Dehai News

(ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስመራ ገቡ

Posted by: Semere Asmelash

Date: Sunday, 08 July 2018

ኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስመራ ገቡ

ኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስመራ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 8፣ 2018 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነትን ያድሳል የተባለለትን ታሪካዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ኤርትራ ገብተዋል።

አስመራ ሲደርሱም ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት እንደዚሁም የከተማዋ ነዋራዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በቆይታቸውም ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የሚወያዩ ይሆናል።

ሁለቱ ሀገራት ያካሄዱትን የድንበር ግጭት ተከትሎ ግንኙነታቸውን ለሁለት አስርት ዓመታት አቋርጠው ቆይተዋል።

በቅርቡ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማደስ የአልጀርሱን ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር ውሳኔ ማሳለፉ ለግንኙነታቸው ተስፋ ፈንጥቋል።

ኤርትራም የኢትዮጵያን የሰላም ጥሪ በመቀበል በቅርቡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ የሚመራ ልዑክ ወደ አዲስ አበባ መላኳ አይዘነጋም።

በዚህም ወቅት ለሀገራቱ ግንኙነት መታደስ መንገድ የሚጠርግ ውይይት መካሄዱን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቆ ነበር።


ኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስመራ ገቡ



EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events