World News

Goolgule.com: አዜብ መስፍን በቁም እስር ላይ ነች

Posted by: Berhane Habtemariam

Date: Wednesday, 29 November 2017

አዜብ መስፍን በቁም እስር ላይ ነች

 
  • የጉዞ ዕገዳ እንደ ተጣለባት ይነገራል

ከሰሞኑ የህወሓት የሥልጣን ሽኩቻ ጋር በተያያዘ የነደብረጽዮን ቡድን አዜብ መስፍንን ከማንኛውም የፓርቲ ሥልጣን ካገዳት በኋላ በቁም እስር ላይ እንደምትገኝ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል። የጉዞ ዕገዳም ተጥሎባታል።

ከህወሓት በተሰጠው መግለጫ ለመረዳት እንደሚቻለው የአዜብ ጉዳይ በዕገዳ ቆይቶ በቀጣይ የሚታይ ቢሆንም ዕገዳው በራሱ የቁም እስር እንደሆነ መረጃው ይጠቁማል። አዜብ የኤፈርት ዋና ኃላፊ እንደመሆኗ በቀጣይ ከዚያ ሥልጣኗ ጋር በተያያዘ ውሳኔ ቢሰጥ የሚያመጣው ተቀጣጣይ ውጤት እየታሰበበት ያለ ጉዳይ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያስረዳል። ከዚህ የቁም እስር ጋር በተያያዘ አዜብ የጉዞ ዕገዳ እንደተጣለባት ተጠቁሟል።

መለስ የሞተ ጊዜ የትግራይ ተገንጣይ ቡድን ዋና “ወንበዴ” የሆነው ስብሃት ነጋ “የግለሰብ ሌጋሲ የሚባል የለም፤ ሌጋሲ የድርጅት ነው” ባለው መሠረት ባሁኑ ጊዜ የመለስን “ሌጋሲ” በ“ስብሃት ሌጋሲ” ለመተካት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። የህወሓት ስብሰባ ሳይጠናቀቅ ለኤፈርት ቅርብ የሆኑት አዜብ መስፍንና በየነ ምክሩ መባረራቸው ይፋ መሆኑ የነስብሃት ቡድን የፖለቲካውን ሙቀት የሚለካበት መሣሪያ ሆኖ ተወስዷል። በቀጣይ ስብሃት ከኤፈርት ኃላፊነቱ ተነስቶ በአዜብ የተተካበትን የፖለቲካ ቁማር የሚበቀልበት ይሆናል እየተባለ ይጠበቃል። የፖለቲካውን መዘውር ለማጥበቅ የኢኮኖሚ ድጋፍ ስለሚያስፈልግ ኤፈርትን በስልት በቁጥጥር ሥር ማዋል የነስብሃት ቡድን ወሳኝ ሥራ ይሆናል። ከዚህ ጋር ተያይዞ አዜብን የሚጠብቃት የቁም ይሁን የቂሊንጦ እስር አብሮ የሚወሰን ይሆናል።

በባሏ ትግሬ የሆነችው አዜብ “ጎላ” መስፍን ባለፈው ከሚሚ ስብሃቱ ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ ህወሓት ቢለቃት “ሃፍታም” እንደምትሆን የገለጸች ሲሆን ይህንንም “ሃፍት” ጉሊት በመቸርቸር መልሳ እንደምታገኘው መግልጽዋ አይዘነጋም። (ፎቶዎቹ ከማህበራዊ ገጾች የተገኙ ሲሆን ተቆራኝተው የተሠሩት በጎልጉል ነው)


EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events