DW.com: የኢትዮ-ኤርትራ ዉዝግብና ግጭት

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Sun, 26 Jun 2016 22:12:51 +0200

የኢትዮ-ኤርትራ ዉዝግብና ግጭት

ኢትዮጵያና ኤርትራ ለረጅም ጊዜ ጋብ ያለ ይመስል የነበረዉን የድንበር ላይ ግጭት እንደገና የጀመሩ ይመስላል። ሰኔ አምስት በተለይ ጾረና በተባለዉ ግንባር የሁለቱ ሃገራት ጦር ተጋጭተው ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ ኃይል ከሁለቱም ወገን መገደሉና መቁሰሉ ተዘግቦአል።

June 26, 2016

Bildergebnis für Ethio-eritrea disputed border

ዉይይት፤ የኢትዮ-ኤርትራ ዉዝግብ: እዝህ ታች ሰንሰለቱ ጫን ኣርጋችሁ ኣዳምጡት።

http://www.dw.com/am/%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE-%E1%8A%A4%E1%88%AD%E1%89%B5%E1%88%AB-%E1%8B%89%E1%8B%9D%E1%8C%8D%E1%89%A5%E1%8A%93-%E1%8C%8D%E1%8C%AD%E1%89%B5/a-19357726?maca=amh-standard_feed-amh-11646-xml

ግጭት ቀድሞ የጀመረዉ ወገን በግልፅ አልታወቀም። የአስመራና የአዲስ አበባ መንግሥታት ግን በግጭቱ መጀመር እርስ በርስ እየተወቃቀሱ ነዉ። ከሰኔ 5ቱ ግጭት በኋላ በድንበር አካባቢ ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን የተለያዩ ምንጮች ይዘግባሉ።
 

የኤርትራ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ አማካሪ አቶ የማነ ገብረአብ ለተመድ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ተመልካች ም/ቤት ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ኤርትራን ለመዉረር እየተዘጋጀች ነዉ በማለት ወቅሰዋል። የተመድ እና ዩኤስ አሜሪካ ሁለቱ ሃገሮች ወደ ጦርነት እንዳይገቡና ነገሮች እንዳይባባሱ በትዕግስት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። እስካሁን በድንበር አካባቢ ያለዉ ዉጥረት እየተባባሰ መሆኑን የተለያዩ ምንጮች ይናገራሉ። ዉጥረት ስላጠላበት የኢትዮጵያ ኤርትራ ወቅታዊ ሁኔታ እንዲወያዩልን የጋበዝናቸዉ፤ መቀመጫዉን አዲስ አበባ ያደረገዉ ዓለማቀፍ የምክክርና የጥናት የትብብር ማዕከል ባልደረባ አምሳደር ተፈራ ሻዉል፤ በኢትዮጵያ ኤርትራ ጉዳይን በቅርበት የሚያዉቁት በለንደን ነዋሪ የሆኑት ኤርትራዊ አቶ አሉላ አብርሃ እንዲሁም ነኖርዌ ነዋሪ የሆኑት የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ አቶ ዩሱፍ ያሲን ናቸዉ። ሙሉ ዉይይቱን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

 
Received on Sun Jun 26 2016 - 16:12:52 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved