Basic

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳለህ በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ነው

Posted by: Semere Asmelash

Date: Thursday, 21 February 2019

የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳለህ በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2019 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳለህ የሚመራ የሀገሪቱ ልዑክ በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል።

በጉብኝታቸውም ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተላከ መልእክት አቅርበዋል።

መልእክቱም በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ጉዳዮች እና ቀጠናዊ ልማት ዙሪያ መሆኑን የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል አስታውቀዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የሁለትዮሽ ትብብር ያለበትን ደረጃ የሚገመግም የከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ያካተተ ኮሚቴ ውይይት ላይም ተሳትፈዋል።



EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events