Dehai News

(ኤፍ ቢ ሲ) ጠ/ሚ ዶክተር አብይ ከጣሊያን መንግስት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱን ተናገሩ

Posted by: Semere Asmelash

Date: Monday, 21 January 2019

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ ከጣሊያን መንግስት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱን ተናገሩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 21 ፣ 2019 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከጣሊያን መንግስት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱን ተናገሩ።

በጣሊያን ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጣሊያኑ አቻቸው ጁሴፔ ኮንቴ ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከጣሊያኑ አቻቸው ጋር ያደረጉት ውይይት ውጤታማና የተሳካ እንደነበር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ጠቅሰዋል።

በተለይም በልማት፣ መሰረት በልማትና ሰላም ዙሪያ ስኬታማ ውይይት ማድረጋቸውን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በተለያዩ መስኮች መግባባት ላይ መድረሱን ገልጸዋል።

ሃገራቱ ከአዲስ አበባ ምፅዋ በሚዘረጋው የባቡር ሃዲድ ዙሪያ ትብብራቸውን ከፍ ማድረግ በሚያስችል ደረጃ ተወያይተዋል።

በዚህም የጣሊያን መንግስት አዲስ አበባን ከምፅዋ ወደብ ጋር ለማስተሳሰር የሚያስችለውን የባቡር ፕሮጀክት የመጀመሪያ ጥናት ወጪ ለመሸፈን መስማማቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈም በመዲናዋ የሚገኙ ኤምባሲዎች የተወሰነውን የኤምባሲ ቦታቸውን ለህዝብ መዝናኛነት ክፍት እንዲያደርጉ ለተያዘው እቅድ የጣሊያን መንግስት ይሁንታ ማሳየቱንም አውስተዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም በአዲስ አበባ የሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ካለው አጠቃላይ ይዞታ የተወሰነውን ክፍል ለህዝብ መዝናኛ ፓርክነት እንዲያውል ለቀረበው ጥያቄ አወንታዊ ምላሽ መገኘቱንም አስረድተዋል።

በተጨማሪም በጣሊያን የረጅም ጊዜ የልማት ትብብር መሰረት ለትምህርት እድሜያቸው የደረሱ ህፃናትን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ፕሮግራሞች ላይ ለመስራት ተስማምተናልም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በዚህም በመዲናዋ ከትምህርት ቤት ምገባ ጋር ተያይዞ ለተማሪዎች ዳቦ ለማቅረብ ለተያዘው እቅድ የጣሊያን መንግስት የዳቦ መጋገሪያ ፋብሪካን ለመትከል በሚኖረው ሂደት ለማገዝ ቃል መግባቱንም በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።

እንዲሁም ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ለተመለሱ ወታደሮች መቋቋሚያ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ለመቀጠል ቃል ገብቷልም ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ውይይታቸው የተሳካ እንደነበር ጠቅሰው፥ የሃገራቱን ግንኙነት በሁለትዮሽ ውይይት በማጠናከር በልማት፣ በሰላምና በቱሪዝምና በጋራ መስራት እንደሚገባም አንስተዋል።

ለጋራ ልማትና ሰላም በጋራ እንስራ ሲሉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ ከጣሊያን መንግስት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱን…

Jan 21, 2019

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ ከጣሊያኑ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

Jan 21, 2019



6ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 6 - ERi-TV Documentary

Dehai Events