Basic

ገጽ-መጽሓፍ: ኢትዮጵያ የኤርትራን ወደቦች ስትጠቀም የሚኖሩ የአገልግሎት ክፍያና የሎጀስቲክ አቅርቦቶችን አስመልክቶ ጥናት ተዘጋጀ

Posted by: Berhane.Habtemariam59@web.de

Date: Wednesday, 10 October 2018

 
 
https://fanabc.com/english/wp-content/uploads/2018/07/Di26SEjXcAAuA44.jpg
 
*ወደብ ምጽዋዕ (ባጽዕ)
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
ጥቅምቲ 10. 2018 ዓም ፈረንጂ
 
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ የኤርትራን ወደቦች ስትጠቀም የሚኖሩ የአገልግሎት ክፍያና የሎጂስቲክ አቅርቦቶችን አስመልክቶ በኢትዮጵያ በኩል ጥናት ተዘጋጀ።

ሁለቱ ሀገራት ወደ ሰላም መምጣታቸውን ተከትሎ ወደቦችን በጋራ ለመጠቀም ከስምምነት መድረሳቸው ይታወቃል።

ኢትዮጵያ የኤርትራን ወደቦች መጠቀም ያቆመችው ጦርነቱን ተከትሎ ከ20 ዓመት በፊት የነበረ ቢሆንም፥ አሁን ሀገራቱ ወደ ስምምነት ሲመጡም ኢትዮጵያ የኤርትራን ወደቦች ለመጠቀም የኤርትራን ይሁንታ አግኝታለች።

የሁለቱን ሀገራት መሪዎች ተቀራርቦ መስራትን ተከትሎ ወደቦቹን ወደ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የማምጣት ጅምር ስራዎች እንዳሉ ይነሳል።

የመንገድ ጥገናዎችን ከመጀመር አንስቶ የተለያዩ ጥናቶችን በማከናወን የምፅዋ ወደብ አሁን ባለበት ደረጃ አገልግሎት እንዲጀምር ለማድረግ ስራዎች ተጀምረዋል።

በኢትዮጵያ የማሪታይም ጉዳዮች ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ የሺ ፍቃደ፥ በመስሪያ ቤታቸው በኩል ቅድመ ዝግጅቱ በሁለት መልኩ ተከፍሎ እየተሰራ እንደሆነ ያነሳሉ።

በዚህም ለወደቡ ጥቅም ላይ የሚውሉ መሰረተ ልማቶቸን ከማሟላት አንጻር መንገድን የመሰሉ ሌሎች መሰረተ ልማቶች ይካተታሉ።

በሁለተኛ ደግሞ ኢትዮጵያ የኤርትራ ወደቦችን ስትጠቀም ቅድሚያ መመለስ ያለባቸውን ጉዳዮች በጥናት የመለየቱ ጉዳይ ጥናት እየተደረገበት ነው።

ለዚህም የባለሙያዎች ቡድን ተዋቅሮ ጥናትን አጥንቷል ያሉት ወይዘሮ የሺ፥ በዚህ ጥናት ላይ ኢትዮጵያ የኤርትራ ወደብን ስትጠቀም ክፍያው ምን ያክል ይሆናል፤ የጉምሩክና የሎጂስቲክስ አቅርቦቶችስ ምን ይሆናሉ የሚለው ምላሽ ተሰጥቶበታል ብለዋል።

የታሪፍ ጉዳይ በኤርትራ በኩልም እየተጠና ስለሆነ ሁለቱ ጥናቶች አንድ ላይ ታይተው ድምዳሜ የሚደረስበት በመሆኑ አሁን መግለጹ አስፈላጊ እንዳልሆነም አንስተዋል።

ከወደብ አገልግሎቱ ባልተናነሰ መርከቦች ከወደብ ዳርቻ ሲደርሱ የጫኑትን እቃ የማውረዱ የሎጂስቲክስ ስራም ትልቁ መከናወን ያለበት ነው።

ግዙፍ ኮንቴነሮችን ከመርከብ እያወረዱ የሚያንቀሳቅሱ ክሬኖችና ማሽኖች እዚህ ወሰጥ ይካተታሉ።

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልገሎት ድርጅት የሺፒንግ አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ካፒቴን ተፈራ በዳሳ፥ ወደቦቹ የኤርትራ እንደመሆናቸው ተጨማሪ የሎጂስቲክስ አቅርቦቶች በኤርትራ ይሰራሉ ብለዋል።

አሁን ላይ ግን በአንዴ እነዚህን መሰረተ ልማቶች ማሟላት ስለማይቻል ወደቦቹ ባሉበት ደረጃ የሁለቱን ሀገራት ጅምር ግንኙነት ለማዳበር ሲባል አገልገሎት መስጠት እንደሚችሉ ያነሳሉ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚው።

በዳዊት በሪሁን
http://www.shareme.one/wp-content/uploads/2016/03/2016-03-25-12.15.49.jpg
*ወደብ ዓሰብ
*እዘን ክልተ ስእልታት ባጽዕን ዓሰብን ወደባት ኤርትራ ብኢደ-ዋኒነይ እየ ለጢፈየን።
 
ብርሃነመስቀል

7ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 7 - ERi-TV Documentary

Dehai Events