Dehai News

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በቁጥጥር ስር ዋሉ

Posted by: Semere Asmelash

Date: Tuesday, 13 November 2018

የሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2018 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳረጋገጠው ተጠርጣሪው በሁመራ በኩል ከሀገር ለመውጣት ሲሞክሩ በትግራይ ክልል ልዩ ሀይል ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

ሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በአሁኑ ወቅት ተይዘው አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰዋል።

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ሌሎች የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለው ትናንት ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወቃል።

በእነዚህ ተጠርጣሪዎች ላይም ፍርድ ቤቱ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱም የሚታወቅ ነው።

በባሃሩ ይድነቃቸው



EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events