Dehai News

Mereja.com: የ”ኦሮማይ” መጽሃፍ ደራሲ በዓሉ ግርማ እንዲገደል የሚያዝ በጄኔራል ገብረየስ ወልደሀና ተጽፎ ለኮ/ል ተስፋዬ ወልደስላሴ የተላከ ደብዳቤ

Posted by: Berhane.Habtemariam59@web.de

Date: Wednesday, 18 July 2018

 

የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት
የወታደራዊ ክፍሎች የፖ/ጉ/ ጠቅላይ መምሪያ

ለጓድ ተስፋዬ ወ/ሥላሴ
የአገር ውስጥ ሚኒስቴር
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፦ ስለ የበዓሉ ግርማ ፀረ-ሕዝብ አመለካከት ላይ እርምጃ ስለ መውሰድ የመለከታል

የሰሜኑ አገራችንን ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት መንግስት ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁለገብ ዘመቻ በማድረግ ከሞላ ጎደል ብዙ ውጤቶችን አስመዝግቧል። ጀግናው አብዮታዊ ሰራዊታችንም ለዘመቻው ከፍተኛ የህይወትና የአካል መስዋዕትነት ከፍለዋል ግን ይህን የሚአሳጣና የሚአቋሽሽ በበዓሉ ግርማ የተጻፈ “ኦሮማይ” መላት የኤርትራ ጉዳይ የሞተ፣ ያለቀለት፣ ያበቃለት በማለት [ …] መጽሃፍ በገበያ ላይ ውሎ ሰራዊታችን እጅ ገብቶ ከፍተቻ ችግር […]

“ኦሮማይ” መጽሐፍ በጠላት ራዲዮ ጣቢያ ሻቢያ በኩል እየተሰራጨ የተወሰኑት አባላት ሰምተው በቡድንና በነጠላ እጅ ከመስጠታቸው በላይ በጠላት ጎራ ሆነው […] ቃላቸውን እየነዙ ይገኛሉ።

መጽሐፉ በገጸ ባህሪዩ ውስጥ ያካተታቸው በቀይ ኮከብ ሁለገብ አብዮታዊ ዘመቻ ወቅት በአገር ጉዳይ ቁልፍ ሚና የተጫወቱትን ባለሥልጣናት እና ተባባሪዎችን […] ለጠላት የሰጠ ሊታረም የማይችል ጥፋት ሀገር ላይ የፈጸመ ግለሰብ እና ፀረ-አንድነት ድርጊት መሆኑ ታውቆ አፋጣኝና ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወሰድበት አሳስባለሁ።

ገብረየስ ወ/ሃና
ብ/ጄኔራል

 

EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events