World News

Goolgule.com: ፈትለወርቅን ማንገስ ያቃተው የስብሃት ቡድን የአዜብ ዕገዳ እንዲነሳ ሊቀበል ነው

Posted by: Berhane Habtemariam

Date: Thursday, 30 November 2017

ፈትለወርቅን ማንገስ ያቃተው የስብሃት ቡድን የአዜብ ዕገዳ እንዲነሳ ሊቀበል ነው

 

መቀሌ ላይ ሲሰዳደቡ የቆዩት የበረሃ ወንበዴዎች ደብረጽዮንን መሪያቸው አድርገው በመምረጥ የፈትለወርቅን ዋና መሪነት ውድቅ አድርገዋል። ይህ ለስብሃት ነጋ ሽንፈት የሆነው ክስተት በአዜብ ላይ የተጣለው ዕገዳ እንዲነሳ ወደመቀበል ሊገደድ ይችላል እየተባለ ነው። የኤፈርት ጉዳይ አሁንም አከራካሪ ሆኗል።

ከልክ ባለፈ ሁኔታ መቀሌ ላይ ሲወነጃጀሉና ሲሰዳደቡ የቆዩት የህወሓት የበረሃና የድህረ በረሃ ወንበዴዎች በመጨረሻ ላይ የስለላውን ማሽን ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን ዋና መሪያቸው አድርገው መርጠዋል። “ሞንጆሪኖ” በማለት ሳሞራ ዩኑስ ጣሊያናዊ ስም የሰጣት ፈትለወርቅ በነስብሃት ቡድን የዋናውን ቦታ እንድትይዝ ከፍተኛ ጥረት ቢደረግላትም “የመለስ ራዕይ” አስጠባቂ የሆነው ቡድን አልረታም በማለት ውድቅ አድርጓታል። በውጤቱም በዓለምአቀፍ የመረጃ ቋት በአሸባሪነት የተመዘገበው የህወሓት ቡድን ምክትል ሆና ተመርጣለች።

የዛሬ 12ዓመት አካባቢ “ሎንዶን ለትምህርት በነበርኩበት ጊዜ በኮምፒውተር መጻፍ አልችልም ነበር፤ የሚቀርቡ ወረቀቶችን በእጄ ጽፌ ነበር የማቀርበው” በማለት በርግጥ የመማሯን ሁኔታ አጠራጣሪ አድርጋ የተናገረችው ፈትለወርቅ፤ የስብሃት ቡድን የህወሓት መሪ ሊያደርጋት ከፍተኛ ሙከራ ቢያደርግም በ“ራዕይ አስጠባቂዎቹ” ቡድን ውድቅ ተደርጎበታል። ውጤቱን መቀበል ግን የሆነበት የስብሃት ቡድን በምክትልነት የመመረጧን ጉዳይ እንደ ድል ወስዶ ስልታዊ ማፈግፈግ አድርጓል።

“የመለስ ራዕይ” አስጠባቂ ቡድን “የግል ራዕይ የለም፤ ራዕይ ድርጅት ነው” በሚለው የስብሃት ቡድን ከፍተኛ ጥቃት በደረሰበት ጊዜ ሒሷን መዋጥ ያቃታት አዜብ ስብሰባውን ረግጣ መውጣቷ ይታወቃል። በአምቦ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆነው ስዩም ተሾመ “ውስጥ አዋቂውን” ጠቅሶ በፌስቡክ ገጹ ላይ እንደተናገረው “የመለስ አጥንት ይወጋናል” የሚለው የራዕይ አስጠባቂ ቡድን የዳያስፖራ (ትግሬዎችን) ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ አግኝቷል። እነዚሁ የመለስ ራዕይ ደጋፊ ዳያስፖራዎች “እናከብራችኋለን እንጂ አንፈራችሁም!” የሚል መልዕክት በስልክና ኢሜል አድራሻዎች በገፍ ሲልኩ” መቆየታቸውን አስታውቋል። እንቅስቃሴውን ማሸነፍ የተሳነው የስብሃት ነጋ ቡድን ፈትለወርቅን በምክትልነት አስመርጦ እጅ መስጠት ግድ ሆኖበታል።

ይህ እጅ መስጠት በአዜብ ላይ የተጣለውን ዕገዳ እንዲነሳ እስከመቀበል ሊያደርስ ይችላል የሚል ግምት እየተሰጠው ይገኛል። በህወሓት የወንበዴዎች ቡድን አሠራር መሠረት ስብሰባ ረግጦ መውጣት ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑ የነስዬ ታሪክ ምስክር ነው። ከዚህ አንጻር የአዜብ ዕገዳ እስከምን እንደሚደርስ በቅርቡ የሚታይ ይሆናል።

ከህወሓት ኅልውና ጋር በተያያዘ የኤፈርት ጉዳይ ትልቁ አጀንዳ በመሆኑ የስብሃት ቡድን ድርጅቱን ወደራሱ ቤተሰብ ለመጠቅለል የሚያደርገው ሙከራ ደንቃራ ገጥሞታል። በመቀሌው የወንበዴዎቹ ስብሰባ ላይ “ከኤፈርት ያለ አግባብ የወሰድከውን 30 ሚሊዮን ዶላር መልስ” የተባለው ስብሃት “ባለቤት የሌለው መስሎኝ ነው የወሰድኩት” በማለት ምላሽ መስጠቱን ስዩም ውስጥ አዋቂ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል። ከዚህ አንጻር የወንድሙ ልጅ የሆነችውን ፈትለወርቅን በማንገስ ኤፈርትንም ለመቆጣጠር ያለመው የስብሃት ጸረ-መለስ ራዕይ ቡድን ኤፈርትንም ለመለስ ራዕይ አስጠባቂ ቡድን ያስረክባል የሚለው ግምት እያየለ መጥቷል።

የበረሃ ወንበዴዎቹ ከዚህ ሁሉ ስድድብና መረን የለቀቀ መናናቅ በኋላ የአሸባሪ ቡድኑን ኃላፊ አድርጎ የቀድሞ ወንበዴዎችን እና ከበረሃ መልስ ወደ ድርጅቱ የገቡትን በመቀላቀል “ሥራ (አሸባሪ) አስፈጻሚ” አድርጎ የሚከተሉትን መርጧል፤

ደብረጽዮን ገብረሚካኤል
ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር
ዓለም ገብረዋህድ
አስመላሽ ወልደሥላሴ
ጌታቸው ረዳ
አዲስዓለም ባሌማ
ኬርያ ኢብራሂም
አብርሃም ተከስተ
ጌታቸው አሰፋ

ከዚህ ቀጥሎ የሚጠበቀው ከላይ የተጠቀሱትን ጨምሮ ከትምህርትና መልካም አስተሳሰብ የጸዱ በርካታ ወንበዴዎችና ዘራፊዎች በሚሰበሰቡበት “ድርጅታዊ ጉባዔ” ላይ የአዜብ “ጎላ” መስፍንን ዕድል ፈንታ መወሰን ይሆናል። ከተሳካላት በ“መለስ ራዕይ” መቀመጫዋን ታስተካክል ይሆናል፤ ካልሆነም “ታጋይ አይሞትም” የሚል “ጉሊት” ከፍታ ከዚህ በፊት የተናገረችውን “ሃፍታም” የመሆን “ራዕይዋን” ለማሳካት ደፋ ቀና የምትልበት “ብሩህ” መጪ ጊዜ ይሆንላታል በማለት አስተያየት ሰጪዎች ተሳልቀዋል።

ለዜናው ቅንብር የተጠቀምናቸው ምንጮች፤ ሪፖርተር እና Ethio think tank ናቸው።


6ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 6 - ERi-TV Documentary

Dehai Events