World News

Zehabesha.com: የአቦይና ራዕይ ቡድኖች በመቀለ ባደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት ሲያጠናቅቁ | ኦህዴድና ብአዴን 1ኛና 2ኛ ሆነው ወደ ቀጣዮ ዙር አልፈዋል

Posted by: Berhane Habtemariam

Date: Thursday, 30 November 2017

የአቦይና ራዕይ ቡድኖች በመቀለ ባደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት ሲያጠናቅቁ | ኦህዴድና ብአዴን 1ኛና 2ኛ ሆነው ወደ ቀጣዮ ዙር አልፈዋል

ከስዩም ተሾመ

https://www.youtube.com/watch?v=hFjc0_4dWBA

በአንድ በኩል ምርጫውን በማራዘም እስከ ቀጣዩ ጉባኤ ህወሓት በም/ሊቀመንበሩ ዶ/ር #ደብረፂዮን እየተመራ ለማስቀጠል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ወ/ሮ ፈትለወርቅን (#ሞንጆሪኖን) የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ ለመሾም ሲደረግ የነበረው የህወሓት ጨዋታ #በአቻ_ውጤት ተጠናቋል፡፡ በመጀመሪያው ግማሽ ጎል ያስቆጠረው #የአቦይ_ቡድን በሁለተኛው አጋማሽ ባደረገው የመከላከል ጨዋታ ሞንጆሪኖን ከዋና ሊቀመንበርነት ወደ ምክትል ሊቀመንበርነት በማውረድ ነጥብ ጥሏል፡፡ በሁለተኛ አጋማሽ አጥቅቶ ሲጫወት የነበረው #የራዕይ_ቡድን ደግሞ ሞንጆሪኖን ጠልፎ በመጣል ደብረፂዮንን ወደ ዋና ሊቀመንበርነት እንዲመጣ አድርጏል፡፡ በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ከተጫዋቾች ጥፋት ተሰርቶብኛል በሚል ጨዋታውን አቋርጣ በመውጣቷ ምክንያት ከጨዋታ የታገደችው በቀጣይ ቅጣቱ ሊነሳላት እንደሚችል ይገመታል፡፡

በጨዋታው ሁለተኛ አጋማሽ ከራዕይ ቡድን ደጋፊዎች ሲሰማ ከነበረው የድጋፍና ተቃውሞ መፈክር ውስጥ፣ <<#የመለስ_ዜናዊ አጥንት ይወጋናል>> የሚል ይገኝበታል፡፡ በተለይ ደግሞ በውጪ የሚኖሩ የራዕይ ደጋፊዎች <<እናከብራችኋለን እንጂ አንፈራችሁም!>> የሚል መልዕክት በስልክና ኢሜል አድራሻዎች በገፍ ሲልኩ እንደነበር ታውቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ የህወሓት የቢዝነስ ኢምፓየር #በአቦይ_ስብሃት ቤተሰብ ተጠቀለለና “ከEFFORT ያለ አግባብ የወሰድከውን 30 ሚሊዮን ዶላር መልስ” እና “ባለቤት የሌለው መስሎኝ ነው የወሰድኩት” በማለት ሲነታረኩ እንደነበር ውስጥ አዋቂያችን ከስፍራው ዘግቧል፡፡

በዚህ መሠረት፣ ሁለቱም ቡድኖች በሁለት ጨዋታ ተሸንፈው አንድ አቻ ወጥተው በአንድ-አንድ ነጥብ ወደ ቀጣዮ ዙር ሳያልፉ ቀርተዋል፡፡ ከምድቡ 2 ጨዋታ አሸንፎ፣ በአንዱ አቻ የወጣው #ኦህዴድ 7 ነጥብ አንደኛነት ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል፡፡ ወጥ አቋም ማሣየት የተሳነው #ብአዴን፤ በመጀመሪያው ጨዋታ አሸንፎ፣ በሁለተኛው ደግሞ ተሸንፎና በመጨረሻው ዙር ጨዋታ አቻ ወጥቶ በ4 ነጥብ ወደ ቀጣዩ ዙር በሁለተኝት አልፏል፡፡ ሌላኛው ተወዳዳሪ #ደኢህዴን በከፍተኛ ግራ መጋባት ውስጥ በመሆኑ ምክንያት ራሱን ከውድድሩ ማግለሉ ይታወሳል፡፡
___________________________________________________________________________________________________
EBC:-

የህወሓት ማዕከላዊ ካሚቴ ከአንድ ወር በላይ ሲያካሂደው የነበረውን ስር ነቀል ግምገማና ሂስ ግለሂስ በዛሬው ዕለት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

ከግምገማና ሂስ ግለሂስ በኋላ የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድና 9 አባላት ያሉት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን ምርጫ አካሂዷል፡፡

በዚሀም መሠረት

1ኛ ጓድ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል

2ኛ. ጓዲት ፈትለወረቅ ገብረእግዚአብሔር

3ኛ. ጓድ ጌታቸው አሰፋ

4ኛ. ጓድ አለም ገብረዋህድ

5ኛ. ጓድ ዶክተር አዲስ አለም ባሌማ

6ኛ. ጓድ አስመላሽ ወልደስላሴ

7ኛ. ጓድ ጌታቸው ረዳ

8ኛ. ጓዲት ኬርያ አብረሃም

9ኛ. ጓድ ዶክተር አብረሃም ተከስተን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አድርጐ

የመረጠ ሲሆን ከነዚህም መካከል

ጓድ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን የድርጅቱ ሊቀመንበር፣ ጓዲት ፈትለወረቅ ገብረእግዚአብሔርን ደግሞ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አድርጓ በመምረጥ ስብሰባውን ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡


EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events