Dehai News

( (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአማራ ክልል ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

Posted by: Semere Asmelash

Date: Wednesday, 07 November 2018

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአማራ ክልል ጉብኝት ሊያደርጉ ነው  

አዲስ አበባ ፣ (ኤፍ ቢ ሲ) የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአማራ ክልል ጉብኝት ሊያደርጉ ነው።

ፕሬዚዳንቱ ከፊታችን ዓርብ ጀምሮ በጎንደር እና ባህር ዳር ከተሞች ጉብኝት ያደርጋሉ።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ዓርብ ጎንደር ከተማ የሚገቡ ሲሆን፥ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል ያደርጉላቸዋል።

በቆይታቸውም በጎንደር እና አካባቢው የሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎችን እና የልማት ስራዎችን እንደሚጎበኙ፥ የጎንደር ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ሞገስ ተናግረዋል።

የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት በሃገር ደረጃ የተጀመረውን ግንኙነት እንደሚያጠናክረው ታምኖበታል።

በጎንደር ከተማ በርካታ ኤርትራውያን በተለያየ ስራ ተሰማርተው ይገኛሉ።

ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ የተመራ የልዑካን ቡድን በአስመራ ጉብኝት ማድረጉ የሚታወስ ነው።

በነብዩ ዮሃንስ

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአማራ ክልል ጉብኝት ሊያደርጉ ነው – 

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአማራ ክልል ጉብኝት 

ሊያደርጉ ነው

FanaBC

Published 

on

 

By

 FanaBC 






EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events