World News

Satenaw.com: በኢሃዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ ስራ አስፈጻሚ ያልሆኑ ነባር አመራሮች ተገኝተዋል

Posted by: Berhane Habtemariam

Date: Tuesday, 13 March 2018

አሁን እየተካሄደ በሚገኘው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ በተደጋጋሚ ጭቅጭቅ እየተፈጠረ ያልተስማሙበት ሁኔታ እንዳለ ታወቀ። ህወሓቶች የመጣው ይምጣ እያሉ ያስፈራራሉ። ኦህዴድን በተደጋጋሚ ይከሳሉ። ብአዴንንም አልፎ አልፎ ያነሳሉ። በህወሃቶች ዘንድ ኦሮሚያ ውስጥ ያለውን ምስቅልቅል ሁኔታ ኦህዴድን ተጠያቂ እያደረጉ ተናግረዋል። አባይ ጸሃዬ እና ደብረጺዮን በዋናነት ኦህዴድ ላይ ጣታቸውን ቀስረዋል።

ጌታቸው በስራ አስፈጻሚ ላይ ያለው ኢንፍሉወንስ እየቀነሰ ነው። ህወሃቶች አግሬሲቭ በሆነ መንገድ ለመሄድ የሚሞክሩት ነገር አልተመቸውም። ግን ምንም ማድረግ አልቻለም።

ደህዴን ህወሃት አንድ ላይ ሆነው ነው ሌሎቹን የሚያጠቁት፡፡

አቶ በረከት ስምዖን አሁን ጠቅላይ ሚኒስትር አያስፈልግም መጀመሪያ መከላከያ አገሪቱን ያረጋጋና ከዛ ብኋላ ይመረጣል እያለ ነው። በእሱ ስሌት መሰረት ወታደሩ እዛም እዛም የሚታዩትን ተቃውሞዎች ደብዛቸውን ካጠፋ ብኋላ ለምን ብሎ የሚጠይቅ ማንም ስለሌለ የዛንጊዜ የፈለግነው ጠቅላይ ሚኒስተር መሰየም እንችላለን ከሚል ነው፡፡ አሁን ባለበት ሁኔታ ግን ደብረፂዮን ከተመረጠ ብጥብጡ ይቀጥላል የሚል እምነት አለው። በረከት ዶ/ር አቢይ ጠቅላይ ሚኒስተር መሆን የለበትም የሚል አቋም ይዞ በስብሰባው እና ከስብሰባው በኋላ ባለው የእረፍት ጊዜ ሌሎችን ሎቢ ሲያደርግ ተስተውሏል። የተወሰኑ የህወሃት አባላት ደብረጺዮን ጠቅላይ ሚኒስተር ይሁን እያሉ ነው። ይህ የማይሆን ከሆነ ምክትሉ ከኛ ይሁን በማለት አቋማቸውን ገልጸዋል። ጌታቸው አሰፋ አሁን ደብረጺዮንን ጠቅላይ ሚኒስተር ማድረግ አሁን ካለው የፖለቲካ ሁኔታ አንጻር ፈጽሞ መሆን የሌለበት ነው በማለት አቋሙን ገልጿል። በህወሃት መካከል ቀጣይ ማን ጠቅላይ ሚኒስተር ይሁን በሚለው ጉዳይ ላይ ሙሉ በሙሉ አንድ አይነት አቋም እንደሌለ ታይቷል።

እስካሁ ባለው ሂደት 4ቱን የብሄራዊ ድርጅቶች ሊቀመናብርት ጠቅላይ ሚኒስተር የመሆን እድል አላቸው።

ወርቅነህ አሁን ሃገሪቷ ካለችበት ሁኔታ አንጻር አሰራሩ ተጥሶ እኔ ጠቅላይ ሚኒስተር መሆን አለብኝ የሚል ሃሳብ አንስቷል። ሌሎቹ ግን አልተቀበሉትም

ስብሰባው እንደቀጠለ ነው። ግምገማ የሚመስል ነገርም አለው፡፡ እስካሁን ያለውን የሃገሪቱ ሁኔታም እየገመገሙ ነው፡፡ በረከተ በስብሰባው ላይ ዋና ተዋናይ ሆኗል። ኦህዴዶች ላይም ትችት ከሚሰነዝሩ ሰዎች አንዱ ነው።

ስብሰባው በጭቅጭቅ ታጅቦ እንደቀጠለ ነው።


EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events