Satenaw.com: የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴና ከፍተኛ የካድሬ አመራርና ታማኝ ምልምል ካድሪዎችና ስብስቦች

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam59_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Fri, 4 Nov 2016 21:31:15 +0100

የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴና ከፍተኛ የካድሬ አመራርና ታማኝ ምልምል ካድሪዎችና ስብስቦች

[ከአስገደ ገብረስላሴ መቀለ ]

የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴና  ከፍተኛ የካድሬ አመራርና ታማኝ ምልምል ካድሪዎች  ፣ ስብስቦች  አመት ሙሉ በስብሰባ ተንጠው ተንጠው ውጤት አልባ ሆነዋል !!!!!
TPLF (1)የህወሐት ስራ አስፈጻሚና ካሁን በፊት ከተለያዩ የማእከላይ ኮምቴ ደረጃ   ወይ  እርከን  ተወግደው  የነበሩ   የማይድነውን   ህወሓት ለመዳን ተሰባስበው ላይና ታች  እያሉ ከርመው የትግራይና የአዲስአበባ ቡዱን በሚል ተከፋፍለው  ሳይግባቡ  በመክረማቸው ፣ ልንስማማ ባለመቻላችን  የሁለቱ ቡዱን   የሚለያዬን ሀሳብ ይዘን  የትኞቹ ናቸው  ሀቀኞች ለሚለው ፍርዱ  እንዲ ሰጡን ላንድጊዜና ለመጨረሻ  ያ እንደፈለጉ እንደፈረስ የሚነዱት ካድሬ   ከመላው ኢትዮጱያ በመሰብሰብ ፣ ጡሮታ የወጡና ያልወጡ የህወሐት የጦር መኮኖች  ነበር  ጭምር ሊገላግላቸው በመጥራት ፣ አስቀድመው በመቀሌ ከተማ   በቡዱን በቡዱን ከፋፍለው  ከ120   ገጽ በላይ  የያዘ  ጽሁፍ  ሰጥተው  ሲያዋያዩና  ሲሰበኩ  ከሰነበቱ በኃላ በዛሬው 21 / 2 /2009  ዓ  ም በመቀሌ ሰማአታት ሐወልቲ  ተሰብስበዋል ። በዚህ ስብሰባ የምንጠብቀው  የህወሐትና ቤተሰቡቹ ወደ ታችና ወደ  ወጎን ለማጥራት ሳይሆን  አንደኛ   ለነዛ ያረጁና  ያፈጁ በሙሱና በተባላሸ ስነምግባር የበሰበሱ  ተከብረውና ተጠብቀው እንዲኖሩ  ለመረጋገጥ  የሚያስችሉ   ሎሌዎች ሊመጡ ይችላሉ ። ሁለተኛ የአባይ ወልዱ ና መዋቅሩ ያስወግዳሉ ።በተረፈ የስርአት ለውጥ የሚያመጣ ነጻነትና የሀገራችን ለአሏውነት ፣ የዜጎች የተሟላ መብቶች   የሚያስጠብቅ  ለውጥ  አያመጡም  ። ሰወስተኛ  ልክ እንደ ኦሆዴድ  የህወሐት  አማራር አጃቢ የነበሩ ፣ ዘበኛ የነበሩ ከስቪል ሰርቢስ ለስሙ ቢኤና ማሰተርስ ዲግሪ   የተቸረላቸው ግለሰዎች ፣ ጥቂት አድርባይ ሙሁራን ነን የሚሉ ፣ ግን ደግሞ  ለሚቀዬረው ያረጀና  ያፈጀ ፣በሙሱና ለተባላሸው የህወሐት አመራር ዘበኛ የሚቆሙ ሰዎች የአርትፍሻል ቃለማሀላ  ሲፈጽሙ እናይ እንሆናለን  ። በፈደራል    ደረጃም እርግጥ  አብዛኞቹ ለጥገናዊ ለውጥ መጠገኛ አብዛኞዎቹ በስቢል ሰርቢስ በሞቅሞቅና በቻይና አይዶሎጁ ካድርነት የተካኑ   የሙሁራን ለውጥ ሊያደርጋሉ ። ሆኖም  ግን በፖለቲካ አስተሳሰብ  ኢህአደግ እስከነዳቸው ድረስ የሚያመጡት የስርአት ለውጥ የለም ።

የህወሐት ማእከላይ ኮሚቴ ውስጣችን ስለበሰበስን በጥልቀት  እንታደስ ብሎ ስብሰባ ከጀመረ እንሆ አመትን አስቆጥራል ።
ሆኖም ግን በሀገራችን ያሉ የኢህአደግ ቡዱኖችና እነሱ የሰራቸው የአናሳ ቢሄረሰቦች ፓርቲ መሪዎች ቢታደሱ  ፣ ቢታደሱ ውጤቱ ባዶ ነው ።

በእኔ እምነት ኢህአደግ ሊታደስ ከሆነ   በሀገራችን   ያለ አድላዊ የሆነ የምርጫ ህግና ስነምግባር ፣ ነባሩ የምርጫ ቦርድ  ከነመዋቅሩ ፈርሶ እንደአዲስ  መዋቀር አለበት ። ሁለተኛ አሁን ተፈጥሮ ላለው ሀገራዊ   ቀውስ  100% ኢህአደግ በመኖፖል የያዘው ፓርላማ መቀየር ሲችል ብቻ ነው ።

አሁን የሀህወሐት አማራርና ከፍተኛ የከድሬዎች ስብስብ በስብሰባ  መናጥ ውጤቱ ከበሬ ወተት አልቦ መጠጣት  ሆኖ ይታየኛል ።
በተለይ በህወሀት ውስጥ ሀቀኛና ነጻ ተመራማሪ ሙሁራን  ወደ የአመራር መድረክ ሊመጡ አይታሰብም።
ይቀጥላል !!!!!…

 
Received on Fri Nov 04 2016 - 16:36:19 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved