Ecadforum.com: ሰበር ዜና… በደቡብ አፍሪካ በወያኔ ኢንባሲ አቀናባሪነት የተጠራዉ የኤርትራ መንግስት የመቃወም ሴራ ከሸፈ!

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Sun, 26 Jun 2016 19:28:43 +0200

ሰበር ዜና… በደቡብ አፍሪካ በወያኔ ኢንባሲ አቀናባሪነት የተጠራዉ የኤርትራ መንግስት የመቃወም ሴራ ከሸፈ!

ልኡል አለም

June 23, 2016

የትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን በደቡብ አፍሪካ ለሚኖሩ ከወያኔ መንግስት ጋር በመተባበር የኤርትራንና የኢትዮጵያን ህዝብ በመሰለል እና በተለያየ ጥቅማ ጥቅም ለሚተዳደሩ ጥቂቶች ያመቻቸውና በዛሬዉ እለት ፕሪቶሪያ ከተማ ላይ የተባበሩት መንግስታት ቢሮ አካባቢ ሊደረግ የነበረዉ ተቃዉሞ ከሽፏል።

ወያኔ ይህንን ተቃዉሞ ሰልፍ ለማመቻት 70 ሺ ራንድ ወጪ ያደረገ ከመሆኑም ባሻገር የትራንስፖርትና የምግብ እንዲሁም የመጠጥ ወጪዎችን መድቦ ፈሰስ ያደረገ ከመሆኑ በተጨማሪ ከስብሰባዉ በሗላ በኢትዮጵያ ዉስጥ ልዩ የእራት ግብዛ ተቃዉሞዉ ላይ ለተሳተፉ ትዉልደ ኤርትራዊያንን በተለይም ንብረታቸዉ የተመለሰላቸዉ የሚባሉትን በጥቅምና በተስፋ ማነቆ የታሰሩ ግለሰቦችን ባጠቃላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አድርጎ ነበር።

ይህንን የተቃዉሞ ስብሰባ በማቀናጀቱ በኩል በደቡብ አፍሪካ ዉስጥ ነዋሪ ከሆኑ የወያኔ ጥቅም ተጋሪዎች መካከል ተስፉ ምስግና በቀለ ወይም አንክል የተባለ ትዉልደ ኤርትራዊ ከወያኔ ወንበዴዎች ጋር በጋር የባልትና ንግድ የሚሰራና በሐዋላ የገንዘብ ዝዉዉር የሚተዳደር ግለሰብ እና አማኑኤል ወልዱ የተባለ በትዉልድ ኤርትራዊ የሆነ ከወያኔ ኢንባሲ በስለላ ጉዳዮ በመተሳሰሩ ምክንያት በወር 10.000 ራንድ የሚከፈለዉና በዚሁ እኩይ ተግባር የሚተዳደር የህዝብ ጠላት ነዉ።

በመሆኑም የደቡብ አፍሪካ ሜትሮ ፖሊስ አገልግሎት ( Department Of Metro Police ) ህወሃታዊ ትዉልደ ኤርትራዊያን ዛሬ ዛሬ 06/23/2016 ሰልፍ እንዲወጡ ፈቅዶ የነበረ ሲሆን በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ይህንን የሰላማዊ ሰልፍ ያዘጋጀዉ የኢትዮጵያ ኢንባሲ መሆኑን ለሚመለከተዉ አካል በማሳወቅና በአሁን ወቅት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ ላይ በተቀሰቀሰዉ የህዝብ አመጽ ምክንያት ሰልፉ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳይሄድ በሚል ሁኔታ ለደቡብ አፍሪካ ሜትሮ ፖሊስ ዲፓርትመንት ማስጠንቀቂያ በመስጠታቸዉ ሰልፉ ተሰርዟል።

የኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ አስከፊ ሁኔታ ላይ በሚገኝበትና መሪዎቻችን አለምን በልመና ባስጨነቁበት በዚህ ወቅት ላይ ህወሃት ኤርትራዊያን በመንግስታቸዉ ላይ እንዲያምጹ ከፍተኛ ወጪ በማዉጣት የህዝባችንና የሐገራችንን ሐብታና ንብረት ማባከኑን ተያይዞታል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

 
Received on Sun Jun 26 2016 - 13:28:44 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved