Dehai News

Zehabesha.com: አየር ሃይል እየታመሰ ነው | 13 ፓይለቶችና ከፍተኛ ባለሞያዎች ጠፍተዋል | ደብረዘይት በተኩስ እየተናወጠች ነው

Posted by: Berhane Habtemariam

Date: Wednesday, 03 January 2018

አየር ሃይል እየታመሰ ነው | 13 ፓይለቶችና ከፍተኛ ባለሞያዎች ጠፍተዋል | ደብረዘይት በተኩስ እየተናወጠች ነው


♦ደብረዘይት በተኩስ እየተናወጠች ነው!
♦አየር ኃይል ግቢ ከፍተኛ ውጥረት አለ !
♦ጉዳዩ ለወያኔ ሽብር ፈጥሯል!

ሙሉነህ ዮሐንስ

የኢትዮጵያ አየር ኃይል 10 ወጣት ፓይለቶች ሃገር ጥለው መሰወራቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች ደርሰውናል። ከነዚህ ውስጥ ስራ ላይ ያሉ 7 የሚግ 27 አብራሪዎች መሆናቸው ተነግሯል። ሶስቱ ደግሞ ሄሊኮፕተር እስኳድሮን ሲሆኑ አንድ ጠቅላይ መምሪያ ፐርሶኔል ሀላፊ ሻለቃ እና ሁለት የሎጂስቲክ መምሪያ ሃላፊወች መሆናቸው ታውቋል። እነዚህ ከፍተኛ ባለሞያዎች የኦሮሞ እና የአማራ ተወላጆች መሆናቸውን ተያይዞ የመጣልን መረጃ ይጠቁማል። ሁለቱ ከደርግ ስርአት ጀምሮ የቆዩ መኮነኖች ናቸው።


አስራ ሶስቱም የአየር ሃይል ባለሞያዎች በተቀነባበረና በተቀናጀ በሚመስል መልኩ ከሁለት ቀናት በፊት ከአገር መውጣታቸውን ነው የመረጃ ምንጮች የሚያስረዱት። ነገር ግን ወደ የት ሃገር እንደሄዱና ዝርዝር ማንነታቸውን ለደህንነታቸው ሲባል ለጊዜው እንደማይገለፅ ተነግሯል።


ወያኔ ዙሪያ ገባውን በህዝባዊ አመፅ ተወጥሮ እያለ የመጨረሻ መተማመኛ አድርጎ የቆጠረው ወታደሩ እንዲህ አይነት ከባድ ትርምስ ከገጠመው ውልቃቸውን መቅረታቸው ነው። በወያኔ የ26 አመት የግፍ አገዛዝ ዘመን ይህን ያክል የአየር ባልደረባ በአንድ ላይ ጥሎ ሲወጣ በቁጥርም በአይነትም ከፍተኛው መሆኑ ነው።
ዘግይቶ የደረሰን መረጃ እንደሚያሳየው ደብረዘይት በተኩስ እየተናወጠች ነው! አየር ኃይል ግቢ ከፍተኛ ውጥረት አለ! ጉዳዩ ለወያኔ ሽብር ፈጥሯል!
ህዝብ ያሸንፋል!

 

 
 
 
 
 
 
 
 

 

 

 


EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events