VOA.com:Audio- “የገደሉት ልጄ አስከሬን ላይ ቁጭ በይ ብለው ደበደቡኝ” ደምቢ ዶሎ የተገደለ ወጣት እናት

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam59_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Thu, 8 Sep 2016 00:35:12 +0200

“የገደሉት ልጄ አስከሬን ላይ ቁጭ በይ ብለው ደበደቡኝ” ደምቢ ዶሎ የተገደለ ወጣት እናት

September 7, 2016
Listen this from VOA:
www.youtube.com/watch?v=wSLTiW6duCA
BBN TV Breaking News - September 7, 2016
https://www.youtube.com/watch?v=eqOsUEJ4x10
 
ሌላው ወጣት ኢብሳ ሩንዴ ደግሞ ግቢው ውስጥ ቆሞ እንዳለ ተኩሰው ገድለውታል ሲሉ የደምቢ ዶሎ ነዋሪ አስታወቀዋል። አስከሬኑን ወደ ሆስፒታል በመውሰድ ላይ እንዳሉ የመንግሥት ታጣቂዎቹ አስቁመው ወደቤት መልሷቸው ሲሉ ነዋሪው አክለው አመልክተዋል።

ከሟቾቹ መካከል የአስራ ስድስት ዓመቱን ወጣት የሃይሉ ኤፍሬም እናንት ወይዘሮ ታደሉ ተማምን በስልክ አግኝተን የልጃቸውን መገደል ሰምተው እንደሆነ ጠየቅናቸው።

“ ቤት ውስጥ ነበርኩ ። እሱ ደግሞ ከልጆች ጋር ሊጫወት ወጣ ብሎ ነበር። ከተማ ውስጥ ብጥብጥ ተነሳ ሲባል መሯሯጥ ጀመሩ። ከፊት ይሮጥ የነበረውን ልጄን መትተው ጣሉብኝ። ጓደኞቹ መጥተው ሲነግሩኝ ሮጬ ሄድኩ።ስደርስ ልጄ ሜዳ ላይ ተዘርግቷል ። አንድ ያለኝ ተስፋ እሱ ነበር። እንደ አባትም ሆኖ በባሌም ምትክ የቀን ሥራ እየሰራ የሚረዳኝን ልጄን ነው ያጣሁት” ብለዋል።

ታጣቂዎቹ ጥለውኝ ሲሂዱ ብጮህ ሰዉ ሁሉ ፈርቶ ሸሽቱዋል። እኔና ሴቷ ልጄ ሜዳ ላይ ብቻችንን አለቀስን ያሉት የሟቹ ወጣት እናት አንገቱ ላይ መትተው ነው የገደሉብኝ ብለዋል። በኃላም ጎረቤቶች ተሰብሰበው ረድተውኝ ልጄን ሸኙልኝ። የአስከሬን ሳጥን መግዣ እንኳን አልነበረኝም ብለዋል።

ከቂለም ወለጋ የፖሊስ አዛዥ ምላሽ ለማግኘት ደውለን ነበር። ይሁን እንጂ አዛዡ ኮማንደር ቦደና ስልኩን ካነሱ በኃላ ዘግተውታል።

Received on Wed Sep 07 2016 - 17:14:17 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved