World News

Satenaw.com: ጠ/ሚ አብይ ለመከላከያ አመራሮች በንድፈ-ሃሳብና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ገለጻ ሰጡ

Posted by: Berhane.Habtemariam59@web.de

Date: Sunday, 03 June 2018

"የመከላከያ ወሳኝ አቅሞች ለማሰደግ በምድር ሀይልና በአየር ሀይል በአፍሪካ ቀደምት ሀገሮች ተርታ ያስቀመጠንን ሀይል ገንብተናል ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ የባህር ሀይል አቅምችንም በቀጣይ ማሳደግ ይገባናል ብለዋል"፡፡

***ገሪሙኒ!፥ "እቲ ናይ ምድሪ ሓይልን ኣየር ሓይልን ዓቕምና ኣብ ኣህጉር ኣፍሪቓ ዝሰርዓና ዓቕሚ መስሪትና ኣሎና" ዝበሎ ኣብ ባይታ ዘየሎን ዝተጋነነ መናፍሕን ንጐድኒ ተገዲፉ፣ "ናይ ባሕሪ ሓይልና ዓቕሚ ብቐጻሊ ከነዕቢ ኣሎና" ዝበሎ ዓጀውጀውን ናይ ኣቦሓጎታቱ ሕልሚን ግን ኣነ ከም ኤርትራዊ ዜጋን ህዝቢ ኤርትራ ድማ ብዓቢኡ የገድሰናን ዘይሕጋውን ዓመጸኛን ከምኡ`ውን ዘለፋ ኣብ ልዑላዊት ናጻ ሃገርና ኤርትራን ላግጺ ኣብ ህዝብናን ስለ ዝኾነ ከይሳዕረረ ክኹነንን ኣንጻሩ ድማ ግብራዊ ስጉምቲ ክውሰድን ይግባእ። ለባማት ኣቦታትና እንክምስሉ "ካብ ሎሚ ዝነቀወ ዝብእስ ጽባሕ`ውን ኣየደቅሰንን`ዩ" ዝበሉዎ፣ እዚ ሓድሽ ቀዳማይ መራሒ ኢትዮጵያ ድማ እታ ዝመሽመሸትን ናይ ቀደም መራሒ ወያነን ኢትዮጵያን ነበር መለስ ዜናውን ተካኢኡን ነበር ሃይለማርያም ደሳለኝን መዝሙር ሰላም ክደግም ጸኒሑ፣ ሕጂ ድማ ሽግር ሃገሩ ኣብ ክንዲ ምፍታሕ "ናይ ባሕሪ ሓይልና ዓቕሚ ብቐጻሊ ከነዕቢ ኣሎና" ምባሉስ ምስ ምንታይ ይቑጸር? ኣበየናይ ባሕሪ`ዩኸ እቲ ባሕሪ ሓይሊ ክስልጥንን ክዓብን? ፖለቲካዊ ዕብዳን`ዶ ክንብሎ ወይ`ሲ ናይ ጫት ምርቀና? ..................

ብርሃነ ሃብተማርያም

የኢፌድሪ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ለመከላከያ ሰራዊት ሃላፊዎች በንድፈ-ሃሳብ የታገዘ ገለጻና ከሃላፊዎቹ ጋር በሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳች ዙሪያ ውይይት አደረጉ።


 

ሀገራችን ብሄራዊ ጥቅሞችን ለማስከበር የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ቴክኖሎጂ፣ ዲፕሎማሲ እና ወታደራዊ አቅሞችን አቀናጅቶ ሀገራዊ ክብርና ልዕልናዋን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የመከላከያ ሰራዊት የማይተካ ሚና እንዳለው ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አስታውቀዋል፡፡

ብሄራዊ ፍላጎትና ጥቅም በሌላ ቋንቋ የህዝብ ፍላጎትና ጥቅም ማለት በመሆኑ የመከላከያ ሰራዊትከ ህገ-መንግስቱ የሚመነጩ ግልጽ ተልዕኮዎችን አንግቦለህ ዝብፍላጎት የሚገዛና ለህዝብ ጥቅም የሚሰራ መሆን አለበት ብለዋል፡፡

ብሄራዊ ፍላጎትና ጥቅም በሌላ ቋንቋ የህዝብ ፍላጎትና ጥቅም ማለት በመሆኑ የመከላከያ ሰራዊትከ ህገ-መንግስቱ የሚመነጩ ግልጽ ተልዕኮዎችን አንግቦለህ ዝብፍላጎት የሚገዛና ለህዝብ ጥቅም የሚሰራ መሆን አለበት ብለዋል፡፡

የተለያዩ ሀገሮች የመንግሰት ምስረታ ታሪክ እንደሚያሳየው በ19ነኛውና 20ኛው ክ/ዘመን በፊት የሀገር ጥቅምና ፍላጎት የሚመነጨው ከተለያዩ የገዥ መደቦችና እምነት ተቋማት እንደሆነ የጠቆሙት ጠ/ሚሩ ዘመናዊው ብሄራዊ ጥቅምና ፍላጎት አረዳድ ግን ህዝብና ህዝብን ብቻ መሰረት ያደረገነው ብለዋል፡፡

የብሄራዊ አቅማችን ዋነኛ መገለጫ የሰላም፣ የልማትና የዲሞክራሲ ግቦች ማሳካት እና የሀገራችን ህዝቦች ክብርና የሀገር ሉዓላዊነት ማስከበር ናቸው ብለዋል፡፡

ዘመናዊው ጦርነት ከመደበኛ የጦርነት አውድ የተለየ ቅርጽና መልክ አለው፡፡ መንግስታትና መንግስታዊ ያልሆኑ የጦርነት ተዋናዮች የሚሳተፉበት፣ የግለሰቦች እና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላትን የማድረግ አቅም ያመጠቀ የቴክኖሎጂ እድገት መኖር እና አለማ-ቀፋዊነት ያመጣው የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ እና የባህል ትስስር ከፍተኛ የሆነበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ሲሉ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የዘመናዊ ጦርነት ምህዳሩን ባህሪያት አስረድተዋል፡፡

የጦርነት ስልቱም አሸናፊ ሆኖ ለመገኘት ከሚደረግ ጥረት ይልቅ የተፃራሪ ኃይሎችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ስርዓቶችን የሚያሳትፍ፣ የተፃራሪ ሀይልን ውሳኔ ሰጪ አካላት ስትራተጂ እቅድ እንዳይሳካ ወይም ውድ ዋጋ የሚያስከፍል ሆኖ እንዲታይ ማድረግን መሰረት ያደረገ የጦርነት ስልት ነው ብለዋል።

ዘመናዊ መደበኛ ጦርነቶች የሚያስከፍሉት ዋጋ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ መግስታት በቀጥታ ጦርነት ከመግባት ይልቅ የውክልና ጦርነትን መምረጥ የሚታይበት ምህዳር እንደሆነጠቁመዋል።

በተጨማሪም የምንገኝበት የአራተኛው ትውልድ ጦርነት አለም በነገሮች እና በኩነቶች መተሳሰር ምክንያት አንድ አካባቢ የሚከሰት ድርጊት አለማቀፋዊ በሆነ መልኩ ቀውስን የሚያስከትል ነው።

በነገሮች እና በኩነቶች መተሳሰር እጅግ በጠነከረበት በዚህ ዘመን የሚያጋጥሙ ስጋቶችን መረባዊ የሆኑ በመሆናቸው፣ ስጋቶቸን መመከት የሚቻለው በመረባዊ አደረጃጀት ነው ብለዋል።

ዘመናዊ መደበኛ ጦርነቶች የሚያስከፍሉት ዋጋ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ መግስታት በቀጥታ ጦርነት ከመግባት ይልቅ የውክልና ጦርነትን መምረጥ የሚታይበት ምህዳርእንደሆነጠቁመዋል።

በተጨማሪም የምንገኝበት የአራተኛው ትውልድ ጦርነት አለም በነገሮች እና በኩነቶች መተሳሰር ምክንያት አንድ አካባቢ የሚከሰት ድርጊት አለማቀፋዊ በሆነ መልኩ ቀውስን የሚያስከትል ነው።

በነገሮች እና በኩነቶች መተሳሰር እጅግ በጠነከረበት በዚህ ዘመን የሚያጋጥሙ ስጋቶችን መረባዊ የሆኑ በመሆናቸው፣ ስጋቶቸን መመከት የሚቻለው በመረባዊ አደረጃጀት ነው ብለዋል።

ይህንን ወቅታዊና ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት መከላከያ ሰራዊቱ ራሱን በቀጣይ የለውጥ ምህዋር ውስጥ ማስገባት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።የሪፎርሙ መነሻ ሁኔታዎችም የሀገሪቱ የማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚ ሁኔታዎችና በአጠቃላይ የህዝብ ስሜት ነው ብለዋል፡፡

ሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዙሪያ መለስ የፖለቲካ አለመረጋጋት ውስጥ በመቆየት ከፍተኛ አደጋ ያንዣበበት ሁኔታ ተፈጥሮ እንደነበር ያስታወሱት ጠ/ሚኒስትሩ ችግሩን የፈጠረው መንግስት ችግሩን መፍታት አይቻልም እስከመባል የደረሰ ትችት ቢደርስብንም ተግዳሮቱን ወደ እድል ቀይረን ሀገራዊ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን በአፋጣኝ መውሰድ በመጀመራችን የህዝቡን ተስፋ በድጋሚ በማግኘታችን ለውጡን ለማስፋትና ለማጥለቅ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል፡፡

የሪፎርሙ መነሻ ሁኔታዎችም የሀገሪቱ የማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚ ሁኔታዎችና በአጠቃላይ የህዝብ ስሜት ነው ብለዋል፡፡

ሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዙሪያ መለስ የፖለቲካ አለመረጋጋት ውስጥ በመቆየት ከፍተኛ አደጋ ያንዣበበት ሁኔታ ተፈጥሮ እንደነበር ያስታወሱት ጠ/ሚኒስትሩ ችግሩን የፈጠረው መንግስት ችግሩን መፍታት አይቻልም እስከመባል የደረሰ ትችት ቢደርስብንም ተግዳሮቱን ወደ እድል ቀይረን ሀገራዊ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን በአፋጣኝ መውሰድ በመጀመራችን የህዝቡን ተስፋ በድጋሚ በማግኘታችን ለውጡን ለማስፋትና ለማጥለቅ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል፡፡

በመሆኑም የመከላከያ ሀይል በኩል ያለው ዋነኛ ቁልፍ ሪፎርም ጉዳይ የሰራዊቱን ፕሮፌሽናሊዝም ማሳደግ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ ይህም ሲባል የሰራዊቱን ሙያዊ ብቃት፣ ሃላፊነት የመውስድና የተሟላ ሰብዕና የተላበሰ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህ ሲሆን ሰራዊቱ በመርህ የሚገዛና ለወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ተጽዕኖ በቀላሉ እጅ የማይሰጥ የህዝብን ፍላጎትና ጥቅም የሚያስከበር ያደርገዋል ብለዋል፡፡በቅርቡ በተደረገው የመንግስት ስልጣን ሽግግር ወቅትም ሰራዊቱ ያሳየውን ሙያዊ ዲሲፕሊን ያደነቁት ጠ/ሚኒስትሩ ይህ ፕሮፌሽናሊዝ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

በቅርቡ በተደረገው የመንግስት ስልጣን ሽግግር ወቅትም ሰራዊቱ ያሳየውን ሙያዊ ዲሲፕሊን ያደነቁት ጠ/ሚኒስትሩ ይህ ፕሮፌሽናሊዝ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

የመከላከያ ወሳኝ አቅሞች ለማሰደግ በምድር ሀይልና በአየር ሀይል በአፍሪካ ቀደምት ሀገሮች ተርታ ያስቀመጠንን ሀይል ገንብተናል ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ የባህር ሀይል አቅምችንም በቀጣይ ማሳደግ ይገባናል ብለዋል፡፡

የኢፌድሪ ህገ -መንግስት መከላከያ ሰራዊቱ የብሄር፣ ብሄረሰቦች ነጸ ብራቅ፣ ከፖለቲካ ወገንተኝነት መጽዳት፣ ለሲቪል አስተዳደርና ለህገ -መንግስቱ ተገዥ መሆን፣ የሀገርን ሉዓላዊነት የማስከበር ተልዕኮ ያሰቀመጠ በመሆኑ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ህገ-መንገስታዊ ባህሪው ጠብቆ መዝለቅ አለበት ብለዋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊት ዋነኛ አላማበሲ ቪል አስተዳደሩ የሚቀመጡ ሀገራዊ ስጋቶችና የደህንነት ስጋቶችን በተቀመጠለት ትርጓሜ መሰረት በላቀ ብቃት ግዳጁን የማስፈጸም፣ የህዝብን ፍላጎቶችና ጥቅሞች ማስከበር እና የሀገር ክብርና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው፡፡


EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events