Dehai News

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርግ ነው

Posted by: Semere Asmelash

Date: Thursday, 07 February 2019

የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2019 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ ከየካቲት 7 ጅምሮ በኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚያደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የጉብኝቱ አላማ የሀገራቱን ታሪካዊ ግንኙነት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ለማጠናከር ነው ተብሏል።

የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑኩ በኢትዮጵያ በሚኖረው ቆያታ በተለያዩ ዝግጅትቶች ተሳታፊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህም ልዑኩ የፊታችን የካቲት 9 ቀን ባህርዳር፣ የካቲት 10 በአዳማ፣ የካቲት 12 በሀዋሳ እና የካቲት 14 ደግሞ በአዲስ አበባ ከተሞች በሚካሄዱ ባህላዊ የሙዚቃ ኮንሰርቶች ተሳታፊ ይሆናል ተብሏል።

ለዚህ ባህላዊ የሙዚቃ ኮንሰርትም ሁሉም ኢትዮጵያዊና ኤርትራዊያን ተሳታፊ እንዲሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል።


6ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 6 - ERi-TV Documentary

Dehai Events