World News

Dahabshiil long banner 728x90
Eritrea for mobile viewing

Goolgule.com: 1. ዝሆን ላይ የሚጮህ እብድ ውሻ ብቻ ነው! ህወሓትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማው!, 2. ህወሓትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማው!

Posted by: Berhane Habtemariam

Date: Thursday, 08 February 2018

ዝሆን ላይ የሚጮህ እብድ ውሻ ብቻ ነው! ህወሓትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማው!

 

የአዘጋጆቹ ማስታወሻ፤ ባለፉት ዓመታት ከህወሓት እየኮበለሉ የወጡ የቀድሞ አባላት በርካታ ናቸው። እንዳንዳቸው የሚወጡበት ምክንያት ቢኖራቸውም ህወሃትን በማጋለጥና ማንነቱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በማሳወቅ የአቶ ገብረመድኅን አርአያን ያህል ታላቅ ሥራ የሠራና መስዋዕትነት የከፈለ አለ ለማለት ያስቸግራል። አብዛኛዎቹ የቀድሞው አባላቱ የህወሓትን ምሥጢራዊ አሠራር እና እጅግ አረመኔያዊ ግፍ፤ ኤፈርት በኢትዮጵያ ሐብት ላይ የፈጸመውንና እስካሁንም እየፈጸመ ያለውን የኢኮኖሚ ግፍ፣ ዝርፊያ፣ ሌብነት፣ … የመሳሰሉ ጉዳዮች በአደባባይ ከመናገር ሲቆጠቡ ተስተውለዋል። አንዳንዶቹም በህወሓት ከፍተኛ አመራር ላይ የነበሩ የቀድሞ አባላት ቢሆኑም፤ ኤፈርትም ሲያስተዳድሩ የቆዩ ቢሆኑም ስለጉዳዩ ሲጠየቁ የሚሰጡት ምላሽ አባይ ጸሐዬ ወይም ስብሃት ነጋ ከሚሰጡት ምላሽ ያልተለየ ሆኖ ተገኝቷል። አቶ ገብረመድኅን አርአያ “ዝሆን ላይ የሚጮህ እብድ ውሻ ብቻ ነው” በሚል ርዕስ ያቀናበሩትን ዳጎስ ያለ ሠነድ በድረገጻችን ላይ እንድናትመው በላኩልን መሠረት ከዛሬ ጀምሮ በተለያዩ ክፍሎች ከፋፍለን እናቀርባለን። የዝግጅት ክፍላችን ለአቶ ገብረመድኅን ምስጋናውን እያቀረበ ሌሎችም የህወሓት የቀድሞ አባላት ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱና በዚህ መልኩ ከሕዝብ ጋር እንዲታረቁ ሃሳብ እንሰጣለን። ያለ እውነት ዕርቅ የለም፤ ያለ ዕርቅ አብሮ መኖር የለም።


ዝሆን ላይ የሚጮህ እብድ ውሻ ብቻ ነው: ህወሓት እና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማ (ክፍል 1)

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከህፃናት እስክ አዋቂው (የወያኔው)፡ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር) ማንነት ካወቁ ብዙ ዓመታት አስቆጥረዋል። ህወሓት ከየት መጣ፣ አላማውስ ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎች የሕዝብ መነጋገሪያ ከሆነ አመታት ያስቆጠረ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ፤ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ደሙ አፍስሦ አጥንቱን ከስክሶ አንዲት ሉዓላዊት ኢትዮጵያ ያደረገ ህዝብ፤ በቋንቋ በሃይማኖት በዘር ያልተነጣጠለ ያልተከፋፈለ ህዝባዊ አንድነቱ ተፋቅሮ ተዋዶ በጋብቻ ተጋብቶ ፍቅርና ሰላም ገንብቶ ለስንት ሺህ ዘመናት ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ የመጣ ኢትዮጵያዊነት ጠብቆ፤ የመጣ ኩሩ ህዝብ ኢትዮጵያዊ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ፤ አረንጓዴ፤ ቢጫ፤ ቀይ ሰንደቅ ዓላማው ከስንት ሺህ ዘመናት ተረክቦ የማንነቱ መግለጫ አርማው፤ ተንከባክቦ ሲጠብቃት ጠብቆም ከትውልድ ወደ ትውልድ እያሸጋገር ሰንደቅ አላማችን የሃገርና የህዝብ ኩራት ደማቅ መለያችን ኩራታችን በመሆን የተስፋችን ሕይወት ሆና ኑራለች።

የውጭ ባእዳን ጠላቶች ኢትዮጵያን በመውረር ግብጽ፤ ሱዳን፤ ጣልያን፤ ሊብያ፤ ወ.ዘ.ተ. በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ለማጥቃትና ለመውረር ያደረጉት ብዙ ሙከራዎች በህዝብዊ አንድነትና አኩሪ ጀግንነት ኢትዮጵያዊ የመጡበት ጠላቶች ፊት ለፊት በጦር ሜዳ ተዋግቶ አሸንፎ ወራሪ ገድሎ ቀሪዉም ወደ መጣበት እንዲሸሽ በማድረግ የሚታወቅ የማይበገር ህዝብ ነው። ኢትዮጵያ በባእዳን ጠላቶች አትደፈርም ብሎ ዘብ የቆመው የኢትዮጵያ ህዝብ በታሪክ ማህደር ውስጥ በጠላት የማትደፈር ኢትዮጵያ፤ በዓለም ውስጥ ቀዳሚው ምዕራፍ ይዛለች።

ኢትዮጵያ ብዙ ጠላቶች አሏት፤ በመሬቱ ተፈጥራዊ አቀማመጥም በጠላቶችዋ የተከበበች ናት፤ቢሆንም ቅሉ ጠላቶቿ የኢትዮጵያ ህዝብ ጀግንነት በጦር የማይቀለበስ ህዝብ፤ ወራሪ ጠላት ቢመጣበትም በአንድነቱ ተሰባስቦ ለጠላት እሾህ ተዋጊ ደፋር ህዝብ መሆኑም በሚገባ ስለሚያውቁ፤ እንደ ድሮው ሠራዊታቸው አስከትለው ኢትዮጵያን ወረው የኢትዮጵያን አንድነት ለማናጋት፤ ችሎታና አቅም እንደሌላቸው በመገንዘብ፤ ከምዕራባውያን በተለይ እንግሊዝና አሜሪካ በመተባበር እነ ሱዳን፤ ግብጽ፤ ኢራቅ፤ ሶሪያ፤ ጣልያን፤ ሊብያ፤ ሶማሊያ፤ ወ.ዘ.ተ. ተባብረው ኢትዮጵያን የምናፈርሳት የምንበታትናት በራስዋ ዜጎች በቻ ነው፤ ይህም አስታጥቀን  በተለያዩ ዘዴዎች እየደገፍን የብሄር ጥያቄ፤ እስከ ነፃነት ጥያቄ የሚታገሉ መፍጠር ብቻ ነው ብለው የፖሊሲ አማራጭ አድርገው ባወጡት እቅድ፤ ማ.ገ.ብ.ት. ወይም ማሕበር ገስገስቲ ብሔረ ትግራይ የዚህ ፍሬ ሊሆን በቅቷል። ለዚሁም የመጀመሪያ ተማራኪው አረጋዊ በርሄ ሲሆን ጋሻ ጃግሬው ግደይ ዘርዓጽዮን አስከትሎ ነው።

ህወሓት የትጥቅ ትግሉን ከመጀመሩ በፊት ተዘጋጅቶ ወደ ትጥቅ ትግሉ የገባበት ምክንያት አሉት።

 1. የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት ለማፍረስ ብሎም ለመበታተን፤
 2. ሕዝቧ በቋንቋው ሃይማናትና ዘርን ማዕከል በማድረግ የኢትዮጵያን አንድነት በሚያዘጋጀው ፖሊሲ ለመከፋፈል ለመበታተን ከዚሁ መነሻ ህዝቡ በእርስበርስ ጦርነት እንዲተላለቅ አመቺ ነው ብሎ ስላመነበት፤
 3. ተሓህት (ተጋድሎ ሓርነት ሕዝቢ ትግራይ)–ህወሓት የተነሳለት ዓላማ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ አንድነት ከፈረስ ህዝቧም እርስበራሱ ወደ ማያባራው ጦርነትና መተላለቅ ከገባ ነፃ የሆነች ትግራይ ወይም የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ለመመስረት አመቺና ጥሩ ሁኔታ ይፈጥራል ብሎ ስለሚያምን፤
 4. የህ.ወ.ሓ.ት መስራችና አመራር በትልቁ በአቋም ደረጃ የያዙት ኢትዮጵያን ለመበታተን ህዝቡን መከፋፈል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የአማራው ህልውና በማያዳግም ሁኔታ መመታትና ከመሬት መጥፋትና መደምሰስ አለበት ብሎ የሚያምን በመሆኑ ነው፤

ከዚሁም ጎን ለጎን ህወሓት የተነሳበትና መጠቀስ ያለበት ሌላው ዓላማ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትናም ሆነ የአማራው ቋንቋ የሆነው አማርኛ አብሮ እንዲከስም ማድረግም አለብን፤ የኢትዮጵያን እስልምና ሃማኖትም አብሮ እንዲጠፋ ማድረግ አለብን ብሎ በማመን ነበር። ይህን በተግባር ስንጀምረው ኢትዮጵያዊነት የሚለው የአማራው ካባውም አብሮ ይከስማል ይጠፋል የሚል ነበር። (በህወሓት ፕሮግራም ቀዳሚ ምእራፍ በመስጠት ይህንን በጽሁፍ አስቀምጦታል።)

ህወሓት የትጥቅ ትግሉ እንደጀመረም በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኘው ሕዝብ በተለይ የትግራይ ሕብረተሰብ በግልጽ በማያሻማ መልኩ ከመነሻው ጀምሮ ተቃውሞታል። ህወሓት የተባለው ድርጅትና ፕሮግራሙን አልተቀበለውም ነበር። ከዚሁም የተነሳ የህ.ወ.ሓ.ት. አመራር ቂም በቀል በመያዝ በሰነዘሩት የጥቃት እርምጃ የትግራይ ሕብረተሰቡ በጣም ብዙ የሕይወት መስዋእትነት ከፍሏል፤ ሃብት ንብረቱ በህ.ወ.ሓ.ት. እየተዘረፈ ውርስ ሆነዋል ተብሎ የፈረሰው ቤት ከህ.ወ.ሓ.ት. ግድያ ያመለጠ ትንሽ ቢሆንም ወደ ጎንደር ሸዋ ጎጃም ተበትኗል።

በየካቲት ወር 1968 የተዘረጋው የህወሓት ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ሕዝብ ፕሮግራሙ በመጀመሪያ ተቃውሞ የገጠመው በትግራይ ሕዝብ ነበር። በዚሁም የተነሳ የትግራይ ሕዝብ ከፍተኛ የመስዋዕትነት እዳ ከፍሎበታል። በህወሓት አመራር ሕዝቡ ከየቤቱ ከተገኘበት በህወሓት የሃለዋ ወያኔ አባላት እየተያዘ ተረሸነ፣ ንብረቱ ተወረሰ፣ ቤቱ ፈረሰ፣ ሕፃናት አሳዳጊና ወላጅ በማጣት ተበታትነዋል። ፕሮግራሙ እውቅና አንሰጥም፣ እናንተ አሁን በትጥቅ ትግል ተሰማርተናል የምትሉትን ማንነታችሁን አናውቅም፤ በግልጽ የሚታየው በፕሮግራም አቋማችሁ ጸረ-ኢትዮጵያ ሉአላዊነት መነሳታችሁ ይናገራል። እኛ የትግራይ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያ ሃገራችን በተደጋጋሚ በግብጾች፣ ቱርኮች፣ የሱዳን ማህዲስቶች፣ በጣልያን ስትወረር ሃገራችንን ከጠላት ለመከላከል ሁላችን ኢትዮጵያውያ አማራ፣ ኦሮሞው፣ አፋሩ፣ አሩሲው፣ ወለጋው፣ ትግሬው፣ ወላይታው፣ ሲዳማው፣ ኦጋዴው፣ ከምባታው፣ ወ.ዘ.ተ. ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድም ሳይቀር በዘር በቋንቋ በሃይማኖት ሳንከፋፈ በአንድነት በኢትዮጵያዊነታችን ተባብረን ተደጋግፈን ሃገራችን ኢትዮጵያ በጠላት እንዳትወረር ደማችንን አፍሰን አጥንታችንን ከስክሰን ነፃነቷን የጠበቀች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን አስረክበናል። ተ.ሓ.ህ.ት. የምትሉት የምትናገራት  ነጻዋን በታሪኳ ገናናዋን ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባለቤት፣ የቀይ ባህር ንግሥት ኢትዮጵያ በመካድ ኢትዮጵያ የተፈጠረችው በዳግማዊ ምኒሊክ ታሪኳ ከ100 ዓመት ያነሰ ነው፤ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር እንዳልነበረች በየቦታው እየተዘዋወራችሁ ለትግራይ ህብረተሰብ ትሰብካላችሁ፤ አማራ የትግራይ ህዝብ ጠላት ደመኛ ጠላት የምትሉት ለኛ ጠላት ሳይሆን ወንድማችን  ሥጋችን ኢትዮጵያዊ ወንድማችን ነው እያለ የትግራ ሕዝብ ገና ከጅምሩ ይቃወም ነበር።

በመቀጠልም፤ ዛሬ ለትግራይ ሕዝብ ታግለን ትግራይን ነፃ አውጥተን የራሷን መንግሥት ትመሰርታለች የምትሉት የተሓህት-ህወሓት መሪዎች ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረበት ይህን በናንተ ፕሮግራም የተካተተውን ለአስተዳደሩ ለቅኝ ገዥነት እንዲመቸው ያስቀመጥው ሃገርና ሕዝብን ከፋፍሎት የነበረውን በጣልያን እቅድ የኢትዮጵያን አንድነት ለማጥፋትና ለመደምሰስ ነው። ታዲያስ እናንተ ከጣልያን የከፋችሁ እንጂ የተሻላችሁ አይደላችሁም፤ በማለቱና በግልጽ በመናገሩ ከሐምሌ 1968 ጀምሮ የህወሓት መሪዎች ሰፊ የመግደልና የማጥፋት እርምጃ  በትግራይ ሕብረተሰብ ላይ በማጠናከር ሕዝቡን አጠፉት፤ ሃብት ንብረቱ ወረሱት፤ ቤቱ አፈረሱት፤ አወደሙት።

በዚህ ወቅት የነበሩት ዋና አመራሮች፤

አረጋዊ በርሄ፣ የድርጅቱ ሊቀመንበርና ወታደራዊ አዛዥ፤

ግደይ ዘርአጽዮን፣ ም/ሊቀመንበር፤

አባይ ፀሃየ፣ የፖለቲካ መሪ፤

ስብሃት ነጋ፣ የአረጋዊ በርሄ አማካሪና የሃለዋ ወያነ ሃላፊ፤

ስዩም መስፍን እና ተጨማሪ ዋና ተባባሪ መለስ ዜናዊ ነበሩ።

እነዚህ ስድስቱ ታጋዮች በሕዝብ ላይ የሚወስዱትን እርምጃ ተመካክረው በአንድነት ተሰባስበው ይወስናሉ፣ በተግባርም ይፈጽማሉ። በ1969 የፈጸሙትን የግፍ ግፍ ለመጥቀስ፤ ጣልያን 1928ዓም ኢትዮጵያን ዳግም በወረረበት ጊዜ ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍል ክተት በማለት ሃገራቸውን ከወራሪ ጠላት ለመከላከል በሞላው ሃገራችን በተለያዩ የጦርነት አውድማ ተሰልፈው ወራሪውን ጠላት በአምስት ዓመት የአርበኞች ታጋድሎ ተሸንፎ ጓዙን ሳይጠቀልል በውርደትና በሃፍረት ተሸንፎ ወደመጣበት ሃገሩ ጣልያን እንደሸሸ ከገድላዊ ታሪካችን ተምረናል። የትግራይ ሕዝብ ከወንድሞቹ ኢትዮጵያውያን ጎን ተሰልፎ ለሃገር ሉዓላዊነትና ክብር ሲል መስዋእትነት ከከፈሉት ኢትዮጵያውያን አንዱ ነው። የተሓህት-ህወሓት መሪዎች ይህ የሃገር ክብር የተቀደሰ ጀግንነት አልተቀበሉትም። ለምን የትግራይ ሕዝብ ጸረ-ጣልያን ሆኖ ተሰለፈ በማለት የተናደዱት በአረጋዊ በርሄ የሚመሩ የተሓህት-ህወሓት መሪዎች አርበኞች አዛውንቶችን ከየቤታቸው በመልቀም ከያሉበት በማሰር በቀን ከእርሻ ቦታው ሌሊት ከቤቱ በማፈን ሃለዋ ወያነ አስገብተው ደብዛቸው በማጥፋት ማንነታቸው የውሃ ሽታ ሆኖ እንዲቀር አድርገዋል። ከነዚህ ከተገደሉት ብዛታቸው ባይታወቅም ለአብነት ከሚጠቀሱት መካከል፤

ፊታውራሪ በጹእ ወ/ጊዮርጊስ፤ የ82 ዓመት አዛውንት፣

ደጃዝማች ዘገየ አዛውንት ከነልጆቻቸው፣ ባቡ ዘገየ፣

ፊታውራሪ እምብዛ፣

ፊታውራሪ አጽብሃ፣

አስር አለቃ ገብረሥላሴ፣ አስር አለቃ ገብረዝጊ አለማየሁ እነዚህ ለአብነት ይበቃሉ።

እነዚህ የኢትዮጵያ አርበኞች ከያሉበት እየተያዙ የተገደሉት ከጣልያን ጋር ለምን ጦርነት ገጠማችሁ ተብለው እንጂ አዛውንቶቹ ያጠፉት አንድም ጥፋት የለም። ይህ ሲሆን እውነት ተሓህት-ህወሓት ለትግራይ ሕዝብ የቆሞ ነው? መልሱ፣ አይደለም ነው። ተሓህት-ህወሓት በፀረ-ኢትዮጵያ ባእዳን የተመሰረተ ድርጅት ነው። ለስልጣን ያበቁትም እነሱ ናቸው። ተሓህት-ህወሓት በትግራይ ሕዝብ ላይ የፈጸመው ግፍ እጅግ ዘግናኝ ስለሆነ ሌላው ቀርቶ ፈዳያን ወይም አትፍቶ ጠፊ አሸባሪ (terrorist) ቡድን በማቋቋም በየአውራጃ ያፈሰሰው ደም የትናንት ትዝታ ነው። የትግራይ ሕዝብ በተሓህት-ህወሓት ንብረቱ ተዘረፈ፣ መሬቱ ተነጠቀ፣ ቤቱ ፈረሰ፣ ለችግርና መከራ ተዳረግ፣ ተገደለ፣ ተሰደደ።

ለዚህ ዋና ተጠያቂዎቹ የህወሓት አመራር፣

አረጋዊ በርሄ፣

ግደይ ዘርአጽዮን፣

አባይ ፀሃየ፣

ስብሃት ነጋ፣

ስዩም መስፍን እና መለስ ዜናዊ ናቸው።

እነዚህም ቢሆኑ ተከታትለው የመጡ፤

ስየ አብርሃ፣

አውአሎም ወልዱ፣

ገብሩ አስራት፣

ዘርአይ አስገዶም፣

ጻድቃን ገብረተንሳይ፣

አስፍሃ ሃጎስ፣

አርከበ እቁባይ፣

ተወልደ ወ/ማርያም ናቸው። እነዚህ ደግሞ በሕብረተሰቡ ውስጥ ግድያ በመፈጸም እና ሕዝቡ ጥሮ ግሮ ያፈራውን ሃብት ንብረት ለህ.ወ.ሓ.ት ውርስ ተደርጓል በማለት በመዝረፍ ተባባሪና አስተባባሪ በመሆን በትግራይ ሕዝብ ወንጀል ፈጽመዋል። በታጋዩ ላይ በፈጸሙት ወንጀል ተጠያቂ ናቸው። በፈፀሙት አሰቃቂ ተግባራቸው በወንጀሉ ይጠየቃሉ። በተለየ ደግሞ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በተመለከተ ከላይ የተጠቀሱት ዋና መሪዎች የኢትዮጵያን አንድነት፣ ሉአላዊነት፣ መሬት አሳልፎ ለሱዳን በመሸጥ የወያኔ አመራር ቀዳሚ ተግባራቸው አደርገው ሲንቀሳቀሱ፣ እነዚህ የተጠቀሱት የማ/ኮሚቴ አባላት ተባባሪ በመሆን በኢትዮጵያና ሕዝቧ ላይ በርካታ የካሃዲነት ተግባራት ሲፈጽሙ የቆዩ ናቸው። የኤርትራን መገንጠልም ተባብረው ከነአረጋዊ በርሄ ጋር በመወገን ኤርትራን በማስገንጠል በሃገር ላይ ጉዳት አድርሰዋል። ለጊዜያዊ ጥቅም ብለው ከሱዳን መንግሥት በጀነራል ጃፋር ኒሜሪ (የሱዳን ፕሬዚዳንት ከመሆኑ በፊት በወቅቱ የነበረው የገዳሪፍ ገዥ) በ1975ዓም መስከረም ወር ከላይ የተጠቀሱ የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች እና የሱዳን ባለሥልጣናት በቋጩት ውል መሰረት የኢትዮጵያ ለምና ታሪካዊ መሬት በጸረ ኢትዮጵያዊነት የተነሱት የወያኔ መሪዎች አሳልፈው ለባእድ ሃገር ለጊዜዊ ጥቅም ሽጠዋል።

ይህም ምንም ህዝባዊ ውክልና ሳይኖራቸው ትግራይን ለማስገንጠል የተነሱ ከሃዲ ባንዳዎች፤ ዛሬ ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው ቅኝ ገዢ ወያኔ ህወሓት ለሱዳን ለመስጠት ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ። በዚሁስ የኢትዮጵያ ህዝብስ የሚወዳት የታሪክ ባለቤት ሃገሩ እየተሸራረፈች  ለባዕድ ሃገር ለሱዳን እየተሸጠች ባለችበት ጊዜ ምን እያለ ነው? የህ.ወ.ሓ.ት. አመራር ድሮ የነበሩ አሁንም ያሉ የኢትዮጵያን ሉዓላዊንት የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በዓለምአቀፍ የተከበረ ወሰን በወያኔ ባንዳ መሪዎች ለባእድ አሳልፎ መስጠት ከባድ ክህደት ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ህዝብ ሃገርና ህዝብ አሳልፎ መሸጥ ተፈጽሞበታል። ወያኔው ህ.ወ.ሓ.ት. ኢትዮጵያና ህዝቧን አጠፋለሁ በማለት ከደደቢት በረሃ ይዞት በመጣ ጸረ ኢትዮጵያ አቋሙ ሥልጣን ከያዘበት ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛቱ ውስጥ ከተቆጣጠረ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያወደመ ያፈረሰ ስርዓት ነው።

በህ.ወ.ሓ.ት. የፖለቲካ ወይም የፖሊሲ ልዩነት ተፈጥሮ ወይም ታይቶ አያውቅም፤ ህወሓት የሚከተለው ፖሊሲ ያው ነች፤ ፀረ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ ፀረ ህዝብ ከፋፋይነት፤ ፀረ-ዲሞክራሲ ነው፤ አሁንም በሥልጣን ያሉትን ጨምረን አንድም የራእይ ልዩነት ያለው ግለሰብ አመራር የነበረው የለም። ችግራቸው የሥልጣን ሽኩቻ ነው፤ ይህም ገና ከትግሉ መነሻ ጀምሮ በማያቋርጥ እስከ አሁኑ ጊዜ በግልጽ የሚታየው ነው። በአሁኑ ጊዜ አረጋዊ በርሄም ሆነ ሌሎቹ የተባረሩ የሚናገሩት ለኢትዮጵያ ህዝብን ለማታለል፤ በትግሉ ጊዜ ብዙ ልዩነት ነበረን ሲሉ ይደመጣሉ፤ ልዩነታችሁ ምን ነበር ተብለው ቢጠየቁ ግን መልስ የላቸውም። በተለይ አረጋዊ በርሄ ከድርጅቱ እስከ ተባረረ ሓምሌ ወር 1977ዓ.ም. በዋናነት፣ በበላይነት ሲመራው የነበረ እርሱ ነው፤ ፕሮግራሙን ተንከባክቦ ያቆየው እሱ ነው፤ የሚወጡ አዳዲስ ፖሊሲ በሱ ነው የተፈጸመው፤ በድርጅቱ ውስጥ አንድም አመራር የአረጋዊ በርሄ ሃሳብ የሚቃወም የለም፤ ሁሉ በእጁ ስለሆነም ዛሬ የሚናገረው ውሸት መሆኑ መታወቅ አለበት። ይህ ሁሉ የሚዘባርቀው፤ህ.ወ.ሓ.ት. ወንጀለኛ ድርጅት ነው በዘር ማጥፋት ወንጀል ይጠየቃል፤ ለወልቃይት ጠገዴ በጉልበቱ በመሪነት፤ እንዲሁም የሰሜን ወሎ ወደ ትግራይ በማካለል የመሬት መስፋፋትና ወረራ የፈጸመው እሱ ስለሆነ ከተጠያቂነት ለማምለጥ ባፈሰሰው የንፁሃን ዜጎች ደም ተጠያቂነት ለመሸሽ፤ በፈጠረው ዘዴ ህዝብ መታለል የለበትም።

አረጋዊ በርሄ በህወሓት ወስጥ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ የመጣበት ማህበረ ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ (ማገበት) ከተመሰረተበት እለት መስከረም 1967 ጀምሮ ተሓህት-ህወሓት የትጥቅ ትግሉን ከጀመረበት የካቲት 11፣ 1967 አንስቶ እስከ 1977 መጨረሻ ህወሓትን የሚዘውረው የነበረ  በዚሁ ፀረ-ኢትዮጵያ አንድነትና ፀረ-ሕዝብ ግለሰብ ነበር። በድርጅቱ የሚፈጸሙ ጉዳዮች የሱን ይሁንታ ማግኘት አለባቸው እሱ ካልፈቀደ ደግሞ ይሰረዛል።

አረጋዊ በርሄ ገና ትግሉ ሳይጀመር የድርጅቱን ፕሮግራም በዋና ሃላፊነት ያዘጋጀ ነው። ይህ ፕሮግራምነው ዛሬ ኢትዮጵያ እያፈረሰ እየበወዘ ሃገራችን ኢትዮጵያ በማትወጣው ችግር  ዳርጓት ያለው። የሰሜን ጎንደር ግዛቶችን አማራው የሚኖርበት ለብዙ ሺህ ዓመታት የአማራ መሬት ከዘር እስከ ዘር ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገር የመጣው የአማራው ባህልና ማንነት እየጠበቀ የመጣው የትግራይ መሬት በሚል አጉል የመስፋፋት ዘይቤ አማራውን ዘሩ በማጥፋት ያለቀው በህ.ወ.ሓ.ት. አመራር ታሪክ ዘግቦታል። ለዚሁ የሰው እልቂት ዘር ማጥፋት ተጠያቂው የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ከ1967 ዓ.ም. እስከ ዛሬዋ እለት ያሉትን አመራር ተጠያቂ ናቸው። ነብሱን አይማረውና ባለቀንዱ የባንዳ ዘር መለስ ዜናዊ እና ሌሎች የሞቱም በወንጀሉ ይጠየቃሉ ማለት ነው። ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ወልቃይት፣ ቃፍታ፣ ሁመራ፣ ህ.ወ.ሓ.ት በፕሮግራሙ ውስጥ (የእጅ ጽሁፉ የአቶ አረጋዊ በርሄ ነው) ከሰሜን ወሎም ራያና ቆቦ፣ ወልዲያ፣ አፍላ ደራ ወዘተ አጠቃላይ አለውሃ ምላሽ ተብለው የሚታወቁት የወሎ ግዛት ወደ ትግራይ አጠቃሎ ካርታውን ያዘጋጀው፣ መልክአ ምድሩን የለወጠው አሁን በትግራይ ክልል የተጠቃለሉት በአረጋዊ በርሄ የተዘጋጀው ነው። ይህን ለማረጋገጥ መቅድም  በሚለው (v) ቁጥር ነው (ገጽ 5) እንመልከት።

ህወሓት ትግሉን እንደጀመረ የቅድሚያ ትኩረት የሰጠው ሰሜን ጎንደርን ነበር። ይህንን የሰሜን ጎንደር ለም መሬት ለመያዝና ወሮ ወደ ትግራይ ለማጠቃለለ በወቅቱ መጠሪያው ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተሓህት) አስቀድሞ በመዘጋጀት ከነዚህም የሚታዩት ከነበሩት ተጨባጭ ሁኔታዎች፤ (ጊዜው ከ1969 ዓ.ም መጀመሪያ ጀምሮ ነው)፤

 • የዚህ ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት አባላት ሰርገው በመግባት በየቦታው የሚኖሩትን አማራ ታላላቅ ሰዎች የቦታው ታሪካዊ ጥናት የሚያውቁ፤ በህዝቡ ተቀባይነት ያላቸው፤ተናግረው ህብረተሰቡ የሚቀበላቸው ጥናት በማካሄድ፤
 • የታጠቁ ሰዎች ብዛታቸውም ሆነ ስሜታቸውን ማጥናት፣ ያላቸውን ሃብትና ንብረት የአካባቢውን ኗሪ ብዛትም ጭምር ማጥናት፣ ይህ የትግራይ መሬት ነው ቢባሉ የሚያስከትሉት ችግር ማወቅ ማጥናት በተናጠል ማነጋገር ወ.ዘ.ተ. የሚሉትን ተሸክመው መንቀሳቀስ ተጀመረ፤
 • ይህንን የሰሜን ጎንደር ለም መሬት በጉልበትና በሃይል ለመውረር በአማራው ላይ ከባድ ጥቃት መፈጸም ግዴታ መሆኑ አስቀድሞ ተይዞ የትግራይን ሕዝብ ድጋፍ የሚፈልጉ የተሓህት አመራር በወቅቱ የነበሩ አመራር፣ አረጋዊ በርሄ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፍን፣ ግደይ ዘርአጽዮን፣ በአራቱ መአዘን ተበታትነው አማራ የትግራይ ሕዝብ ጠላት መሆኑን፣ የትግራይን መሬት ነጥቀው የትግራይን ሕዝብ ለችግርና መከራ የደረጉት ደመኛ ጠላቶችህ ሲሆኑ የነጠቁህን መሬትህ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ቃፍታ፣ ሁመራ፣ እንዲሁም በሰሜን ወሎ ከአለ ውሃ ምላሽ የተነጠቅነውን መሬታችንን ለማስመለስ የትግራይ ሕዝብ የፈጠርከው መሪ ድርጅትህ ተሓህት ድጋፍህን እና እርዳታህን እንፈልጋለን፣ እያሉ ሕዝብ እየሰበሰቡ ተቆርቋሪ በመምሰል እያለቀሱ የትግራይን ሕዝብ አስተሳሰብ ለመቀየር ከፍጠኛ እንቅስቃሴ አደረጉ። ቢሆንም ከትግራይ ሕዝብ ያገኙት መልስ የሚከተሉት ነበሩ።
 • አማራ ጠላታችሁ ነው የምትሉን ከእውነት የራቀ ነው። አማራ የትግራይ ሕዝብ ጠላት አይደለም፣ ሆኖም አያውቅም። በአንድነት ሁነን ኢትዮጵያን ከብዙ የውጭ ወራሪ ሃይል አድነናል ተከላክለናልም። በዚህም አማራና ትግሬው ኢትዮጵያዊ ማተባችን በጋብቻና በባህል የተሳሰረ ሕዝብ ነው። ስለዚህ አማራ የኛ ወገን ትግሬውም የአማራ ወገን ነው።ልዩነት ጥላቻ ቅራኔ የለንም አንድ ኢትዮጵያዊ ህዝብ ነን። ለወደፊቱ አይኖርም፤ አብረን እንኖራለን ።
 • ስለመሬቱ የምትናገሩት የትግራይ አልነበረም፤ ሆኖም አያውቅም። ስለሆነም የሰሜን ጎንደርና የሰሜን ወሎ የትግራይ መሬት አልነበረም፤ አሁንም አይደለም፤ ከትግራይ የተነጠቀ መሬት የለም። የራሳቸው መሬት ነው። የኛ የትግራይ አይደለም፣ አልነበረም። የትግራይ ሕዝብ በተናገረው እውነተኛ ሃሳቡ ቀጠለ። ከሃቀኛ ሃሳቡ ፍንክች ባለማለቱ የወያኔው አመራር ግራ ተጋባ ጸረ ትግራይ ህዝብም መንቀሳቀስ ተጀመረ፤
 • ስለ ተሓህት የትግራይ ሕዝብ ድርጅት ነው የምትሉት፣ የታጠቀ ሃይል የትግራይ ሕዝብ ድርጅት አይደለም፣ አናውቀውም፤ የራሳችሁ የናንተው ነው፤ የትግራይ ሕዝብ ይህንን ድርጅት ከየት እንደመጣ፣ ማን እንደፈጠረው የምናውቀው ነገር የለም፣ እውቅናም አንሰጥም፣ በማለት የማያወላውል መልስ አግኝተው ራሳቸውን ደፉ። በዚሁ ጊዜ ግንቦት ወር 1968ዓ.ም አካባቢ የትግራይ ህዝብን በተናጠል ለማጥቃት የተነሱት እነ አረጋዊ በርሄ፤ እነዚህ የተህሓት መሪዎች በትግራይ ሕዝብ ላይ አጸፋዊ ጥቃት በተቀናጀ መልኩ እንዲፈጸም ፖሊት ቢሮ፣ ማለትም በአረጋዊ በርሄ በሚመራው ግደይ ዘርአጽዮን፣ አባይ ፀሃየ፣ ስብሃት ነጋ፣ ስዩም መስፍን ተሰብስበው በሶስት እቅዶች ላይ ተሰማሙ፡
  • የከተማውንና የገጠር ሕዝብ ግንኙነት በሕዝቡ ሙሉ የጥናት ክትትል እያደረጉ ለግደይ ዘርአጽዮን አንዲያቀርቡ፤
  • የከተማውን ኗሪ የሚያጠቃ ፈዳያን “አጥፍቶ ጠፊ” አሸባሪ (terrorist) እንዲቋቋም፣ ስልጠናም እንዲያገኝ፣
  • ክብሪት የሚባል ጉጅሌ ገዳይና አፋኝ ቡድን እንዲቋቋም ተስማሙ። ይህ ጉጅሌ 12 ሰዎች የያዘ ሲሆን 7 ታጋዮች 5 ሚሊሽያ ሆኖ ተመሰረተ። የሚሊሽያው ዋና ተግባሩ መንገድ መሪ የሚፈለጉ ሰዎች ጠቁሞ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 3 የተጠቀሱትን ተግባራዊ እንዲሆኑ ተደረገ ።

በዚሁም ጊዜ  የነበሩት (06) ሓለዋ ወያነ፣ ቀደም ሲል የነበሩት ሰፋፊ ቤቶች እየተፈለጉ ነዋሪውን በማባረር ሲጠቀሙበት የነበሩትን በመተው ሰው በማይንቀሳቀበት ቦታ ተመረጡ፤ እነዚህም፤ ሽራሮ ወረዳ ሸሸቢት ቡምበት፣ ሱር፣ ወርዲ፣ ፃኢና አዲበቅሎ፣ ዓዴት፣ ዓዲ ጨጓር፣ በለሳ፣ ማይሃምቶና ባኽላ ሳምረ ናቸው። እነዚህን ሰፋፊ መግደያ ቦታዎች በአዲስ ዘዴ  በመስራት ተገነቡ። ይህም በግደይ ዘርአጽዮን መሪነት ከመሬት በታች 2 ሜትር ተቆፍረው እንዲሰሩ ከ200 ያላነስ እስረኛ የሚታሰርበት አንዲት ጠባብ መስኮት ያላት ሆኖ እንዲሰራ  በህ.ወ.ሓ.ቱ. ም/ሊቀመንበር ግደይ ዘርዓጽዮን ትእዛዝ መሰረት ከላይ በተጠቀሱ ቦታዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ተሰሩ። በትእዛዙ መሰረትም ሥራው ተጠናቀቀ። ይህ ጊዜ 1969ዓም መጨረሻ ነበር። የትግራይ ህዝብም ያለቀው የተገደለው በእነዚህ ቦታ ነው። ዛፍ በእርጥቡ እየተቆረጠ ተፈልጦ በእሳት በማቀጣጠል በጠባብዋ መስኮት በመልቀቅ የሰው ልጅ ፍጡር በጢሱ ታፍኖ ያለቀው አምላክ ይቁጠረው። የዚች አሰቃቂ ግድያም የግደይ ዘርዓጽዮን ብልሃት ናት። ለዚህ ክፉ የወንጀል ግድያም ይጠየቅበታል። ይህ ክፉ አገዳደል በተለይ በአማራው ህዝብ በስፋት የወያኔ መሪዎች በመጠቀማቸው የአማራውን ዘር አጥፍተዋል።

ክብሪት ተንቀሳቃሹ ጉጅሌ፡ ሆኖ ሲመሰርቱ፣ በ16 ጉጅሌ ነበር የተመሰረተው። የእነዚህ መሪዎችም በአርከበ እቁባይ፣ አሰፋ ማሞ፣ ሰአረ መኮንን፣ ሽሻይ በላይ (አመደ)፣ ታደሰ ጋውናይ፣ ወዘተ በመደራጀት በየገጠሩና በየከተማው አካባቢ እንዲሁም በየወረዳው በሌሊት ተሽለኩልከው በመግባት የሚፈልጉትን ሰው ወንድ፤ ሴት አፍነው በማውጣት ሃለዋ ወያነ ታስሮ/ታስራ በማስገባት እዛው እርምጃ ይወሰድበታል። (06) ሓለዋ ወያኔ የገባ ሰው ሁሉ በሕይወት ወደ ቤቱ አይመለስም። ሕዝብ የሚገደልበት መግደያ የሲኦል ገሃነብ ነው። በገጠሩ ነዋሪ በፈለጉት ሰአት በመሄድ ኗሪውን ሰላማዊ ዜጋ ኢትዮጵያዊ በማሰር ንብረቱን በመውረስ እየታሰረ ሃለዋ ወያኔ ገብቶ ይገደላል፤ ቤት ፈረሰ ልጆች ካለ አባትና እናት ተበታትነው ቀሩ፤ በጅምላ ጉድጓድ በጥይት ይረሸናሉ። መግደያ ጉድጓዳቸውም የሚቆፉራት ራሳቸው ተገዳዮቹ ናቸው።

ፈዳያን የተባለው በብስራት አማረ የሚመራው አጥፍቶ ጠፊ ሽብርተኛው ክፍል የተመሰረተው ከሓምሌ ወር 1969 ዓ.ም ጀምሮ በየከተማው አውራጃዎች አድዋ፤ መቀሌ፤ ሽሬ፤ አክሱም አዲግራት፤ ውቅሮ ሁለት አውላእሎ፤ ወዘተ እንዲሁም በወረዳዎች እየገባ በመቶዎች የሚቆጠሩ በየከተማውና በወረዳው በቀን ተመሳስሎ በመግባት በየመጠጥ ቤቱ ሻይ ቤት በማኸል ከተማ  ቤተ ክርስትያን ውስጥ አጋጣሚው ሲመችለት አፍኖ በማስወጣት የስንቱን ንጹሃን ዜጎች በጠራራ ቀን ደማቸው ፈሰሰ፤ ተገደሉ።

በዚሁ ፈዳያን የተሰማሩ አመራር፣ አረጋዊ በርሄ፣ አድዋ፣ አባይ ፀሃየ፣ አክሱም፣ አርከበ እቁባይ፣ አዲግራት፣ ስዩም መስፍን፣ ውቅሮ፣ ስብሃት ነጋ፣ ተምቤን፣ በሽብርተኝነት ተሰማርተው ሰዎች ገድለዋል። ግደይ ዘርአጽዮን እንትጮ፣ ሰለክላካ፣ ራማ፤ ኩሓ የስንት ሰው ሕይወት ከግብረአበሮቹ ፈዳያን ጋር አጠፋ። ይህ የወያኔ ጥቃት ከተሓህት-ህወሓት በትግራይ ሕዝብ የማጥቃት  ዘመቻው በተለያየ መልኩ ቀጠለ። ግደይ ዘርዓጽዮን አክሱም ከተማ የጉጅሌ መሪ በመሆን ሁለት የአብርሃ ወአፅብሃ ሁለተኛ መለስተኛ ደረጃ አስተማሪዎች መምህር አበበ፤ መምህር መላኩ መንገሻ የተባሉ አስተማሪዎች በመግደሉ ተወገዘ። ተመልሶ አክሱም የሚገባበት እድልም የለውም። ይህ ሰው በተፈጠረው ውግዘት ለወላጆቹም ግደይ በፈጸመው ወንጀል ቁርሸው ትቶ አልፈዋል። የግደይ ጣጣ በዙ ነው፤ ግደይ ዘርዓጽዮን ሱር ሓለዋ ወያኔ ታስረው የነብሩት ብዙዎቹ አማራ ቀሪዎቹ የትግራይ ሰዎች በየታሰሩበት ከመሬት በታች የጉድጓድ እስር ቤቶች የዓየ እንጨት በማቀጣጠል እንጨቱ እየተቀጣጣለ በትንሽዋ ቀዳዳ መስኮት የገባው ጢስ እዛው ጉድጓዱ የታሰረው ንፁሃን ዜጎች በጢሱ ታፍነው ሲያልቁ የተመለከተው በህዝብ ግኙኝነት ክፍል የሚሰራ ታጋይ ዓለም ወልደገሪማ የሚባለው የቀ.ኃ.ሥ. ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት ኢኮኖሚክስ ተማሪ የነበረው፤ ግደይ ዘርዓጽዮንን ኢሰብአዊና አረመኔያዊ ግድያ ህዝቡ ላይ ሲፈጽም፣ ሕዝቡን ሲፈጅ በዓይኑ በማየቱ በድርጊቱ አወገዘው። ግደይ ግን ቂሙን ቋጥሮ ቆይቶ፤ በስራ ምክንያት ዓለም ወልደገሪማ ወደ ሪጅን 2 የሚሄድ መሆኑ ስላወቀ ዓዴት የሚገኘ ሓለዋ ወያኔ 06 ለብስራት አማረ ደብዳቤ ፅፎ፤ የደብዳቤዋ የውስጥ ይዘትዋ፤ ዓለም ወልደገሪማ ይህች ደብዳቤ እንደሰጠ ተቀብለህ ወዲውኑ እሰረው፣ ከዛ ረሽነህ ግደለው የምትል ነበረች። ዓለም ወልደገሪማም የመገደያውን የፍርድ ወረቀት ተሽክሞ ሂዶ አዲበቅሎ ዓዴት ወዲያውኑ በጥይት ተደብድቦ ተገደለ። ይህች የግፍ ግድያ ብዙም ሳትቆይ እጃቸው ለደርግ የሰጡ የአክሱም ልጆች ታጋይ ነበር፤ ዓለም ወልደገሪማ በግደይ ዘርዓጽዮን እንደተገደለ ለወላጅ አባቱ ነገሯቸው። ምህረይ (ቄስ) ወልደገሪማም የአክሱም ህዝበ አዳም በልጃቸው በህ.ወ.ሓ.ት. መሪው የተፈጸመው ግፍ በየቤተክርስትያኑ ከማጋለጥ ቀጠሉበት። የዓለም ወልደገሪማ ወንድሞች ደማቸው ለመበቀል፤ ጊዜያቸው እየጠበቁ ናቸው። ወደ ዋናው ርዕሳችን ስንመለስ። (በቀጣይ እናትማለን)።

ገብረመድህን አርአያ፣ ፐርዝ፣ አውስትራሊያ

*********************************************************

ህወሓትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማው! -2

 

የአዘጋጆቹ ማስታወሻ፤ ባለፉት ዓመታት ከህወሓት እየኮበለሉ የወጡ የቀድሞ አባላት በርካታ ናቸው። እንዳንዳቸው የሚወጡበት ምክንያት ቢኖራቸውም ህወሃትን በማጋለጥና ማንነቱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በማሳወቅ የአቶ ገብረመድኅን አርአያን ያህል ታላቅ ሥራ የሠራና መስዋዕትነት የከፈለ አለ ለማለት ያስቸግራል። አብዛኛዎቹ የቀድሞው አባላቱ የህወሓትን ምሥጢራዊ አሠራር እና እጅግ አረመኔያዊ ግፍ፤ ኤፈርት በኢትዮጵያ ሐብት ላይ የፈጸመውንና እስካሁንም እየፈጸመ ያለውን የኢኮኖሚ ግፍ፣ ዝርፊያ፣ ሌብነት፣ … የመሳሰሉ ጉዳዮች በአደባባይ ከመናገር ሲቆጠቡ ተስተውለዋል። አንዳንዶቹም በህወሓት ከፍተኛ አመራር ላይ የነበሩ የቀድሞ አባላት ቢሆኑም፤ ኤፈርትም ሲያስተዳድሩ የቆዩ ቢሆኑም ስለጉዳዩ ሲጠየቁ የሚሰጡት ምላሽ አባይ ጸሐዬ ወይም ስብሃት ነጋ ከሚሰጡት ምላሽ ያልተለየ ሆኖ ተገኝቷል። አቶ ገብረመድኅን አርአያ “ዝሆን ላይ የሚጮህ እብድ ውሻ ብቻ ነው” በሚል ርዕስ ያቀናበሩትን ዳጎስ ያለ ሠነድ በድረገጻችን ላይ እንድናትመው በላኩልን መሠረት ከጥቂት ወራት በፊት ክፍል አንድን አቅርበን ነበር። (ይህንን ዕትም ለመረዳት ክፍል አንድን ማንበብ አስፈላጊ በመሆኑ እዚህ ላይ በመጫን እንዲያነቡ እናሳስባለን)። ስማቸው የግድ መገለጽ ስላለበት ስማቸው የወጣ ለዚህ ጽሁፍ ምላሽ መስጠት ለሚፈልጉ በራችን ክፍት ነው። የዝግጅት ክፍላችን ለአቶ ገብረመድኅን ምስጋናውን እያቀረበ ሌሎችም የህወሓት የቀድሞ አባላት ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱና በዚህ መልኩ ከሕዝብ ጋር እንዲታረቁ ሃሳብ እንሰጣለን። ያለ እውነት ዕርቅ የለም፤ ያለ ዕርቅ አብሮ መኖር የለም።


ዝሆን ላይ የሚጮህ እብድ ውሻ ብቻ ነው!

ወያኔዎች በትግራይ ህዝብ የጥቃት ዘመቻ የከፈቱበት ምክንያት የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ እምነቱ ከፋፋይና ዘረኛው ወያኔ ፤ በእውቅና አለመቀበሉ ቀጥሎ ያለውን ዋና ምክንያቶች እንመልከት።

1. አማራ ደመኛ ጠላትህ ሲሉት አይደለም ወንድሜ ወገኔ ኢትዮጵያዊ ነው በማለቱ፣

2. ተሓህት የትግራይን ሕዝብ አይወክልም አናውቃችሁም በማለቱ፣

3. ተሓህት የነጠቀውን የሰሜን ጎንደርና የሰሜን ወሎ ለም መሬቶች አንቀበልም፣ የሰሜን ጎንደሩ የጎንደር ጠ/ግዛት ነው፣ የሰሜን ወሎ የወሎ ጠ/ግዛት ነው፣ ከትግራይ ግንኙነት የላቸውም፤ በጎንደር በኩል የሚያዋስነን ተከዜ ወንዝ ነው። በወሎ በኩል ማይጨው ችንኮማጂ ነው፤ ሲሆን በምን መልኩ ነው የትግራይ የሚሆነው በማለቱ፣ ከወንድሞቻችን ጥላቻና ቅራኔ አትፍጠሩብን ብሎ ጮሆ በመናገሩ፤ ሸዋዊ የትግራይ አማራ ተብሎ የግድያ ኖህ የወረደበት።

4. የተሓህትን ፕሮግራም አንቀበልም 1ኛ ትግራይ የኢትዮጵያ የታሪክ አስኳል የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ የሚመካ ነው፤ ትግራይ የኢትዮጵያ አካል ግዛት እንጂ ቅኝ ተገዢ አይደለችም፤ አማራው ኢትዮጵያዊ፤ ትግራይም ኢትዮጵያዊ ፤ ምንም ልዩነት የለንም በማለት ጮሆ በመናገሩ።

5. በጣሊያን ጊዜ የተዋጉና በኢትዮጵያዊነታቸው የሚኮሩ የትግራይ ልጆችን የህ.ወ.ሓ.ት.ን መርህ የሚያጨናግፉ ናቸው ብሎ በማሰብ ህ.ወ.ሓ.ት አጥፍትዋቸዋል። በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የታሪክ አዋቂዎች አዛውንት ሊቃውንት የአምስት ዓመት ከወራሪው ጣልያን የተዋጉ አርበኞች በመብራት እየፈለገ የወያኔው መሪዎች የገደልዋችው ያጠፍዋችው፤ ተገድለውም ሃብት ንብረታቸው ህ.ወ.ሓ.ት ወርሶታል። እነዚህ የሃገርና የህዝብ አለኝታዋች ሙሉ በሙሉ በትግሉ ጊዜ አጠፉዋቸው፤ ገደልዋቸው። ዛሬ ስለ ትግራይም ሆነ አጠቃላይ ስለ ነበረው ጥንታዊ ታሪክ በትግራይ ውስጥ የሚያውቅ ተፈልጎ አንድም አይገኝም።

ትግራይ በ17ቱ የህ.ወ.ሓ.ት. የትግሉ ዘመን ወድማለች። የታሪክ አዋቂ በኢትዮጵያዊነቱ የሚቆረቆር በትግሉ ዘመን ተመልሶ እንዳያንሰራራ ተመልሶ እንዳይፈጠር አድርገው በመምታት አጥፍተዉታል። በጣም የሚያስገርም ሁኔታም የተፈፀመው በወልቃይት፤ ጠለምት፤ ጠገዴ ብቻ በሰሜን ጎንደር አማራው በተመሳሳይ ሁኔታ አዛውንቶች እየተፈለጉ በስውር እየታፈኑ፣ የት እንደገቡ የማይታወቁ ማን ተያዘ ማን ተገደለ የሚለው በግልጽ ለማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም ብዙ የሰሜን ጎንደር አዋቂ ሽማግሌዎች የውሃ ሽታ ሆነው የቀሩ አሉ፤ ይህን ለማወቅ የሚችሉት የየአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው። የታሪክ አዋቂ ሲጠፋም ተተኪው ትውልድ ይቸገራል። የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች ይህ እንደፖሊያሳቸው የሚጠቀሙበትም የቆየው ታሪክ ለማጥፋትና ለማክሰም ነው።

በእነዚህ ንጹሃን የትግራይ እና የሰሜን ጎንደር ኢትዮጵያውያን የፈሰሰሰው ደም ተጠያቂው ማነው? ማነውስ ሃላፊነቱ የሚቀበለው? ምንስ አጥፍተው ነው? ወደ ትግራይ ስንመለስ፤ የተናገሩት እውነት ነው፤ ትግራይ የአማራው ቅኝ ተገዢ አይደለችም፤ ሰሜን ጎንደር፤ ወልቃይት፤ ጠገዴ ጠለምት፤ ቃፍታ (ሰቲት) ሁመራ  የሰሜን ወሎን መሬቶች የትግራይ አይደሉም፤ አልነበሩም፤ ይህም ታሪክ የሚያውቀው ሃቅ ነው። የትግራይ ህዝብ ምን አጠፋ ህ.ወ.ሓ.ት የገደለው የረሸነው ያጠፋው። ማንኛውም ህዝብ አስተዋይና አርቆም ሃሳቢ እንደሆነ ሁሉ የትግራይ ህዝብም ከዚሁ ተነስቶ ነበር እውነቱን የተናገረው። ይህ ህ.ወ.ሓ.ት. የጀመረው በትግራይ ህብረተሰብ ማጥቃትና መግደል የንጹሃን ዜጎችን ደም በከንቱ የፈሰሰው ይህ ደም አሁንም በእግዚአብሔር ፊት እየጮኸ ይኖራል። መሬትና ሰማይ የፈጠረ ጌታም ፍርዱን ይሰጣል፤ የማይቀር ነው። የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች የአማራው ጎንደሬው ለምና ሰፊ መሬት በሕገ ወጥ በጉልበት ለመንጠቅ፤ የአማራው ደም የንጹሁን ኢትዮጵያውያን ዜጎች ደማቸው በትውልድ መንደራቸው እንደጎርፍ ካለምንም ጥፋትና ሃጥያት ፈሰዋል�#4709;ረተሰብ የጀመሩትን ጥቃት እንደቀጠለ ሁኖ የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት፤ ሰቲት ሁመራን፤ በጉልበትና በማንአለብኝነት በካርታቸው የተካተተው በፕሮግራማቸው ውስጥ የትግራይ መሬት ነው በማለት ሰፊዉን የጎንደር ክፍለ ሃገር መሬት የሰሜን ወሎ መሬት በማካተት (ፀሃፊና አዘጋጅ አረጋዊ በርሄ ነው) ሕገ ወጥ የለም ሰፊ መሬት ወረራ ፈጽመዋል። ይህን ወረራ ለማስፈጸም የተካሄድ ቅድመ ዝግጅት በሰሜን ቤገምድር (ሰሜን ጎንደር)፤ ንን ዘለለው የተባለው ነገር ግን አካባቢውን የማያውቀው በስመ ተወላጅ በአባቱ በኩል ተወላጅ የሆነውን ታጋይና በህዝብ ግኑኝነት ክፍል የተመደበ በሱ የሚመራ ቡድን በወልቃይት፤ በጠገዴ፤ በጠለምት ጥናት እንዲያካሂድ በ1969 ዓ.ም ውስጥ ተላከ። ይህ ከሃዲ ግለሰብ ከግለሰው እስከ ቡድን ከቡድን በየበአላቱ እሁድ ወ.ዘ.ተ. በየቤተክርስትያኑ እየተንቀሳቀሰ ወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት፤ ቃፍታ ሁመራ የትግራይ መሬት መሆኑ የሰሜን ጎንደር ህዝብም ሁሉ ትግራዋይ መሆኑ የታሪክ ሃቅነት በጎደለው ለማሳመን ባካሄደው መፍጨርጨር ሳይሳካለት በሙሉ የሰሜን ጎንደር ህዝብ በልበ ሙሉነት ወድቅ አደረገው። በግልጽም እናንተ ወራሪ የጣልያን አሽከሮች ውላጅ ናችሁ በማለት አሸማቀቃችው። ይህ የጎንደር ግዛት በማንም ያልተደፈረ በእናንተ ከሃዲዎች እይፈፈርም ብሎ ህዝቡ በግልጽ የተናገረበት ጊዜም ነው። ከዚያም ተዋርዶ ተደብዶቦ፤ ህዝቡም ወደ ማንም ቤት ዝር እንዳይሉ በማስጠንቀቅ በርሃብ ጠውልገው ወደመጡበት እንዲመለሱ አደረጋቸው። ነገር ግን መኮንን ዘለለውና ቡድኑ ሲያደርጉት የነበረው ሤራ ህዝቡ ሁሉ ቢቃወምም ትልልቅ ሰዎች የታሪክ አዋቂዎች የበሰሉ ጠንካራ ሰዎች በብዛት በሚስጢር እየመዘገቡ፤ እነዚህ ሰዎች በሂወት ካሉ ነገሩ አይሳካም በማለት በድብቅ ስማቸው ወደ ወያኔ መሪዎች በየእለቱ በማስተላለፍ ለክፉ ሞት ዳረጉዋቸው።

የህ.ወ.ሓ.ት . መሪዎች አሁን የገጠማቸው ክሽፈትና ወርደት አጸፋውን ለመመለስ ዝግጅታቸውአሰቀመጡ። ቀደም በማለት በትግራይ ሕብረተሰብ የአፈና ዘዴ በመጠቀም አነስተኛ ሀይል አፋኝ ጉጅሌ በማደራጀት ክፉና አረመኔው ጨካኞች አፋኝ ቡድን ሶስት አቅጥጫ ተሰማራ። ይህ ጊዜም በ1969 ዓ.ም. ወደ መጨረሻው አካባቢ  በሶስት አቅጣጫ በማሰማራት

 1. ወልቃይት፣
 2. ጠለምት፣
 3. ጠገዴ

ውስጥ ሲገቡ ጉጅሌያቸውን ይዘው በሶስቱ ቦታዎች ተሰማርተው ቀደም ሲል ከመኮነን ዘለለው የነበሩ የህዝብ ግኑኝነት መሪነት በድብቅ በዘዴ የተቃወሙት የሰሜን ጎንደር አማሮች አንድ በአንድ በተናጠል እያፈኑ ሰውን በመልቀም ያፈኑዋቸውን ሓለዋ ወያኔ በማስገባት ወንድ፣ ሴት ሳይሉ ገደሉዋቸው። ሃብት ንብረታቸውም  እየተወረሰ ዝርፍያው ቀጠለ ቀስ በቀስም የጀመሩት ጥቃት እየተስፋፋ ሄደ።

ተ.ሓ.ህ.ት. ለ1ኛው ጉባኤ ይዘጋጅም ስለነበረ 1ኛ ጉባኤው የካቲት 5 ቀን 1971 ዓ.ም. ዓዲ ዳዕሮ አካባቢ ማይ አባይ በተባለው ቦታ ተካሂዶ የአመራር ቦታ ለውጥም ተደረገ። በዚሁ መሰረት እንደሚከተለው ተደላደሉ።በዚሁ ጉባኤ የተመረጡ አመራሮች አምስቱ የቆዩ ፖሊት ቢሮ (ሥራ አስፈጻሚ) እንዳሉ ተመልሰው ሥልጣናቸው ሲይዙ ቀሪዎቹም ዝርዝር የሚከተለው ነው፤

1ኛ. አረጋዊ በርሄ፤ ወታደራዊ አዛዥ፤ ፖሊት ቢሮ

2ኛ. ስብሃት ነጋ፤ የህ.ወ.ሓት ሊቀ መንበር፤ ፖሊት ቢሮ

3ኛ. ግደይ ዘራፅዮን፤ የህ.ወ.ሓ.ት ም/ሊቀመንበር፤ ፖሊት ቢሮ

4ኛ. አባይ ፀሃየ፤ የፕሮፓጋንዳ ክፍል ዋና ሃላፊ፤ ፖሊት ቢሮ

5ኛ. ስዩም መስፍን፤ የውጭ ጉዳይ ዋና ሃላፊ፤ ፖሊት ቢሮ

6ኛ. ገብሩ አስራት፤ ማዕከላዊ  ኮሚቴ

7ኛ. መለስ ዜናዊ፤ የፕሮፓጋንዳ ጽ/ቤት ም/ሃላፊ፤ ማዕከላዊ  ኮሚቴ

8ኛ. አስፍሃ ሓጎስ፤፤ ማዕከላዊ  ኮሚቴ

9ኛ. አርከበ (ዮሓንስ) እቁባይ፤ ማዕከላዊ  ኮሚቴ

10ኛ. ፃድቃን ገብረተንሳይ፤ ማዕከላዊ  ኮሚቴ

11ኛ. ስየ አብርሃ፤ ማዕከላዊ  ኮሚቴ

12ኛ. አታክልት ቀፀላ፤ ማዕከላዊ  ኮሚቴ፤ ግንቦት ወር 1971 ዓ.ም በስብሃት ነጋና በአባይ ፀሃየ እንዲሁም በመለስ ዜናዊ  የተገደለ። ገዳይ ሳሞራ (መሓመድ) የኑስ በሲሞኖቭ ባልር መነጽር ጠመንጃ።

13ኛ. ዘርአይ አስገዶም፤ ማዕከላዊ  ኮሚቴ

14ኛ. አውዓሎም ወልዱ፤ ማዕከላዊ  ኮሚቴ

15ኛ. ተወልደ ወ/ማርያም፤ ማዕከላዊ  ኮሚቴ ብዙም ሳይቆይ በህመም ምክንያት ሱዳን ሂዶ 1975 ዓ.ም የተመለሰ ነው።

የነዚህን ስም ዝርዝር ያስቀመጥኩበት ካለ ምክንያት አይደለም፤ በተለይ በአማራው ላይ የዘር ማፅዳት ከባድ ወንጀል በመፈጸማቸው ነው። አማራው ያፈራው ሃብት ንብረት ወ.ዘ.ተ. መርፌም ሳትቀር ለህ.ወ.ሓ.ት. ውርስ እንዲሆን ብለው የህዝብ ሃብት ንብረት የዘረፉ፤ የአማራው ህዝብ  የገደሉ፤ የግድያውም ቀንደኛ ተባባሪዎችና ፈፃሚዎች የነበሩ ናቸው። እነዚህ ተሰባስበው ነው በንጹሃን ዜጎች ላይ እልቂትና ሰቆቃ እያደረሱ የመጡ፤ ከአምስቱ ፖሊት ቢሮ ስድስተኛው መለስ ዜናዊ አብረው ሊጠየቁና ሊከሰሱ የሚገባቸውናቸው። የሰሜን ጎንደር ህዝብ በአረጋዊ በርሄ የሚመራው የህ.ወ.ሓ.ት ሰራዊት ቀሪው አራቱ ፖሊት ቢሮ በየቦታው ተሰማርተው ትዕዛዝና አመራር በመስጠት ማእከላዊ ኮሚቴውም ይበልጥ በዘር ማጥፋቱ ተሰማርተው የነበሩ፤

1. አዋአሎም ወልዱ፤ 2. ስየ አብርሃ፤ 3. መለስ ዜናዊ ከስየ አብርሃ ተደራቢ በመሆን፤ 4. ዘራይ አስገዶም፤ 5. ፃድቃን ገብረ ተንሳይ፤ 6. ገብሩ አስራት፤ 7. አርከብ እቁባይ፤ 8. አስፍሃ ሓጎስ ናቸው።

ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ደግሞ በየተዋጊው ሰራዊት ተመድበው ትእዛዝ በመስጠት በአማራው ላይ ጥቃት በመክፈት የአማራ ዘር ማጥፋት ከባድ እርምጃ በመውሰድ፤ አማራው ሊቋቋመው በማይችል ሁኔታ ሰላማዊው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ዘሩን ለማጥፋት ያለው የሌው ሃይላቸው አጠናክረው ግፍ የፈጸሙ የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች፤ 1. አረጋዊ በርሄ፤  2. ግደይ ዘራጽዮን፤ 3. ስብሃት ነጋ፤ 4. አባይ ጸሃየ፤ 5. ሥዩም መስፍን፤ 6. መለስ ዜናዊ፤ በሰሜን ጎንደር አማራ በትንሹ ከ1969ዓ.ም. የጀመረው ጥቃት በክፉ መልኩ ተጠናክሮ ከታህሣስ ወር 1972 ዓ. ም. የተጀመረው የአማራ ዘር ማጥፋት ዘመቻ እስከ 1977 ዓ .ም. በቀጠለበት ጊዜ በዋናነት የዘር ማጥፋት ወንጀሉን በአማራው ላይ የፈጸሙ ዋናዎቹ እነዚህ ናቸው። በዚሁ የወያኔ ጥቃት ከ2 ሚልዮን በላይ ነብሰ ጡር አራስ ህፃናት ሽማግሌዎች ወጣቶች ወንድ ሴት ልዩነት በሌለው በወያኔ እጅ ተገድለዋል። አገዳደሉም በተለያየ ስልትና ዘዴ ተፈጽሞባቸውል። ቀሪው ለስደት ተዳርጓል፤ የመጣ ይምጣ ከቤቴ ወጥቸ አልንገላታም ያለም አለ።

ከማ.ገ.ብ.ት ምስረታ እስከ የካቲት ወር 1967 ዓ.ም. የማገብት ሊቀ መንበር፤ ቀጥሎም በትግሉ ሜዳ ከየካቲት ወር 11ቀን 1967 ዓ.ም እስከ የካቲት ወር 1971 ዓ፣ም ሊቀ መንበርና ወታደራዊ አዛዥ የነበረው አረጋዊ በርሄ ነው። በምን ምክንያት ሊቀ መንበርነቱን ለቀቀ ለሚል ጥያቄ አጭር መልስ።

አረጋዊ በርሄ፤ ስብሃት ነጋ፤ መለስ ዜናዊ ስብሰባዎች በሚካሄዱባቸው ጊዜያት ገና ወደ ጉባኤው ሳይገባ ሶስቱ እየተደበቁ የሚያደርጉት ስምምነት ነበራቸው። ድርጅቱን በሞኖፖል ለመቆጣጠር የሚያስችላቸው ሶስቱን የተስማሙበት አረጋዊ ሊቀመንበርነቱን ለስብሃት ነጋ ሊሰጠው አረጋዊ በወታደራዊ አዛዥነቱ እንዲወሰን መለስ ዜናዊ የማርክሲስት ሌኒንስት፤ በሌኒናዊ መርሀግብር የካድሬዎች አሰልጣኝና አደራጅ ኮሚሽን እንዲሆን በተስማሙት መሰረት ነበር። 1ኛው ጉባኤው ተካሂዶ 15 አመራር ተመርጠው የሥራ አስፈፃሚው ምርጫ በሚመረጥበት ጊዜ በሁሉም ተሰብሳቢ በሙሉ ድምጽ የተመረጠው አረጋዊ በርሄ የህ.ወ.ሓ.ት. ሊቀመንበር ቢመረጥም ብሞትም አልቀበልም ስብሃት ነጋ ነው ብቁ ለሱ ይስጠው ብሎ አንገቴን ለካራ አለ። የተመረጡ  አመራር ስብሃት ለዚሁ ብቃት የለውም እባክህ ተቀበለን ቢሉቱም በፍፁም አልቀበልም በማለቱ ለስብሃት ነጋ ሰጡት። መለስ የተሰጠውን ቦታ አደላድሎ ያዘ፤ አረጋዊም ድሮም የራሱ የነበረው ወታደራዊ አዛዥነቱን ያዘ፤ቀሪው በየቦታው ተደላደለ። በአጭሩ ነው የገለፅኩት እንጂ ብዙ ታሪክ አለው፤ ለወደፊቱ ራሱን በቻለ ርዕስ ለህዝብ አሳውቃለሁ፤ ለአሁኑ ይህ ይበቃል። አረጋዊ በርሄ ደግሞ በታጋዩ እንዲጠላ እንዲናቅ ያደረገው ዋናው ይህ ነው። ስብሃት ነጋ ማለት አእምሮው የዞሮበት ደፍድፍ ደንቆሮ ገዳይ ጨካኝ አውሬ ነው።

አረጋዊ በርሄ

ህወሓት ከኢህአፓ ጦርነት ስለአጋጠመው ደፍሮ ሰሜን ጎንደር ሕዝብ ለማጥቃት ሁኔታውና ጊዜው አልፈቀደለትም ነበር። ከኢህአፓ ጋር በተካሄደው ጦርነት ኢህአፓ ጥቃት ደርሶበት ሰሜን ጎንደርን ለቆ በመውጣቱ ምክንያት በአረጋዊ በርሄ ወታደራዊ አዛዥ የሚመራው የወያኔ ሰራዊት ጠቅላላ ወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት(‘ሰሜን ጎንደር’) በመውረር ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጸመ። ስብሃት ነጋ፣ ግደይ ዘርአጽዮን፣ አባይ ፀህየ፣ ስየ አብርሃ፣ ስዩም መስፍን መለስ ዜናዊ የወያኔውን ሰራዊት ተከፋፍለው በመያዝ ሰሜን ጎንደር የንጹሃን ዜጎች አማራ የሬሳ ክምር መሬት አደረጉት። እነዚህ ሁሉ አመራር በቀጥታ ትእዛዝ የሚቀበሉት፣ የሚንቀሳቀሱት፣ ጥቃት የሚፈጽሙበት ቦታዎች ከአረጋዊ በርሄ በሚሰጣቸው መመሪያ ነበር። በዚሁ ጊዜም ተጨማሪ (06) ሃለዋ ወያነ በስፋት እንዲዘጋጁ አመራሩ ስላመነበት በምክትል ሊቀመንበሩ ግደይ ዘርአጽዮን ቁጥጥር ተጨማሪ ሃለዋ ወያን እንዲዘጋጅ በታዘዘው መሠረት በርሱ ኃላፊነት ተጨማሪ ከመሬት በታች 12 ሜትር ጥልቀት ትንሽ ጠባብ መስኮት 150 እስከ 200 እስረኞች የሚይዙ ሆነው እንዲሰሩ ወስኖ የነበሩትም እንዲሰፉ አድርጎ አሰራው። የሚሰሩበትም ቦታዎቹም፣ ግህነብ (ቃሌማ)፣ ፍየል ውሃ፣ ባኽላ ሳምረ፣ ሱር እስር ቤት ሲሆን፣ እንዲሰፋ የተደረጉባቸው ቦታዎች ደግሞ አዲ በቅሎ፣ ወርዒን ፃኢ ጨምሮ በስፋትና በብዛት ከመሬት በታች ሃለዋ ወያኔ ተሰሩ። በዚሁ ጊዜ አማራዎች፣ ሽማግሌ፣ ወጣት፣ ህፃን፣ ሴት፣ ወንድ ሳይለዩ ወደነዚህ ሃለዋ ወያኔ እየታፈሱ ታጋዙ። እዛው እንደገቡም በተለያዩ የጭካኔ ግፍ ተገደሉ። በጢስ እየታፈኑ የሞቱት አማራዎች ብዙ ናቸው። በጅምላ ጉድጓድ በጥይት እየተደበደበ ያለቀው አማራ ብዙ ነው። ወህኒ ቤት ውስጥ በገባው ተላላፊ በሽታ ምክንያት ኮሌራን ሌላ በሽታዎች በመተላለፍ ሕዝብ አለቀ። በቶርቸር፣ በመርዝ፣  በእሳት፣ የጋለ ብረት ወደ ሆዱ በመክተት አሰቃይተው ንጹህ ኢትዮጵያዊ ዜጋ አጠፉት። የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች በአማራው ያልፈጸሙት ግፍ የለም ። እነዚህ አረመኔ ግፈኞች በአንድ ህዝብ ላይ አማራ ጠላታች ብለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ አካሂደዋል። የሞተም በሂወት ያሉትና የሞቱትም እንደነ መለስ ዜናዊ በከባድ ወንጀል

1. ዘር በማጥፋት፤

2. ሃገር ለባእዳን መሸጥ (ለሱዳን)፤

3. የመሬት ወረራ መፈጸም (ሰሜን ጎንደር፤ ሰሜን ወሎ) የታላቅዋን ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ የትግራይ መንግሥት ማስፋት የሌላው ክፍለ ሃገር ለምና ሰፊ መሬት በመንጠቅ  የህዝቡ ማንነት፣ ባህሉን፣ ወጉን፣ ፀረ ዲሞክራሲ፣ ፀረ ህልውና፣ በመሆነ መልኩ የፈጸሙት ከባድ የወንጀል ተግባር ነው። አሁንም ህ.ወ.ሓ.ት በዚሁ እየቀጠለበት ሲሆን እንዲያውም በከፋ መልኩ በግማሹ ወደ ትግራይ በማካለል ግማሹ ለሱዳን መንግሥት በመሸጥ በአማራው ላይ የሚፈጸመው ግፍ አባብሶታል።

በአማራው እየተፈጸመ ያለው ግፍ አማራን ብቻ የሚመለክት አይደለም፤ የሁሉ ኢትዮጵያዊ ጥቃት ነው፤ አማራው ዘሩ ሲጠፋ አማራው ብቻ አይደለም ዘሩ የሚጠፋው ያለ ሁሉ ኢትዮጵያው ነው ዘሩ የሚጠፋ ያለው፤ የጎንደር ለምና ሰፊ መሬት ለሱዳን እየተሸጠ ያለው የጎንደር ብቻ አይደለም የሁሉ ኢትዮጵያዊ ነው፤ የኢትዮጵያ የታሪክ ቦታዎች፤ ቴዎድሮስ በመቅደላ፤ ዮሃንስ በመተማ እምቢ ለጠላት ብለው የተሰዉበት መሬት ወያኔ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ለሆነው የሱዳን መንግሥት አሳልፎ መሸጥ ታሪካችንም አሳልፎ እየሸጠው ይገኛል።ስለሆነም የጎንደር ህዝባዊ ትግል የሁሉ ኢትዮጵያዊ ትግልም ነው። የምንታገልበትም ጊዜው አሁን ነው። ጎንደርና ትግራይ፤ ጎንደርና ሲዳሞ፤ ጎንደርና ሓረር፤ ጎንደርና አፋር፤ ጎንደርና ኦጋዴን፤ ጎንደርና ጋምቤላ፤ ወ.ዘ.ተ ምንም ልዩነት የለንም! ሁላችን የኢትዮጵያ ልጆች ነን፤ ኢትዮጵያ የሁላችን ሃገር መመክያ ናት፤ ሁላችን ሃገራችን ከወያኔው ፋሽሽት ስርአት ከሃዲ ባንዳ ተባብረን ኢትዮጵያን እናድን።

የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት፤ ሌላውም አማራ በህ.ወ.ሓ.ት.፤ የወረደበት ከባድ የጥቃት ዘመቻ በዝምታ ወይም እየተገደለ አልቀረም። ተወልዶ ያደገበት የትውልድ ቦታው ስለሆነ መግቢያው መውጫው ስለሚያውቀው፤መሳሪያ ያለው ታጥቆ፤ የሌለው በቤቱ ያገኘው ጎራዴ፤ ፋስ፤ ገጀራ፤ ወ.ዘ.ተ. እናቶች ወጣት ሴቶች ወንድም ሳይቀር በርበሬ በመያዝ ወያኔን በሚገባ በሁሉ አቅማቸው ገድለዉታል፤ አጥቅተዋል። በአንዳንድ ቦታዎችም ሙሉ በሙሉ ለማለት የሚቻለው የወያኔ ሠራዊት ደምሠዉታል። የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በታሪክ የተመሰከረለት አርበኛ ተዋጊ፤ ሙሉ ወኔ ያለው ህዝብ ከመሆኑ የተነሳ ከ1972 ዓ.ም. ጀምሮ ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. እንደፈለገው ኢትዮጵያን እንዲያፈርስ ህዝብ ሊበታትን በደም ሊያቃባ እድል አልሰጠዉም። የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት ህዝብ ቆለኛም ደገኛም ህዝብ ነው። የመሬቱ ነፋስ የተስማማ ከመሆኑ የተነሳ ወያኔ ይህ ህዝብ በቀላሉ ሊያጠቃው ጠራርጎ ሊያባርረው አልቻለም። ሌላው አማራ ቶሎ ብሎ በመቻኮል ወደ በቀል አርምጃ አይሸጋገርም፤ ከተነሳ ግን ወደ ኋላ አይታጠፍም፤ በአማራ ጥርስ የገባ ጠላት የመጨረሻ እጣ ፈንታው ውድቀት ምርኮ ናት። አማራ ለኢትዮጵያ አንድነት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ዋልታና ማገር፤ የሃገሩ ድንበር በመጠበቅ፤የእስልምና፤ የክርስትና ሃይማናት ባለቤት በመሆኑም እነዚህ ሁሉ ተዳምረው በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ህዝብ፤በባንዴራው አረንጓዴ፤ ብጫ፤ ቀይ የሚኮራ ህዝብ ነው። ይህ አማራ የሚባለው ህዝብ ዘሩን ካልጠፋ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር በአፄ ምኒሊክ የተፈጠረች ናት፤ ከተፈጠረችም ከ100 ዓመት ያነሰ ዕድሜ ያላት ታሪክ-አልባ ሃገር ናት፤ ከዓለም ካርታ ለመፋቅ ይቻላል፤ ብሎ የተነሳው የባእዳን ቅጥረኛ ባንዳ ወያኔ፤ የአማራው ወኔ ጥንካሬ ጀግንነት አይቶታል፤ አሁን እያየው ነው።

ህ.ወ.ሓ.ት አማራውን ሲያጠቃ አብሮም የተጠቃው የኢትዮጵያ ተዋህዶ ክርስትናም ነው። ቀደም ሲል በ1971 ዓም በአክሱም አውራጃ እንዳባ ጴንጦሌን (ብዙ አክሱማዊም እንዳባ ፍሬሚናጦስ) እያለ የሚጠራው ከአክሱም ከተማ የ5 ኪሎሜትር ርቀት ያለው አካባቢው የሚጠራበት ስም ደግሞ እንዳየሱስ በተባለው ቦታ ጥንታዊው ገዳም እንዳ አባ ጴንጦለን ብዙ ጥንታዊ ቅርሶች፤ ብዙ ጥንታዊ የታሪክ መጻህፍት፤ ጥንታዊ የብራና ጽሁፎች የሚገኝበት ገዳም ለመዝረፍ ህ.ወ.ሓ.ት በሰነዘረው ጥቃት ሳይሳካለት ቀርቷል። ቀጥሎም በአድዋ ውስጥ የሚገኘው እንዳሥላሴ ገዳም ላይ ቢሞክርም አልተሳካለትም። ይህ ኦፐረሽን የተመራው በአረጋዊ በርሄ ነበር፤ቀጥሎ ወያኔ የዘመተው ወደ ዋልድባ ገዳም፤ በዚሁ ገዳም ተልእኮው ሙሉ ለሙሉ ተሳካለት፤ በህ.ወ..ሓ.ቱ ሊቀ መንበር ስብሃት ነጋና በህ.ወ.ሓ.ቱ ም/ሊቀመንበር ግደይ ዘራጽዮን መሪነት ዋልድባ ገዳም ሙሉ በሙሉ ተዘርፈዋል። ብዙ ብጹዓን ባህታውያን፤ ቀሳውስት፤ አባዎች ተገድለዋል፤ ታሪካዊ ቅርሶች መጻህፍት ብራናዎች ሃብቱ ንብረቱ ወ.ዘ.ተ. ተዘርፈዋል። አሁንም ዋልድባ ገዳም እየተጠቃ ይገኛል፤ ባለታሪክ ጥንታዊ ገዳም እየወደመ ለህልፈቱም ገደል አፋፍ ነው ያለው፤ ይህ ገዳም አማራን ብቻ አይመለከትም የሁሉ ኢትዮጵያዊነው፤ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይና ዋልድባ ገዳም በሚል ርእስ ለሁሉ ኢትዮጵያዊ ስለ አሰራጨሁት የዚሁ ቅዱስ ዋልድባ ገዳም በህ.ወ.ሓ.ት. የደረሰበትና እየደረሰበት ያለው ጥቃት በዝርዝር ስለፃፍኩት ጽሁፉ በየዌብ ሳይቱ ስለሚገኝ እዛው ፈልገን እንመልከት።

በአማራው የተፈጸመው አሰቃቂ ጥቃት ደግሞ ከሁሉ የከፋ በአርከበ እቁባይ፣ ዘርአይ አስገዶም፣ ሳሞራ የኑስ፣ ታደሰ ወረደ፣ ሃየሎም አርአያ ወዘተ የሚመሩ የገዳይ ቡድን ሕዝቡን እየሰበሰቡ በሳር ቤት ውስጥ በማስገብት ቤቱን በእሳት በማቃጠል ያለቅው ሰው ቁጥር ብዙ ነው። እኔ ራሴ ያየሁት አርከብ እቁባይ 12 ቤተሰቦችን ሰብስቦ በገዛ ቤታቸው፣ አባት፣ እናት፣ ልጆች፣ የተዳሩ ሴቶች ልጆቻቸውን ጨምሮ ከነህፃናቱ ሰብስቦ ሳር ቤት አዳራሽ አስገብቶና ቤቱን ዘግቶ እሳት ለቀቀባቸው። ሁሉም ቤተሰብ በእሳቱ አለቁ። በዚሁ በሰሜን ጎንደር የተካሄደው የዘር ማጥፋት ወንጀል በተጨማሪ ሁሉም ንብረታቸው ሃብታቸው፣ በሬ፣ ላም፣ ፍየል፣ በግ፣ አጋሰስ ጠቅላላ የቤት እንሣት ሁሉ በህወሓት ተዘርፈው ተወርሰው ተወሰደዋል።

ከ1972 ዓ.ም. ታህሳስ ወር ይህ ሁሉ ጥቃት የተጀመረው አጠቃላይ የጠገዴ፣ ጠለምት፣ ወልቃይት አማራ ዘሩ ሲጠፋ ቀሪው ደግሞ ወደ ሱዳን ተሰደደ፤ ጫካ ውስጥ ገብቶ ፀረ ወያኔ በሽምቅ ውጊያም የተሰማራ ጥቂት አልነበረም። ህዝብም ባገኘው መንገድ ሁሉ ወያኔን ከማጥቃት አላቆመም፤ የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት፤ ሴቶች በርበሬ በትንሽ ከረጢት ቋጥረው ከወገባቸው አትለይም በቤታቸው ውስጥም የተዘጋጀ አለ የወያኔ ታጋይ በመንገድ ሲገኙት አቁመው ለማነጋገር በመሰለ መልኩ ከያዝዋት በርበሬ ዘግነው በማውጣት አይኑ ላይ በመርጨት እዛው ሲደናበር መሣሪያ ማርከው ብዙ የወያኔ ታጋይ ገድለዋል። ወደ ቤታቸው የሚመጣ ታጋይም በርበሬ በውሃ በጥብጠው የሚበላ የሚጠጣ አቅርበው ደህና ነው ብሎ ሆዱን ሲሞላ፤ የበጠበጡት በርበሬ አይኑ ላይ በመድፋት የታጠቀው መሳሪያ ማርከው ታጋዩም በድምፅ አልባ መሳሪያ ይገድሉታ፤ በዚሁም ተገድሎ የጠፋ የወያኔ ታጋይ ብዙ ነው።

በ1973 ዓ.ም . በተለያየ መንገድ የተገደሉ ከማስታውሳቸው ውስጥ፤ በህዝብ ግንኙነት የነበሩት፤ አለማየሁ፤ብርሃነ፤ ፍስሃ፤ ገብረተንሳይ፤ ነጋሽ፤ አማረ፤ ደስታ የተባሉና ሌሎችም ብዙ ተገድለዋል። እነዚህን የጠቀስኩት ከማውቃቸው ነው። በወያኔ ታጋይ ሰራዊትም በተለያዩ መንገዶች በህዝቡ የተገደሉም ብዙ ናቸው ከማስታውሳቸው ለመጥቀስ ገብረ ሥላሴ፤ በላይ፤ ፍጹም፤ ካህሳይ፤ ነጋሽ፤ ገረግዚሄር፤ አባይ፤ አበበ፤ ጸጋይ፤ የሚባሉ ህዝቡን ለመግደል በቡድን በቡድን ተከፋፍለው ሲንቀሳቀሱ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብም በየጫካው  ተደብቆ በማድፈጥ የገደላቸው እነዚህን አስታውሳለሁ። የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት ህዝብ የሚቻለውን ሁሉ አቅሙ በፈቀደለት መጠን ህ.ወ.ሓ.ት. ወያኔን ከማጥቃት ባለው መሣሪያ እየተጠቀመ ወደ ኋላ ሳይል ጀግንነቱን ያስመሰከረና ያሳየ ህዝብ ነው። እኔ ባለኝ እምነት ይህ ኩሩ ጀግና ህዝብ ከወያኔ ፋሽሽት ቅኝ ገዢ አረመኔ ስርአት እየታገለ የመጣና ባለኝ እምነት መሠረት እውነትም የኢትዮጵያ መድህን ጠባቂም ነው። ተስፋ ሳይቆርጥ ከ1972 ዓ ም. አንስቶ እስከ ዛሬዋ ዕለት የማንነት ጥያቄው አድማሱን በማስፋት ወያኔ በማጥቃት ተሰማርቶ ይገኛል። በመሬቴ ላይ እሞታለሁ እንጂ ትወልድ ቦታየ አለቀም ያለው በ1969 ግንቦት ወር  የተጀመረው ጥቃት እስከ ዛሬ ድረስ ቀጥሏል። ይህ የሰሜን ጎንደር ህዝብ በወያኔ እየሞተ እየተገደለ ማንነቴን አሳልፌ አልሰጥም ብሎ 42 ዓመት ሙሉ ከተሓህት-ህወሓት ዘራችንም ብታጠፉ አንድ ሰወ እስኪቀር ማንነታችን አሳልፈን አንሰጥም እኛ አማራ ጎንደሬዎች እንጂ ትግሬዎች አይደለንም፤ ብሎ እስከ አሁን ድረስ በማንነቱ የማይደራደር ማንነቱን አሳልፎ የማይሰጥ ኩሩ ኢትዮጵያዊ አማራ ነው።

በምሬት እየታገለ የሚገኝ የጎንደሩ ህዝብ ከቀን ወደ ቀን ጥንካሬው በግልጽ እየታየ ነው። በየትም ቦታ የተገኘ አማራ እንዲገደል ህ.ወ.ሓ.ት. ያወጀው በ1969 ሲሆን፣ በትግራይ ውስጥ የሚኖሩ አማራዎችም ከየቦታው እየተለቀሙ እንዲገደሉ አምስቱ የተሓህት አመራሮች፣ አረጋዊ በርሄ፣ ሊቀመንበር፣ ግደይ ዘርአጽዮን፣ የድርጅቱ ም/ሊቀመንበር፣ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፍን፣ ስብሃት ነጋ አድርገዋል። ትግራይ የትግራዮች እንጂ የሌላው መጤ ቦታ አይደለችም፣ ስለሆነም ማንም የትግራይ ተወላጅ ያልሆነ ከትግራይ ይውጣ ተብሎ እንዲታወጅም ያደረጉት እነዚሁ ናቸው። በአዋጁ መሰረትም አማራው በነቂስ እየተፈለገ ተገደለ፣ እነዚህ ይህ ውሳኔ የተላለፈባቸው ከትግራይ ተጋብተው ልጆች ወልደው ያሳደጉም ናቸው፤ ያመለጠውም ሂወቱና ቤተሰቦቹን ይዞ የሸሸም ብዙ ነው። ይህ የተመለከተና ያየ የትግራይ ህዝብም ወያኔን አወገዘ፤ መሬታቸው ነው አይወጡም፤ ይህ የኢትዮጵያ ቦታ ነው፤ ማነው ወጪ ማነውስ አስወጪ፤ ከፈለጋቹህ ወያኔዎች ውጡ እያለ ከአማራው ወንድሙ ጋር ቆመ። በየቦታው ፀረ ወያኔ እንቅስቃሴ ተነሳ፤ ወያኔም በየቦታው ይህ እንቅስቃሴ የታዩባቸው ቦታዎችን በህዝብ ግንኙነት ክፍል በኩል በፀረ ወያኔ ፖሊሲ ተንቀሳቅሰዋል ያላቸውን የትግራይ ሰዎች አንድ በአንድ እየለቀመ ሓለዋ ወያነ በማስገባት ደብዛቸው አጠፋቸው፤ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።

ተሓህት-ህወሓት ይህን ሁሉ በሰሜን ጎንደር አማራው ኅብረተሰብ ላይ ይህን ሁሉ ግፍ ሲፈጽም እጃቸውን ለወያኔ የሰጡ የኢህአፓ አባላት የነበሩ፤ ታምራት ላይኔ፣ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ በረከት ስምኦን፣ ዮሴፍ ረታ፣ መለሰ ጥላሁን፣ ህላዊ ዮሴፍ፣ ታደሰ ካሳ፣ ሙሉአለም አበበ፣ ወዘተ ይገኙበታል። ከወያኔ ህወሓት ጋር በመተባባር የሰሜን ጎንደር፣ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት ወዘተ የቀድሞዎቹ ኢ.ህ.ዴ.ን. በህ.ወ.ሓ.ት. አምሳልና ቡራኬ ተጠፍጥፈው የተሰሩ ተላላኪዎች የዛሬዎቹ ብአዴን አካባቢው ለብዙ ጊዜ የቆዩበትና የሚመሩበት ስለነበሩ ሕዝቡን በነቂስ ስለሚያውቁት አካባቢ እየመሩ ለወያኔ ጥቃትና የዘር ማጥፋት ወንጀልም ተባባሪ ሆነዋል። ወያኔን እየመሩ የሰሜን ጎንደሬውን አማራ አጥቅተውታል። ስለሆነም በማራው ላይ የደረሰው የዘር ማጥፋት ወንጀል በተለያዩ የጥቃት ዘዴዎች በህወሓት የተፈጸመው እነዚህ የብአዴን አመራር ከህወሓት አመራር ጋር አብረው ተጠያቂ ናቸው።

በሕዝብ ላይ ለሚደርሰው ጥቃት፤ ሃብት ንብረት ዘረፋ፤ ለሚደርሰው ማንገላታት ሰላማዊ ዜጋው ተይዞ ለእስር የሚዳረገው በሕዝብ ግንኙነት በኩል ጥናትና ሪፖርት ነው። መኮንን ዘለለው ለመጀመሪያ ጊዜ በህ.ወ.ሓ.ት በኩል ወደ ወልቃይት ጠገዴ የተሰማራው እሱ ነበር፤ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ግን አልተቀበለውም። ሪፖርቱ ሲያስተላልፍም ሁሉም ፀረ ተ.ሓ.ህ.ት./ህ.ወ.ሓ.ት ናቸው በማለት ከነስም ዝርዝራቸው ለወያኔ ፖሊት ቢሮ (ከ100 በላይ ሰዎች ሴቶችም አሉበት) ቀስ በቀስ አንድ በአንድ ብስራት አማረ በሚመራው አፋኝ ቡድን ተለቅመው በቡምበትና ሱር ሓለዋ ወያነ ገብተው ጠፍተዋል፤ ንብረታቸውም ሙሉ በሙሉ በወያኔ ተዘርፎ ባዶ ቤት ቀርቶዋል። የዚህ ሁሉ ተጠያቂው ስንመለከት፣ መኮንን ዘለለው ነው። በዚህም ላይ የሚጠየቁ መረሳ ረዳ፣ አጽብሃ ሃይለማሪያም፣ ፀጋይ በርሄ (ሃለቃ)፣ መኮንን የአዲረመጽ ሕዝብ ግንኙነት፣ አርአያ ወርቅነህ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ቀሺ ታደሰ፣ መሃሪ ግብርገርግስ፤ ሃለቃ ታደለ አለምሰገድ፤ መብራት በየነ፤ ወዘተ ናቸው። እነዚህም አንኳር ተጠያቂ ናቸው።

ገብረመድህን አርአያ፣ ፐርዝ፣ አውስትራሊያ

በሚቀጥለው ዕትም “የህወሓት ፕሮግራም” በሚል ርዕስ ሃተታ እናቀርባለን።

Dm eri tv subscribe

HDRI Publishers: Book Release - ህያው ደብሪ A Book Hailed As A Game Changer in Eritrean Modern Poetry