Basic

Satenaw.com: አጋዚና ልዮ ሃይል በሞያሌ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ቦንብ ወርውርው ከባድ ጥቃት አደረሱ 3 ሰዎች ገደል፣ 64 ሰዎች አቆሰለ

Posted by: Berhane.Habtemariam59@web.de

Date: Wednesday, 18 April 2018

 

በትግራይ ጀንራሎች እና በአጋዚ ጦር የሚደገፈው የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይሎች በሞያሌ በሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ የቦንብ ጥቃት ፈፀሙ። በተወረወረውና በደረሰው የቦንብ ከሶስ በላይ ንጹሃን ዜጎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል።

በሞያሌ ከተማ በአብዲ ሊሌ የሚመራው የሱማሌ ልዩ ሀይል በፈፀመው የቦንብ ጥቃት እስካሁን አራት ንፁሀን ዜጎች ህይወታቸው አልፏል:: የቆሠሉት ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ64 በላይ ነው።

የቦንብ ጥቃቱ የደረሰው በርካታ ሰዎች ተሰብስበውበት በነበረው በሞያሌ ከተማ የአቶብስ መናሀርያ ውስጥ ነው።

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ እንዴት ኖት ደና ኖት ወይ ታርቀናል ካሉ ሁለት ሳምንት ሳይቆጠር በአብዲ ሊሌ የሚመራው የሱማሌ ክልል ልዩ ሀይል በሞያሌ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ የቦንብ ጥቃት ፈፅሟል ጥሩ ንግግር ማድረግ አገርን መምራትትና ማስተዳደርን አይወክልምና እርሶም ስልጣኔን ለቅቄያለው ከማለቶ በፊት ይህን ግድያና የማፈናቀል ጉዳይ አስቡበት:: ሌላው የወልቃይትንም እንዲሁ:: በወልቃይት ጉዳይ ላይ እርሶ ከተናገሩት በላይ አደጋ አለው ይህ አደጋ ደሞ ለማንነቱ መሰዋት ሊሆን የተዘጋጀ ማንነቱንና መሬቱን ንብረቱን ለሀያ ሰባት አመት የተቀማ የአማራ ህዝብ እንዳለ አይዘንጉት:: ይህን ጉዳይ በቶሎ መፍትሄ አበጁለት:: የህወሀትን ሰዎች ለማስደሰት ብለው በወልቃይት ጉዳይ ላይ ማኖ ነክተዋልንና ከባድ ችግር እንዳይፈጥሩ:: አልያ ከዚህ በኃላ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚደረገው ግድያ ቀጥተኛ ተጠያቂ ኖት:: ደሞ ይህንንም የዲያስፖራ የፌስቡክ ወሬ ነው እንዳይሉ::

በሀይለማሪያም ግዜ የአጋዚ ታጣቂዎችና ልዩ ሀይሎች ግድያ በክላሽ ነበር:: እድሜ ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ልዩ ሀይሎችና አጋዚዎች ተሻሽለው በቦንብ አረገውታል:: ትንሽ ከቆየን በታንክና ፀረ አውሮፕላን በመጠቀም ይጨሩስናል::

በሶማሌ ክልል በተወረወረ ቦንብ የተቆሰሉና የተጎዱ የኦሮም ብሄር ተወላጆች

በሶማሌ ክልል በተወረወረ ቦንብ የተቆሰሉና የተጎዱ የኦሮም ብሄር ተወላጆች

በሶማሌ ክልል በተወረወረ ቦንብ የተቆሰሉና የተጎዱ የኦሮም ብሄር ተወላጆች


EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events