Ethsat.com: “የቢሾፍቱ እልቂት ከደረሰ በሁዋላ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአጋዚ ወታደሮች ተገድለዋል”

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam59_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Mon, 10 Oct 2016 23:53:39 +0200

“የቢሾፍቱ እልቂት ከደረሰ በሁዋላ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአጋዚ ወታደሮች ተገድለዋል”

October 10, 2016

Watch these news:

ESAT DC Morning News Mon 10 Oct 2016

http://video.ethsat.com/?p=29341

ESAT Daily News Amsterdam October 10,2016

http://video.ethsat.com/?p=29343

መስከረም ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያውያንንና የአለምን ህዝብ ድንጋጤ ውስጥ የከተተው የቢሾፍቱ እልቂት ከተከሰተ በሁዋላ የተነሱ ህዝባዊ ንቅናቄዎችን ለማፈን የአጋዚ ወታደሮች በወሰዱት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መገደላቸውን ከተለያዩ አካባቢዎች የኢሳት ወኪሎች ያሰባሱበዋቸው መረጃዎች አመልክተዋል።

ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ በተካሄደባቸው በምስራቅ ሸዋና በምዕራብ አርሲ እልቂቱ ከፍተኛ እንደነበር ወኪሎቻችን ገልጸዋል።

በሊበን ዝቋላ ወረዳ ለተከታታይ 5 ቀናት በተደረገው ህዝባዊ ትግል 29 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል። ተቃውሞው በወረዳው ዋና ከተማ አዱላላ እና የወ/ሮ አዜብ መስፍን እንደሆነ በሚነገርለት የመስኖ ስራና የከብት ማደለቢያ ቦታ ሲሆን፣ በተለይ አርብ እለት አርሶአደሮች  ባስነሱት ተቃውሞ አጋዚዎች ከአርሶአደሮች ጋር የተኩስ ለውውጥ አድርጓል። እስር ቤቱን በማቃጠል እስረኞችን ያስፈቱ ሲሆን፣ ከ90 በላይ የጦር መሳሪያዎችን በመውሰድ ወታደሮችን ገድለዋል።

ተቃውሞው ከቁጥጥር ውጭ የሆነበት ገዢው ፓርቲ ተጨማሪ የአጋዚ ወታደሮችን በማሰማራት የጅምላ ግድያ ፈጽሟል።

አብዛኛው ህዝብ ጫካ ውስጥ መግባቱን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ አካባቢው በአገር ሽማግሌዎች እየተዳደረ ነው መሆኑንም ገልጸዋል።

በሊበን ቅዳሜ ሩግቻ በምትባል ቀበሌ ደግሞ አማራዎችንና ኦሮሞችን ለማጋጨት የሞከረው ግጭት ከሽፎ አማራውና ኦሮሞው በአንድነት ተቃውሞውን ሲያሰማ ሰንብቷል። በአካባቢው ያሉ መንገዶችን አሁንም ደረስ ተዘግተዋል።

በአርሲ ነገሌ በተለያዩ ቦታዎች በተፈጸሙ ጭፍጨፋዎች ደግሞ ከመቶ በላይ ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ሄረሮ ላይ ባለፈው ቅዳሜ ደግሞ ህዝቡ አትግደሉን በማለት ወደ አደባባይ ሲወጣ አጋዚዎች በወሰዱት እርምጃ 23 ሰዎች ተገድለው አስከሬናቸው ከስንዴ ማሳ ማሀል ተገኝቷል።

ከአርሲ ነገሌ 48፣ አጄ፣ ቡራና ሻላ 30 የተገደሉት በየቀኑ ከሚገደሉት አንዳንድ ሰዎች ጋር ሲደማመር ከመቶ በላይ መሆኑን የሚገልጹት ነዋሪዎች ፣ በዚሁ አካባቢ በወላይታና ኦሮሞ መካከል ግጭት ለመፍጠር መሞከሩን ገልጸዋል ። በመላ አገሪቱ የሚታየው ውጥረት ያሰጋው አገዛዙ  ለ6 ወራት ወይም ከዚያ በላይ ሊቆይ የሚችል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጓል።

*******************************************************************************

ገዢው ፓርቲ ከወጣቶች ጋር እርቅ ለመፍጠር ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

October 10, 2016

መስከረም ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ አንዳሳ በሚባለው አካባቢ ከጎበዝ አለቆች ጋር እርቅ መፍጠር እንፈልጋለን በሚል ገዢው ፓርቲ ያቀረበውን ጥያቄ ወጣቶች ውድቅ አደረጉት። ወጣቶቹ፣ ማንኛውም ሰው፣ ፖሊስም ሆነ ወታደር ረብሻ ቢፈጥር እርምጃ እንወስዳለን በማለት የተማማሉ ሲሆን፣ አካባቢያችንን ከእንግዲህ እኛ የመረጥናቸው እንጅ እናንተ የምትመርጡት አያስተዳድረውም በማለት በፖሊሶች እና በአመራሮች ላይ ድንጋይ በትኖ አባሯቸዋል።

ሰባት አሚት በሚባለው አካባቢ ደግሞ የቀበሌ አመራሮችን ለመምረጥ የተደረገው ሙከራ ከሽፏል። የአካባቢ ካድሬዎች ምርጫ እናስደርጋለን ብለው ቢሄዱም ህዝቡ ፈቃደኛ ሳይሆን የቀረ ሲሆን፣ የቀበሌውን ቁልፍ በመቀየር ቀበሌውን በእጁ አስገብቷል።

Received on Mon Oct 10 2016 - 16:32:44 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved