Dehai News

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤርትራ የባህል ልኡካን የኪነ-ጥበብ ስራዎቻቸውን በሃዋሳ ሲዳማ ባህል አዳራሽ እያቀረቡ ነው

Posted by: Semere Asmelash

Date: Tuesday, 19 February 2019

የኤርትራ የባህል ልኡካን የኪነ-ጥበብ ስራዎቻቸውን በሃዋሳ ሲዳማ ባህል አዳራሽ እያቀረቡ ነው

አዲስ አበባ፣የካቲት 19፣2019 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤርትራ የባህል ልኡካን የኪነ-ጥበብ ስራዎቻቸውን በሃዋሳ ከተማ ሲዳማ ባህል አዳራሽ እያቀረቡ ነው ።

የባህል ቡድኑ  በአሁኑ ሰዓት ሃዋሳ ከተማ  በሚገኘው የሲዳማ ባህል አዳራሽ ባህላዊና ዘመናዊ የኤርትራ ዘፈኖችን ጨምሮ የተለያዩ የኪነጥበብ ስራዎች እያቀረበ ይገኛል ።



የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ልኡካን  በዛሬው  ዕለት በሃዋሳ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ ቦታዎችን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል ።

በነገው ዕለትም  የሃዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክን በመጎብኘት ከሰዓት በኋላ ወደ አዲስ አበባ የሚመለስ መሆኑን ከተያዘው መርሃግብር ለመረዳት ተችሏል፡፡

የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ልኡክ  በአዳማ ከተማ የነበረውን ጉብኝት አጠናቆ ትናንት  ማምሻውን ሃዋሳ ከተማ መግባቱ ይታወቃል ።

የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ልኡክ  ሀዋሳ ከተማ ሲደርስ የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ፣ የደቡብ ክልል ምክር ቤትና ፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች እንዲሁም የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

በመጨረሻም ቡድኑ የካቲት 21 ቀን  2019 ዓ.ም 25 ሺህ የመዲናዋ ነዋሪዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ  የተለያዩ ዝግጅቶች የሚያቀርብ መሆኑ ተገጿል።



Dr. Fikrejesus Amahazion at the XXIX International Rosa Luxemburg Conference in Berlin on January

Dehai Events