World News

Satenaw.com: ሰበር ዜና – የመቀሌው ሕንፍሽፍሽ – የህወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ በ3 ተከፈለ!!

Posted by: Berhane.Habtemariam59@web.de

Date: Tuesday, 12 June 2018

ወዲ/ሻምበል ዘብሔረ ኢትዬጵያ

http://welkait.com/wp-content/uploads/2018/06/Ye-Mekele-Hinfishfish-768x432.png

የክልሉ ዋና ከተማ መቀሌ ላይ በድንበር ውሳኔ ለመምከር ለአስቸኳይ ስብስባ የተቀመጠው የህወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ ለሶስት መከፈሉን ተሰምታል አንደኛው መሬትን አሳልፈን እንስጣቸው ሲል ሁለተኛው በፍፁም አናደርገውም ብሏል ሶስተኛው ደግሞ ከኢህአዴግ እራሳችንን እናግልል ወይም እንውጣ ብሎአል አሁንም ገና እልባት አላገኘም።

ምንጭ በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው ባለ ፅኑ አቋም ከትግራይ አክቲቭስት ኃይለኪሮስ ታፈረ።

******

ቁጣ፣ ክፍፍልና ትርምስ … ኢሕአዴግ፣ ሕወሓት፣የትግራይ ህዝብ፣ ዓረና ትግራይ፣ አይጋ ፎረም እና ሌሎች የሕወሓት ሚዲያዎች

(ከድር እንድርያስ)

#ኢሕአዴግ

♦ የሕወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ #የኢሕአዴግን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያሰላለፈውን ውሳኔ፣ ያወጣውን መግለጫ እና ለኤርትራ መንግስትና ህዝብ ያቀረበውን የሰላም እና የጋራ ተጠቃሚነት ጥሪ #ለመሻር ወይም #ለማሻሻል በመቀሌ ተሰባስበዋል።

#ሕወሓት

♦ በሕወሓት ውስጥ ያላው ክፍፍል እየከረረ ነው። አሁን ያለው ሕወሓት የሌቦች እና የባልቴቶች ጥርቅም ነው። የትግራይ ህዝብ ተከድቷል። የአድዋ የቤተሰብ ዳይናስቲ ይወገዱ፣ ለፍርድም ይቅረቡ የሚሉ የሕወሓት ካድሬዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። ሌላ #አንጃ ሊፈጠርም ይችላል። የመለስ ራዕይ ደጋፊዎች እና በቅርብ በተሐድሶ ከስልጣን የተባረሩት አመራሮችም እጃቸውን አስገብተዋል።

#የትግራይ ህዝብ

♦ የትግራይ ህዝብ ከኤርትራ ጋር ሰላም ይቅደም፣ ኤርትራውያን በደም የተሳሰርን አንድ ህዝብ ነን በሚሉ የኣግኣዚያን እንቅስቃሴ አባላት እና ሉዐላዊነታችን ይቅደም መሬታችን ለሻዕቢያ አንሰጥም፣ የአልጀርሱን ውሳኔ ፈፅሞ አንቀበልም በሚሉ የትግራይ ተወላጆች መካከል ያላው ልዩነት እየሰፋ ነው። ዛሬ በትግራይ በርካታ ስብሰባዎች በመካሄድ ላይ ናቸው።

#ዓረና ትግራይ

♦ ሕወሓት እና ዓረና ትግራይ ፍጥጫ ላይ ናቸው። የዓረና ትግራይ አመራሮች ሰሞኑን ስብሰባ ላይ ናቸው። በመግለጫቸው እንደጠቆሙት በመላ ትግራይ ታላላቅ ስብሰባዎችን እና ሰልፎችን ለመጥራት በዝግጅት ላይ ናቸው።

#አይጋ ፎረም

♦ አይጋ ፎረምን ጨምሮ ሌሎች የሕወሓት ሚዲያዎችም የትግራይ ህዝብ ከኢሮብ ህዝብ ጎን በመቆም የሕወሓት/ኢሕአዴግን ውሳኔ እንዲቃወም ጥሪ አቅርበዋል። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስትን አቋም አክርረው በመቃወም ላይ የሚገኙት የሕወሓት ካድሬዎች ናቸው። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳት፣ የአልጀርሱ ስምምነት መቀበል፣ የእስረኞቹ መፈታት፣ የሚዲያዎች ሚዛናዊነት ማጣት፣ የኦሕዴድ እና ብአዴን አካሄድ፣ የዶ/ር አብይ ያልተጠበቁ እርምጃዎች ጥቂቶቹ ናቸው።

#ኢህአዴግ

ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫና ጥሪ…

ኢትዮጵያ ኤርትራ መካከል ተፈጥሮ የቆየውን አለመግባባት እንዲያቃና በሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰለም እንዲፈጠር ከኢህአዴግ የቀረበ ጥሪ!

….. የሁለቱ ሀገር ሕዝቦች የጋራ ጥቅም ሲባል የኢትዮጵያ መንግስት የአልጀርሱን ስምምነት እና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ የወሰነና ለተግባራዊነቱ ያለማመንታት በቁርጠኝነት የሚሰራ መሆኑን ለመግለፅ ይፈልጋል፡፡

ወልቃይት


EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events