Dehai News

(ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን የጋራ የትብብር ፕሮጀክቶችን ለመተግበር ተስማሙ

Posted by: Semere Asmelash

Date: Tuesday, 05 March 2019

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን የጋራ የትብብር ፕሮጀክቶችን ለመተግበር ተስማሙ

አዲስ አበባ ፣ (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን የጋራ የትብብር ፕሮጀክቶችን ለመተግበር ስምምነት ላይ ደረሱ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት በዛሬው እለት በደቡብ ሱዳን ጁባ የሶስትዮሽ ውይይት አድርገዋል።



በውይይታቸው ወቅም ሃገራቱ በጋራ በሚተገብሯቸው የትብብር ፕሮጀክቶች ላይ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ስምምነት የተደረሰባቸው የትብብር ፕሮጀክቶች የቀጠናውን የኢኮኖሚ ትስስር በማፋጠን ለጋራ ተጠቃሚነት እንደሚረዱ ታምኖባቸዋል።

ከዚህ ባለፈም መሪዎቹ ሃገራቱ በቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራት የሚችሉበትን አግባብ ማመቻቸት በሚቻልበት ጉዳይ ላይም በስፋት መክረዋል።



በተጨማሪም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው በኩል የሃገራቱን ኢኮኖሚያዊ ውህደት ለማምጣት ለመስራት ተስማምተዋል።

ከደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘም በደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት በጋራ መስራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂም ውይይታቸውን አጠናቀው መመለሳቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በትናንትናው እለት ወደ ኤርትራ ማቅናታቸው ይታወሳል።

በቆይታቸውም ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የሶስትዮሽ ውይይት አድርገዋል።


EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events