Ethsat.com: ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ትልቅ የገበያ ማእከል ገንብተው እያከራዩ ነው

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Fri, 3 Jun 2016 01:04:49 +0200

ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ትልቅ የገበያ ማእከል ገንብተው እያከራዩ ነው

Watch this:
http://video.ethsat.com/?p=24432
June 2, 2016

samora Yenus ግንቦት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ መከላከያ ከፍተኛ የሰራዊት አዛዦች በአዲስ አበባ ዘመናዊ የንግድ እና የመኖሪያ ቤቶችን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እያወጡ መገንባታቸውን የሚያሳዩ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች በኢሳት ሲለቀቁ ቆይተዋል። በአሁኑ ሰአት በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የሚገነቡ ዋና ዋና የሚባሉ የህንጻ ግንባታዎች በህወሃት የፖለቲካ መሪዎች፣ በህወሃት ነባር ታጋይና አሁን ከፍተኛ የጦር ኣዛዦች በሆኑ ግልሰቦች እንዲሁም ከእነርሱ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የጥቅም ቁርኝት የፈጠሩ “ባለሃብቶች” የተያዘ ነው። በዚህ ረገድ የአገሪቱን የመከላከያ ሰራዊት የሚመሩት እና ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በሁዋላ ከፍተኛውን ስልጣን በመያዝ አገሪቱን የሚመሩት ጄ/ል ሳሞራ የኑስ በባለቤታቸው አማካኝነት ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ግዛት እየመሰረቱ ነው።

ወ/ሮ ሶፍያ ይባላሉ። የ ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ባለቤት ናቸው። ጄ/ል ክንፈ ዳኘው እና ጄ/ል ሳሞራ የኑስ በሚስቶቻቸው አማካኝነት በጋብቻ ተሳስረዋል። በጋብቻ መተሳሰር ብቻ ሳይሆን ሁለቱም በረጅም ጊዜ የስልጣን እድሜያቸው በአገሪቱ ውስጥ የኢኮኖሚ ግዛት እየመሰረቱ ነው። ጄ/ል ክንፈ ዳኘው የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ወይም ሜቴክ ስራ አስኪያጅ ናቸው። ሜቲክ ደግሞ በቅርቡ 10 የስኳር ፕሮጅክቶችን እገነባለሁ ብሎ ከስኳር ልማት ድርጅት ጋር የኮንትራት ስምምነት ካደረገ በሁዋላ ፣ ፕሮጀክቶቹን ለመስራት ባለመቻሉ ከ 77 ቢሊዮን ብር  የሃገር ሃብት ያወደመ ድርጅት ነው። ሜቴክ በቀድሞው እና በኢህአዴግ መንግስት የተገነቡ ፋብሪካዎችን አጣምሮ የሚያስተዳድር ድርጅት ሲሆን፣ በስሩም ጋፋት አርማመንት ኢንዱስትሪ፣ ሆሙቾ ኮሚኒኬሽን ኢንዱስትሪ፣ ሃይቴክ ኢንዱስትሪ፣ ደጀን አቪየሽን እንዱስትሪ፣ አዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ፣ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ፣ አዳማ እርሻ ኢንዱስትሪ፣ ኢትዮ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ፣ ህብረት ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ፣ ብረታብረትና ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ፣ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ፣ አቃቂ ቤዚክ ሜታል እንዱስትሪ፣ ሎኮሞቲቭ ንኡስ እንዱስትሪ፣ ነዳጅና ፕሮፔላንትን ንኡስ እንዱስትሪ እንዲሁም ኢትዮ ፓወር ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የተባሉ ድርጅቶችን ያስተዳድራል። መንግስት በአገሪቱ ውስጥ ከሚያስገነባቸው የብረታብረት ስራዎች ውስጥ አብዛኛውን ፕሮጀክት የሚወስደው ሜቲክ፣ የወሰዳቸውን ፕሮጀክቶች በወቅቱ ካለማስረከቡም በላይ ስራዎች ጥራት የላቸውም። ለማዳበሪያ ግንባታ፣ ለመብራት ሃይል፣ ለአባይ ግድብ ግንባታና ለሌሎችም ፕሮጀክቶች መቴክ የወሰደውን ድርሻ ባለመወጣት አቤቱታዎች በተደጋጋሚ ይቀርቡበታል።የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ መንግስት በሜቴክ ላይ ተደጋጋመ ቅሬታዎች ከአገር ተቆርቋሪ ዜጎችና ከመንግስት መስሪያ ቤቶች ሃላፊዎች ቢቀርብለትም አንድም እርምጃ መውሰድ አልቻለም። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱን በጀኔራል ሳሞራ የኑስና በጄ/ል ክንፈ ዳኘው መካከል ያለው ቤተሰባዊ ትስስር እና የፈጠሩት ግዙፍ የቢዝነስና የደህንነት ግዛት ነው።

ጄ/ል ሳሞራ የኑስ በባለቤታቸው በወ/ሮ ሶፍያ አማካኝነት በገነቡት የአስመጪና ላኪ የንግድ ድርጅት በሜቴክና በመከላከያ ስም ያለ ቀረጥ ከውጭ ያስገባሉ። በሚያገኙትም ትርፍ በአዲስ አበባ እና በትግራይ በርካታ የሪል ስቴት ግንባታዎችን አካሂደዋል። ጄ/ል ሳሞራ በባለቤታቸው ስም ካስገነቡዋቸው ግዙፍ የንግድ ማእከሎች መካከል ቄራ አካባቢ ገብሬል ቤተክርስቲያንን አለፍ ብሎ የሚገኘው ሶፊያ የንግድ ማእከል Sofina Mall የተባለው አንዱ ነው። ሶፊያ ሞል ለንግድ እንቅስቃሴ አመቺ በሆነ ሰፊ ቦታ ላይ የተገነባ ሲሆን በውስጡ ባንኮች፣ የመድህን ድርጅቶች፣ ካፌዎች፣ የልብስና የጫመ መደብሮች፣ ትምህርት ቤቶች፣   የፎቶ ስቱዲዮዎች፣ የመኪና አከራይ ድርጅቶች ፣ ኢትዮ ቴልኮምና ሌሎችም በርካታ ደርጅቶች ተከራይተውታል። ሰፊ የመኪና ማቆሚያ ( ፓርኪንግ) ያለው ይህ የንግድ ማእከል በየወሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ለጄ/ል ሳሞራና ባለቤታቸው ያስገባል። የህንጻውን የውስጥ ክፍል በተመለከተ ወኪላችን የቀረጸው ይህን ይመሰላል ። ጄ/ል ሳሞራ ወርሃዊ ደሞዛቸው ከ6 ሺ ባይበልጥም መንግስት ልዩ ጥበቃ የሚያደርግበትና ከ200 ሺ ብር በላይ ወርሃዊ ኪራይ የሚከፈልበት ዘመናዊ መኖሪያ ቤት አላቸው።

********************************************************************************

የፌደራል ፖሊስ አባላት ስራቸውን የሚለቁት በደሞዝ ማነስና የአላማ ጽናት ጉድለት አኳያ ነው ሲል ኮሚሽኑ አስታወቀ

June 2, 2016

ግንቦት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በአምስት አመት እቅዱ ላይ መስሪያ ቤቱን የሚለቁ ወታደሮች መበራከታቸውን እና  አዳዲስ አባላትን ለማሰልጠን የተደረገው ጥረትም አለመሳካቱን ገልጿል። መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ዝርዝር ሪፖርት ላይ ለፍልሰቱ የሰጠው ምክንያት ኢኮኖሚያዊና የአቋም መላላት የሚል ነው። በሃገራችን ይላል ሰነዱ “ ካለው አጠቃላይ እድገት የሚመነጭ የስራ አማራጭ በማየትና አንዳንድ የአላማ ጽናት የሚጎድላቸው አባላትም በኩብለላም ሆነ ህጋዊ የስንብት ጥያቄ በማቅረብ የሚለቁ አባሎች ስላሉ ፍልሰቱን ሙሉ በሙሉ ማስቆም ባለመቻሉ የሰላም ሰራዊት ግንባታ ትግበራ እንደተጠበቀ ሆኖ የሰራዊቱን የኑሮ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለማሻሻል የሚያግዙ ድጋፎች ያስፈልጋሉ ።”

“በየጊዜው በተቋሙ የሚታየው የሰው ሀይል ፍልሰትና አዳዲስ የሰው ሀይል ተቋሙ ለመሳብና ለማቆየት ያለው ሁኔታ ምቹ አለመሆን” ስጋት ፈጥሮብናል የሚለው ፌደራል ፖሊስ፣ ከኢኮኖሚና ከኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን እድገት ጋር ተያይዞ የወንጀል አፈጻጸሞች እየከበዱና እየተራቀቁ መምጣታቸው የህግ ማስከበር ስራውን አክብዶታል ብሎአል። ሐይማኖትን እንደ ሽፋን የሚጠቀሙ አክራሪ ቡድኖች እንቅስቃሴ በየጊዜው በአለም ላይ እየተበራከተ መምጣቱና ተለዋዋጭ የሽብር ዜዴዎችን የመተግበር ሁኔታቸው እያደገ መምጣት፤ አንዳንድ ቡድኖች የሀገራችንን የብሔር ብሔረሰቦች ልዩነት እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ግጭት በመፍጠር ድብቅና አፍራሽ የፖለቲካ አላማቸውን ለመተግበር የሚያደርጉት እንቅስቃሴ፤ በሰላማዊ መንገድ ተደራጅተውና ትክክለኛ ህዝባዊ አመለካከት ይዘው ለነጻ ምርጫ ለመወዳደር አቅም ያጡ አንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች ህዝቡ ውስጥ ተሸሽገው ድብቅ አላማቸውን ለማሳካት ብጥብጥና ሁከት ለማስነሳት የሚሞክሩ መሆኑ፤ የሽብርተኝነት ወንጀል ለመፈጸም የሚያግዙ ሁኔታዎች እና ጂኦፖሊቲካል አካባቢ ውስጥ መኖራችን የህግ ማስከበርና ወንጀልን የመከላከል አላማችን ላይ ጫና እየፈጠረ ነው ሲል ይዘረዝራል።

የፈደራል ፖሊስ መደበኛ አባላት በአብዛኛውም የተቃዋሚ ደጋፊዎች መሆናቸው በተለይም በኢሳትና በፌስቡክ የሚለቀቁ መረጃዎችን በንቃት እንደሚከታተሉ ምንጮች ይገልጻሉ። የፌደራል ፖሊስ አመራሮች የሚፈጽሙትን ሙስና እና የሰራዊቱን ህይወት በተመለከተ ኢሳት በሚቀጥለው ሳምንት መግቢያ ላይ በሰነድ የተደገፈ ልዩ ሪፖርት እንደሚያቀርብ ለመግልጽ ይወዳል።

Received on Thu Jun 02 2016 - 19:04:49 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved