Dehai News

(ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምላሽ ምስጋና አቀረቡ

Posted by: Semere Asmelash

Date: Thursday, 21 June 2018

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምላሽ ምስጋና አቀረቡ

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምላሽ ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ ሰኔ፣13፣2010( ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶክተር አብይ አህመድ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያን መንግስት የእርቅና ድርድር ጥሪ ለሰጡት ምላሽ ምስጋና አቅርበዋል።

በመልዕክታቸውም ኢትዮጵያ የኤርትራን የልዑካን ቡድንን በታላቅ አክብሮት ተቀብላ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን ነው ያስታወቁት።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምላሻቸውን የሰጡት በየዓመቱ በሚከበረው የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ላይ በቀጥታ ቴሌቪዥን ስርጭት ባደረጉት ንግግር ሲሆን፥ በድንበር ጉዳይ ላይ የሚነጋገር የሃገራቸውን ልዑክ ወደ አዲስ አበባ ለመላክ ማሰባቸውን ነው ዛሬ ጧት ላይ የተናገሩት።

በአፍሪካ ቀንድ በተለይም በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታዩ ያሉት ለውጦች ተገቢ ትኩረት የሚፈልጉ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት በሽግግር ላይ ትገኛለች ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ አሁን ላይ የቀረው በሁለቱ ሀገራት መካከል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ወደ ነበረበት ለመመለስ ቅድሚያ ተሰጥቶት ይሰራል ነው ያሉት።

ለዚህም በዜና ከመከታተል እና ከመቀባበል በዘለለ ያለውን ሁኔታ በቀጥታ ማወቅ ስለሚያስፈልግ፤ እንዲሁም በቀጣይ ሊሰራበት ስለሚገባ የልዑክ ቡድን ወደ አዲስ አበባ እንደሚላክ አስታውቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በዛሬው ዕለትም ከደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ መሪ ከሪክ ማቻር ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡


EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events