Ecadforum.com: በትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን ጸብ አጫሪነት የተቆሰቆሰዉ ጦርነት ከፈተኛ ዝግጅት እየተደረገበት ይገኛል!

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Sun, 19 Jun 2016 02:06:41 +0200

በትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን ጸብ አጫሪነት የተቆሰቆሰዉ ጦርነት ከፈተኛ ዝግጅት እየተደረገበት ይገኛል!

በልኡል አለም

በኢትዮጵያ ወታደራዊ ደህንነት በኩል በከፍተኛ ሚስጥር እንዲያዝ በታቀደ ሁኔታ በሰሜኑ እዝ ዉስጥ ከተጠቃለሉት ክ/ጦሮች በተጨማሪ ከማእከላዊ እዝ ወታደሮችና ሜካናይዝድ ብረት ለበስ ሰራዊቶች እየተደራጁ ይገኛሉ።will not escalate clash with Eritrea

በጎንደር በኩል በተለየ ሁኔታ ከሁመራ እስከ ኡማህ ጅር እንዲሁም በሰሜን 14.718326 አየር ካርታ ዳር ዳሩን በምያዝ ከአፋር ዞን 1 እስከ አፋር ዞን 2 ብሎም እስከ አድዋ ከድዋ እስከ አዲ አቡን ድረስ ሰራዊት ለማሰማራት ታቅዶ የሐይል እጥረት መከሰቱን መከላከያ ምንጮች ጠቁመዋል።

በኤርትራ በኩል ከፍተኝ ጥበቃ እየተደረገ በመሆኑ ምክንያት እንዲሁም ኤርትራ ባደረገችዉ መልሶ ጥቃት ምክንያት ከፍተኛ አደጋ የደረሰበት የወያኔ ሰራዊት እንከን የገጠመው ከመሆኑ በተጨማሪ የሰራዊት ክዳት ከፍተኛ ችግር ማድረሱም ተረጋግጧል!

በሰሞን በተቀሰቀሰዉ ጦርነት ብቻ ከ140 በላይ ወታደሮች ከሰሜኑ እዝ በመኮብለል የተሰወሩ ሲሆን አንድ በጄኔራልነት ማእረግ ላይ የሚገኝ አመራር ብዛት ያላቸዉ ወታደሮችን ይዞ ወደ ኤርትራ ገብቷል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

Received on Sat Jun 18 2016 - 20:06:42 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved