴራሊዝም ችግር ብቻ ሳይሆን ኢሕአዴግ ስልጣኑን ላለመነተቅ የሸረበው ሴራ ነው። ሕዝብ ባለው አገዛዝ ሴራ ከመጠቀም ይልቅ እንዲጨፋጨፍ ግፊት እየተደረገበት ነው። በዙሪያችን ያለውን ነገር በመገምገምና ከኢሕ አዴግ የፖለቲካ ባሕርያት አንጻር በመለካት ልንታገልል ይገባል። ለዚህ ደግሞ መፍትሔ የሚሆነው ባለው አገዛዝ ላይ ጫና በመፍጠር በህዝብ መሃል ገብቶ በማስተማርና የትግል ፍሬዎች እንዲያብቡ በመታገል ነው።


7ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 7 - ERi-TV Documentary

Dehai Events