Ethsat.com: ነውራም ሓሶት ወያኔ ትግራይ እንክቃላዕ! የተዛቡ ምስሎችን በድረገጾቸው ላይ የለጠፉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴርና ኢቢሲ አንባቢዎችን ይቅርታ ለመጠየቅ ተገደዱ።

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Tue, 17 May 2016 14:40:39 +0200

ነውራም ሓሶት ወያኔ ትግራይ እንክቃላዕ!

ለባማት ኣቦታትና "ሓሶትን ስንቅን'ሲ እናሓደረ ይፈኩስ" ኢሎም ይምስሉ። እዚ ኩነት እዚ ናይ ሎሚ ሓዲሽ ተርእዮ ጥራሕ ዘይኮነስ ናይ ሓሳውን  መደናገርን ባህርያት ናይ ግዜኡ ገዛኢ ደርቢ ኢትዮጵያ ዓሌታዊ ጉጅለ ህውሓትን ብፍላይ  ጎይቶቱን መወልቱን ናይ ዓለምና ግዳማውያን ሓይልታት ድማ ብሓፈሻ መቐጸልታ ናይ'ቲ ን18 ዓመታት ኣንጻር ሃገርና ኤርትራን ህዝባን ከካይድዎ ዝጸንሑን ሕጂ'ውን ዝቕጽልዎ ዘለዉ ከንቱ ናይ ሓሶት ጸለመን ናይ ስነ-ኣእምሮኣዊ ኲናትን ቅሉዕ ተጻብኦን እዩ። እዚ እኳ ንማንም ኤርትራዊ ዘገርም ኣይኮነን፣ እቲ ምንታይ'ሲ ዝላደናሉን ጽቡቕ ጌርና ስለ እንፈልጦን። እቲ ዘስደምምን ይቕሬታ ዘይበሃሎን ግን ገለ ኣካላት ኤርትራውያን ኢና በሃልቲ ኣብ ትሕቲ'ዚ ነውራምን ዓሌታውን ከዳምን ስርዓት ተዓሲቦም ንዕኡ ከቃናጅዉን ከገልግሉን ጽሓይ ዝዓርቦምን ኣንጻር ሃገሮምን ክቡር ታሪኽ ህዝቢ ኤርትራ ለይትን መዓልትን ክልፍልፉን ዓጀወጀው ክብሉን  ክሕስዉን ምዕዛብና እዩ። ይኹን እምበር "በትሪ ሓቅስ ትቐጠን እምበር ኣይትስበርን" ከም ዝበሃል፣ እዚ ኩሉ ሸርሒን ሓሶትን ድማ ከም'ቲ ናይ ትማሊ ግዜኡ በሊዑ ምስቶም ዋናታቱ ኣብ ናይ ታሪኽ ጐሓፍ ገረወኛ ተደርብዩ ክምሽምሽ ምዃኑ ፍጹም ዘጠራጥር ኣይኮነን።

ዓወት ንሓፋሽ!

ዘልኣለማዊ ዝኽሪ ንስውኣትና!

ብርሃነ ሃብተማርያም

የተዛቡ ምስሎችን በድረገጾቸው ላይ የለጠፉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴርና ኢቢሲ አንባቢዎችን ይቅርታ ለመጠየቅ ተገደዱ።

ኢሳት (ግንቦት 8 ፥ 2008)

May 17, 2016

የመንግስት ኮሚውኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን  ከአርበኞች ግንቦት ሰባት የተማረኩ ጦር መሳሪያዎችና የመንገድ ግንባታ ናቸው በሚል በድረገጾች ላይ የተለጠፉ ምስሎች የኢትዮጵያ ያልሆኑ መሆናቸውን በማስመልከት በማህበራዊ ድረ-ገጽ ተጠቃሚዎች በደረሰባቸው ጫና ምስሎቹን ማንሳታቸው ታወቀ።

የመንግስት ኮሚውኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትና በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮሮፖሬሽን በድረገጾቻቸው ላይ ያሰራጯቸው ሁለት ምስሎች በኢትዮጵያ ውስጥ ያልተነሱ መሆናቸውን ማህበራዊ ድረገጽ ተጠቃሚዎች ስለደረሱባቸው መስሪያ ቤቶቹ ይቅርታ ለመጠየቅ ተገደዋል።

አዋሽ ወልዲያ፣ ሃራ ገበያ ተብሎ በኮሚውኒኬሽን ጽ/ቤት የተሰራጨው ምስል Devil’s Slide Tunnel ተብሎ የሚጠራው  ፓሲፊካ በሚባል ካሊፎርኒያ አሜሪካ ግዛት የሚገኝ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ኮሚውኒኬሽን ጽ/ቤት ይህንን ምስል በወልዲያ አካባቢ በመንግስት ወጪ የተሰራ ነው በማለት ለአንባቢ የተሳሳተ ምስል አቅርቦ እንደነበር ይታወቃል።

ሆኖም የኮሚኔኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያሰራጫቸው የምስሎች መረጃ፣ የተሳሳቱና ከጽሁፎቹ ጋር የማይገናኙ በመሆኑ ይቅርታ እንጠይቃለን ሲል የፌስቡክና ትዊተር ድረ-ገጽ ተከታዮችን ይቅርታ ጠይቋል።

በተመሳሳይ መልኩም የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኤርትራ ከሚታገዙ አሸባሪ ድርጅቶች የተማረከ ነው በሚል የጦር መሳሪያ የሚያሳይ ምስል ትክክል እንዳልሆነና፣ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በቀጥታ እንደወሰደው ገልጾ፣ አንባቢዎቹን ይቅርታ ጠይቋል። ለተፈጠረው ስህተት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ተጠያቂ ነው ሲልም ክስ አቅርቧል።

ከኤርትራ የሚታገዙ አሸባሪዎች ላይ የተማረከ መሳሪያ ነው በማለት ኢቢሲ ያሳየው ምስል በ2004 በኢራቅ ፋሉጃህ ግዛት በ82ኛው አየር ወለድ ክፍለጦር የተማረከ መሆኑን የማህበራዊ ድረ-ገጽ ተሳታፊዎች እጅ ከፍንጅ ይዘዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ተቋማት አንባቢዎችን ሲዋሹ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳልሆነና፣ ብዙ ጊዜ የሚያቀርቡት ዘገባ በእውነት ላይ የተመሰረተ እንዳልሆነ የማህበራዊ ድረገጽ ተሳታፊዎች በጻፏቸው አስተያየቶች ተመልክቷል።

 
Received on Tue May 17 2016 - 08:40:39 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved