World News

Satenaw.com: የሕወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ኣጫጭር መረጃዎች

Posted by: Berhane Habtemariam

Date: Friday, 24 November 2017

የሕወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ኣጫጭር መረጃዎች  

አሰግዴ ገብረስላሴ (መቐለ)

November 24, 2017 23:19
 


——————————–
የሕወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ ጭንቀት የተሞሏበት፣ አንድ አንድ የማእከላዊ አባላት ታመናል ብለው ወደ ዉጭ የሸሹበት ፣ታመምን ብለው ተደብቀው በሰው ቤት የተኙበት ፣የስብሰባ መድረክ ረግጠው የወጡበት ( የሸሹ ) ፣ በስብሰባ ውስጥ ገብተው የተጣሉበት ፣ በአጠቃላይ ስብሰባው ጠብ ፣መናናቅ ፣በቂም በቀል ብድር መማላለስ የተሞሏበት ሆኖ ነው የሰነበተው ።  አንዳንድ የውስጥ አዋቂዎች እንደነገሩን፡

1ኛ ብርሃኔ ኪዳነማርያም (መራት) ታመምኩ በማለት ወደ ዉጭ ሄዷል።

2ኛ በየነ ሞኩሩ “በሙስና ተባላሽታሀል” የሚል ከባድ ሂስ ከተሰጠው በኃላ፣ በተጨማሪ ከደብረጽዮን ጋር በመድረክ ላይ በተደጋጋሚ ስለተጣሉ፣ “ታምሚያለሁ” በሚል ምክንያት ከስብሰባው ወጥቶ ከቤቱ ውጭ በጓዶኞቹ ቤት ተኝቶ ሳለ፣ እንደገና ተለምኖ ወደ ሰብሰባ ገብቷል።

3ኛ ኣዜብ መስፍን አንደኛ “በሙስና ተባለሽተሻል” ስለተባለች ሁለተኛ አባይ ወልዱ በጸረ ዲሞክራሲ አሰራሩ፣በትግራይና በጎንደር ግጭት ምክንያት ስለሞቱት የትግራይ ተወላጆች ፣ስለወደመው የህዝብ ሀብት እና ስለግጭቱ በዋናነት ተጠያቂ መሆኑ ስለተነገረው ፣ በትግራይ ክልል በሚሊዮን የሚቆጠር የህወሓት ኣባል ከኣባልነት በመውጣቱ ፣ብዙ የመንግስት ሰራተኛ በኣባይ ወልዱ ጸረ ዲሞክራሲ ምክንያት ከክልሉ በሙሉ እንዲወጡ በመደረጉ፣ የትግራይ ህዝብ የፍትህና የማህበራዊ ኣገልግሎት ባለማግኘቱ ፣ በክልሉ የሌለ የልማት እድገት የውሸት ዳታ በማቅረቡ ከባድ ሂስ ስላረፈበት ፣ ኣዜብ መስፍን “እንደ ኣባይ ያለ የመለስን ረኣይ ስትራተጂ እና ፖሊሲ ያስፈጸመ የለም” ብላ አባይን ለመመከት ስትሞክር ከተሰብሳቢዎች ብዙ ዘለፋ ስለደረሰባት ፣ ስለኤፈርት ኣማራር ውድቀት ስላብጠለጠሏት ክብሬን ተነካ ብላ ከመድረክ ወጥታለች። ከወጣች ከቀናት በኃላ በጀነራል ሳሞራ የኑስ ኣስታራቂነት ይቅርታ ጠይቃ ልትመለስ ተደርጎ ስትመለስ ፣ደብረጽዬን ገብረሚካኤል እና ቡዱኖቹ “ ኣዜብ መስፍን የድርጅታችን መተዳደሪያ ደንብ ረግጣ ስለወጣች መመለስ የለባትም ። ካሁን በፊትም የህዋሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ኣንጃዎች የፓርቲው መተዳደርያ ደንብ በመጣሳቸው ነው የተባረሩት ፣በመሆኑም ኣዜብ መመለስ የለባትም”  በማለት አጥብቀው የተከራከሩ ሲሆን በመጨረሻ ኣዜብ በድምጽ ኣብላጫ ይቅርታ ጠይቃ እንድትቀላቀል ተደርጓል። ሆኖም በመድረኩ ገብታ በሂስ እየተመታች በጭንቀት ውስጥ ትገኛለች።

4ኛ ኣለም ገብረዋህድ ፣ አዲስኣለም ባሌማ ፣ሚኪኤለ የኣክሱም ዞን ኣስተዳዳሪዎች በከባድ የሙሱና ብለሽት ከባድ ሂስ እያረፈባቸው ይገኛል። በተለይም ብዙ ሀብት በምዝበራ እንዳከማቹ ተነግሯቸዋል ።

5ኛ ኪሮስ ቢተው ፣የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሀላፊ በትግራይ የሌለ የእርሻ ምርት የውሸትት ዳታ በማቅረቡ ሂስ ኣርፎቦታል ። ይህ እንዳለ ሆኖ ኪሮስ ቢተው የዉሸት ልማት ዳታ በማቅረቡ ፣እርዳታ ይሰጡን ለነበሩ ለጋሽ ኣገሮችም የእርዳታ እጃቸው እንዲስቡ ኣድርጓል በማለት ነበር ከባድ ሂስ ያረፈበት።

6ኛ እነዛ ኣንጋፋ ሙሶኞች የህወሓት ከፍተኛ ኣማራር የነበሩ ገና ሂስ እስኪሚያርፍባቸው በሩቅ ሆነው ምንም ገበና እንደሌላቸው ኣመካሪዎች ፣ ኣስተያዬት ሰጭዎች ሆኖው ጸጥ ጭልጥ ብለው ቃላት እየወረወሩ ይታያሉ ።እኒህ ኣዛውንቶች ኣሁን ጭዋ እና ንጹሃን ይምሰሉ እንጅ ኣስቀድመው የዚህ ሀገርና ህዝብ ኣንጡራ ሀብት ዘርፈው ዘርዘራቸው በሁለገብ ያቋቋሙና ልጆቻቸው ያዳላደሉ ናቸው ።

7 በ1993 ዓ / ም ከህወሃት ተገንጥለው የወጡ ማእከላይ ኮሚቴ የነበሩ ገብሩ ኣስራት ፣ስዬ ኣብርሀ ፣ኣውዓሎም ወልዱ ሲቀሩ ሌሎች ማ / ኮሚቴ የነበሩ ይመለሱ ኣይመለሱ ክርክር ተደርጎ ኣባይ ወልዱና ጥቂት ቡዱኖቹ ሲቃወሙ ሌሎች ግን ተስማምቷል ።

8ኛ በኣጠቀላይ በስብሰባው ተጠምዶና ተጨንቆ ያለው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በብዙ ቡዱኖች ተከካፋፍለው ከርመው በኣሁኑ ጊዜ በጥቅማቸው ተሳስረው ወደ ሶስት ጠንካራ ቡዱኖች እና ሶስት ደካማ ቡዱኖች ወርደዋል ። ወና ዋናዎቹ ፣

  • የኣባይ ወልዱ የትግራይ ማእከላይ ከሚቴ የሚባል በኣባይ ወልዱ ኣዲስ ኣለም ባሌማ በየነ መኩሩ ፣ኣለም ገብረዋህድ ፣ኣባይ ጸሀዬ ፣አለም ገበረወህድ ሓገስ ጤና ጥበቃ ፣ኪሮስ ቢተው ፣ እና ሌሎች እንደሮቦት በሪሞት የሚነዱ ሆነው ትልቅ ቡዱን ነበሩ ። ኣሁን ግን ኣባይ ወልዱና ኣባይ ጸሀዬ ኣዜብ መስፍን ፣ሀጎስ እና ጥቂት ሰዎች የመለስ ረኣይ ነክሰው እንደቀሩ ነው።
  • ይህ ቡዱን የኣርከበ እቁባይ በመጠኑ እነደብረጽዮን እና ጌታቸው ኣሰፋን የሚደግፍ ቡድን ነው። ሰልጣናችን ለሀቀኛ እና ቡቁ የምሁራን ትወልድ እናስረክብ ፣እስከኣሁን በስመ ምሁር በማእከላዊ ኮሚቴና ሌላ የስልጣን ቦታ ያስቀመጥናቸው ሌቦችና ለሆዳቸው ያደሩ ናቸው ባይ ነው። ይህ ቡድን በብዛቱ ጥቂት ነው ።
  • ሰብሀት ነጋ የያዘው ቡዱን ነው። ይህ ቡድን “ህወሓትን እናድን። ነባር ተጋዮችና ኣማራር ፣ኣባልት እንሰብስብ” ይላል”” እንደ ኣርከበ በዱንም ወደነ ደብረጽየን እና ጌታቸው ኣሰፋ ያዘነብላል ።
  • እነ ብርሀነ ገብረክርስቶስ ያሉባቸው ጥቂት ሰዎች ደግሞ የህዝብ ማእበል ወላፈን እንዳያቃጥላቸው መሐል ሰፋሪ ሆነዋል ።

ኣለም ገብረዋህድ ኪሮስ ቢተው ፣ ኣዲስ ባሌማ በየነ መኩሩ የያዙ በርከት ያሉ የሂስ ዱላ ካረፈባቸው በኃላ ለሌላው ቡድን ፈርተው ወደእነ ደብረጽዮን እና ጌታቸው ኣሰፋ እንደወገኑ ከህወሓት ስብሰባ መረጃው ኣፈትልኳል ።

ከላይ እንደጠቀስኩት ደብረጽዮንና ጌታቸው ኣሰፋ እነኪሮስ ቢተው ኣስከትሎ ለኣባይ ወልዱና ጓደቹ በከባድ ሂስ ከሰራ ውጭ እያደረገ ያለ ትልቅ ቡዱን ነው ። ጀነራል ሳሞራ የኑስም በውጭ ሆኖ ኣባይ ወልዱን፣ አዜብንና  አባይ ጸሀዬ እንደሚደግፍ የወጡ መረጃዎችን ይጠቁማሉ ።

በማጠቃለል የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በኣሁኑ ጊዜ በውስጡ ኣንድነቱ ተበጣጥሶ ታክሞ ሊድን በማይችልበት ሁኔታ ነው የሚገኘው ።በአሁኑ ጊዜ እነዚህ ፍጡራን ለሀገርን ህዝብን ፍትህ ሰላም ለማስፈን ኣቅማቸው እንዳለቀ ኣምነው ስልጣናቸው ለማህበረሰብ ኣስረክበው ፣ገበና ካላቸው ወደ ህዝብ ቀርበው፣ ፍረዱን ከማለት ፈንታ ከስልጣን ጋር የሙጡኝ ብለው መያዝ ኣያዋጣቸውም ።

ከላይ የተቀመጠው የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ከተባላሸው ስብሰባ ተያይዞ በመቀሌ ከተማ ካሁን በፊት ያልነበረ የጸጥታ ሀይሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት የድህንነት ፣ የናሳ ከኖሬሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በስብሰባው ኣካባቢ እያንጃበቡ ከባድ ጥበቃ እያደረጉ ይገኛሉ ።ተራ የስለላ ወይ ድህንት ሃይሎች ፣ፈደራል ፓለስ የትግራይ ልዩ ሀይል በሙሉ መቀለ ከተማ ነው ያለው ። የመከላከያ ሀይልም ከወትሮው የተለዬ ኣለ ።
ኣስገደ ገብረስላሴ
መቀለ
15 / 03 / 2010


EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events