Zehabesha.com: በአ.አ. 17 የፖሊስ አባላትና 1 የወረዳ ባለስልጣን ተገደሉ – መንግስት የሞተው 1 ፖሊስና 1 ባለስልጣን ብቻ ነው እያለ ነው

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Thu, 30 Jun 2016 14:53:06 +0200

በአ.አ. 17 የፖሊስ አባላትና 1 የወረዳ ባለስልጣን ተገደሉ – መንግስት የሞተው 1 ፖሊስና 1 ባለስልጣን ብቻ ነው እያለ ነው

13567117_1648833925438454_8858208581294920612_n

(ዘ-ሐበሻ) በመላው ኢትዮጵያ ገዢው የሕወሓት መንግስት ሕዝብን በየፊናው እያሰቃየ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሕዝብ የራሱን እርምጃ በባለስልጣናቱና ጠመንጃን በታጠቁ ሰዎች ላይ መወሰድ ጀምሯል:: ዛሬ በአዲስ አበባ የነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 17 የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት እና አንድ የወረዳ ከፍተኛ ባለስልጣን መገደላቸው ታውቋል::

በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ በተለምዶው ሃና ማርያም አካባቢ የሕዝብን ቤት ለማፍረስ የተያዘውን እቅድ ለማስፈጸም የከተማው አስተዳደር ከሕዝቡ ጋር በተፋጠጠበት ወቅት ከሕወሓት ደህንነት ቢሮ የተላኩ ሰምቶ አደሮች ባነሱት ግርግር የተነሳ; ተነሳ በተባለው ግጭት ፖሊሶች ወደ ህዝብ መተኮስ በመጀመራቸው ህዝቡ የራሱን እርምጃ በመውሰድ በ17 የፖሊስ አባላት እና በወረዳው ባለስልጣን ላይ እርምጃ ወስዷል::

ከህዝቡም ወገን በርካታ ሰዎች እንደቆሰሉ የተሰማ ሲሆን ፖሊሶችም እንዲሁ እንደተጎዱ መረጃው ይጠቁማል::

ይህንን ብጥብጥ ህዝብ እንደጀመረው ለማስመስል የደህንነት አባላቱ ተንኩሰው መሰወራቸውን የሚናገሩት የአይን እማኞች ሆን ብሎ ቤቴ አይፈርስብኝም ያለውን ህዝብ ለማሸማቀቅ ነው ብለዋል::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ መንግስት በዛሬው ብጥብጥ 1 ፖሊስ እና አንድ የወረዳ ባለስልጣን መገደሉን ገልጾ ጥቃቱን ሕገወጦች ያደረሱት ሲል ወንጅሏል:

Received on Thu Jun 30 2016 - 07:32:10 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved