| Jan-Mar 09 | Apr-Jun 09 | Jul-Sept 09 | Oct-Dec 09 | Jan-May 10 | Jun-Dec 10 | Jan-May 11 | Jun-Dec 11 | Jan-May 12 |

[dehai-news] Ethsat.com: Video-ለኢትዮጲያ መንግስት የሚያገለግሉ የፌደራል ፓሊስ አባላት ከዱ (must see)!

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Mon, 19 Nov 2012 23:24:00 +0100

ለኢትዮጲያ መንግስት የሚያገለግሉ የፌደራል ፓሊስ አባላት ከዱ

ህዳር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 19.11.2012


ESAT News Analysis Federal police & TPDM November 19 2012


Video-

ኢሳት ዜና:-ለኢትዮጲያ መንግስት የሚያገለግሉ የፌደራል ፓሊስ አባላት እየከዱ መሆናቸውን እንዲሁም በሁመራና በመተማ ወታደራዊ ግጭቶች በመካሄድ ላይ መሆናቸውን አንድ የፌደራል ፓሊስ ሃላኢ ገለፁ። ይህም በምስልና በድምፅ ይፋ ሆኗል። በሌላምበኩል በሰሜን ኢትዮጲያ ጠረፋማ አከባቢዎች ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች አንዱ የሆነው ትሕዴን ሰራዊቱን በክፍለ ጦር ደረጃ ማዋቀሩን ለቀመንበሩ ለኢሳት ገልፀዋል።

በምስራቅ ኢትዮጲያ በኦጋዴን አከባቢ የፌደራል ፖሊስ አባላትን ሰብስበው ገለፃ ያደረጉት የፌደራል ፖሊስ ሃላፊ ፖሊሶች እየከዱ ማስቸገራቸውን ገልፀዋል። ለሰባት ዓመታት ለማገልገል የገቡትን ሥምምነት ጥሰው በመኮብለላቸው እየያዝን ጅጅጋ እስር ቤት እንከታቸዋለን ሲሉ አሳስበዋል። በምስራቅ ካለው ይልቅ የሰሜኑ ችግር የሰፋ መሆኑን በሁመራና በመተማ ዘወትር ግጭት በመታየት ላይ መሆኑን አብራርተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በሰሜን ኢትዮጲያ ነፍጥ ካነሡት ሃይሎች አንዱ የሆነው ትሕዴን ተከታታይ ወታደራዊ ጥቃት ሲያደርስ መቆየቱን ሊቀመንበሩ አስታውቀዋል። የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትሕዴን) ሊቀመንበር ታጋይ ሞላ አስገዶም ለኢሳት በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት ትሕዴን ወታደራዊ ተጠናክሯል ከሌሎች የኢትዮጲያ ሃይሎች ጋር ግንባር በመፍጠርም በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት በሃይል ለመጣል እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አመልክተዋል ።

 

Received on Mon Nov 19 2012 - 21:28:44 EST
Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2012
All rights reserved