ኤርትራውያኑ ከ21 ዓመት በላይ በአደራ የተቀመጠ የእቁብ ገንዘብ ተመለሰላቸው
ኤርትራውያኑ ከ21 ዓመታት በኋላ 48 ሺህ የዕቁብ ብራቸውን ከነወለዱ ባህርዳር ከተማ ካሉ ወዳጆቻቸው ተረክበዋል፡፡
በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል በተፈጠረው ችግር ምክንያት ከወዳዶጃቸው ጋር የገቡትን እቁብ ገንዘብ በአደራ ተቀምጦ ከ21 አመታት በኋላ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ዳግም ሰላም በመፈጠሩ የአደራ ገንዘባቸውን ባህርዳር ከተማ በአካል ተገኝተው ተረክበዋል፡፡
በባህርዳር ከተማ ከ30 ዓመታት በላይ የኖሩት ኤርትራዊያኑ አቶ ፀሀዬ ሀይሉ እና ባለቤታቸው በአገራቱ መካከል ሰላም ተፈጥሮ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ በመምጣታቸው ደስታቸውን ገልፀዋል፡፡
በሁለቱ አገራት መካከል ዳግም ሰላም ይመጣና ተመልሰው ከወዳጅ ዘመዶቻቸው እንደሚቀላቀሉ እምነታቸው እንደነበርም አቶ ፀሀዬ ገልፀዋል፡፡
አብመድ