Mereja.com: የህወኃት ጊዜያዊ የኃይል አሰላለፍና ትኩረቱ! ቀደም ብሎ ከመከላከያ ተሰናብተው የነበሩ የጦር መኮነኖች ( ፃድቃን፤ አበበ፤ ታደሰ) አለቃ ፀጋየን እንደሚያማክሩ ተሰምቷል።

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam59_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Fri, 14 Oct 2016 00:49:31 +0200

የህወኃት ጊዜያዊ የኃይል አሰላለፍና ትኩረቱ! ቀደም ብሎ ከመከላከያ ተሰናብተው የነበሩ የጦር መኮነኖች ( ፃድቃን፤ አበበ፤ ታደሰ) አለቃ ፀጋየን እንደሚያማክሩ ተሰምቷል።

የህወኃት ጊዜያዊ የኃይል አሰላለፍና ትኩረቱ!
ይህ መረጃ ለህወኃት /ኢህአዴግ/ ቅርበት ካላቸው ሰወች የተቀበልኩት ነው። መተንተንና መፍቴ ማበጀት የተጠቃሚው ስራ ነው።
-የህወኃት (ኢህአዴግ) ማዕከላዊ አመራር ሁሉም በፀጥታ ስራው ላይ ተሰማርቷል። ህወኃት/ ኢሀአዴግ/ ሙሉ አቅሙን እየተጠቀመ ነው ማለት ነው።
-የፀጥታ ስራው ዋነኛ ትኩረት ጎንደር፤ ጎጃምና አዲስ አበባ ዙሪያ ሁኗል። የማዕከላዊና የምዕራብ እዞች ሙሉ ኃይላቸውን ጎንደርና ጎጃም ላይ አድርገዋል። አንድ ክ/ጦር የሚገመት የፌደራል ፖሊስና አንድ የአግአዚ ኮማንዶ ሻለቃ በተደራቢነት ተመድቧል።
-አዲስ አበባ ዙሪያ 5 የአግአዚ ኮማንዶሻለቆች፤ 2 የአግአዚ ልዩ ኃይል ሻለቆች፤ የአዲስ አባባ ዙሪያ ጥበቃ ክ/ጦር ከሰሜን ዕዝ የተላኩ 3 እግረኛ ሻለቆች እና 2 ክ/ጦር የሚገመት የተለያየ ሙያ ያለው የፌደራል ፖሊስ፤
-በአዲስ አበባ ዙሪያም ሆነ ጎንደርና ጎጃም በመጠን ለመገመት የሚያስቸግሩ በርከት ያሉ ብረት ለበስ ተሽከርካሪወችና በተሽከርካሪ ላይ የተጠመዱ መካከለኛ ርቀት ያላቸው መሳሪያወች ከየግንባሩ ተስበዋል።
-በዚህ የኃይል አሰላለፍ የተነሳ የኢትዮ ኤርትራ ግንባር መሳሳቱ ሌላ ጭቅጭቅም እንደፈጠረባቸው ተሰምቷል። እንደመፍትሄም በርከት ያለ የትግራይ ሚሊሻን ወታደራዊ ልብስ በማልበስ በደንበሩ እንዲከትም ተወስኗል።
የማዕከሉን ኮማንድ ፖስት በስራ አስኪያጅነት አለቃ ፀጋየ በርሄ ተመድቦበታል። በአባልነት የደህንነት፤ የመከላከያ፤ ፖሊስ ፤ አዛዦችና ምክትሎቻቸው ተመድበዋል፤ ካሳ ተክለብርሃንም የዚሁ ኮሚቴ አባል መሆኑ ተሰምቷል( ይህ ኦፕሬስናል ኮሚቴው መሆኑ ነው)።
-ኃይለ ማሪያም የሚመራው ደግሞ ሌላ የፖለቲካ ውሳኔ የሚሰጥ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ በመባል የሚታወቀውን አደራጅቷል..ይህ ለመጠቀሚያነትና ለህጋዊ ሽፋንነት የሚያገለግል ከአራቱም ድርጅቶች የተውጣጣ የይስሙላ አመራር መሆኑ ነው።
-ቀደም ብሎ ከመከላከያ ተሰናብተው የነበሩ የጦር መኮነኖች ( ፃድቃን፤ አበበ፤ ታደሰ) አለቃ ፀጋየን እንደሚያማክሩ ተሰምቷል።
በሶስቱም የአደጋ አካባቢወች (ወያኔወች እንደሚሉት ማለቴ ነው) ያለውን ዝርዝር የምደባና የኃይል ሚዛን ለማወቅ እየጣርኩ ነው።
ህወኃት አገራችን ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የህዝብ ተጋድሎ በተገቢው ሁኔታ ገምግሞ የመጨፍለቂያውን ስትራቴጅ መንደፉን ነው የምንረዳው፤ እናም ይህንን የጥፋት ስትራቴጅ አምክነን ባጭር ጊዜና ባነሰ ኪሳራ ድል መቀናጀት የምንችልበትን ዘዴ መፈለግ አለብን።

Received on Thu Oct 13 2016 - 17:28:36 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved